Skip to content
← Esther

Chapter 8 · Amharic

Esther

1በዚያም፡ቀን፡ንጉሡ፡አርጤክስስ፡የአይሁድን፡ጠላት፡የሐማን፡ቤት፡ለንግሥቲቱ፡ለአስቴር፡ ሰጠ።አስቴርም፡ለርሷ፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡ነግራው፡ነበርና፥መርዶክዮስ፡ወደ፡ንጉሡ፡ፊት፡ገባ።

2ንጉሡም፡ከሐማ፡ያወለቀውን፡ቀለበቱን፡አወጣ፥ለመርዶክዮስም፡ሰጠው።አስቴርም፡በሐማ፡ቤት፡ላይ፡ መርዶክዮስን፡ሾመች። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

3አስቴርም፡እንደ፡ገና፡በንጉሡ፡ፊት፡ተናገረች፤በእግሩም፡ላይ፡ወድቃ፡እያለቀሰች፡የአጋጋዊውን፡ የሐማን፡ክፋትና፡በአይሁድ፡ላይ፡የተተነኰለውን፡ተንኰል፡ይሽር፡ዘንድ፡ለመነችው።

4ንጉሡም፡የወርቁን፡ዘንግ፡ለአስቴር፡ዘረጋላት፤አስቴርም፡ተነሥታ፡በንጉሡ፡ፊት፡ቆመችና፦

5ንጉሡን፡ደስ፡ቢያሠኘው፥በፊቱም፡ሞገስ፡አግኝቼ፡እንደ፡ኾነ፥ይህም፡ነገር፡በፊቱ፡ቅን፡ቢኾን፥እኔም፡ በርሱ፡ዘንድ፡ተወድጄ፡እንደ፡ኾነ፥አጋጋዊው፡የሐመዳቱ፡ልጅ፡ሐማ፡በንጉሡ፡አገር፡ዅሉ፡ያሉትን፡ አይሁድ፡ለማጥፋት፡የጻፈው፡ተንኰል፡ይገለበጥ፡ዘንድ፡ይጻፍ።

6እኔ፡በሕዝቤ፡ላይ፡የሚወርደውን፡ክፉ፡ነገር፡አይ፡ዘንድ፡እንዴት፡እችላለኹ፧ወይስ፡የዘመዶቼን፡ጥፋት፡ አይ፡ዘንድ፡እንዴት፡እችላለኹ፧አለች።

7ንጉሡም፡አርጤክስስ፡ንግሥቲቱን፡አስቴርንና፡አይሁዳዊውን፡መርዶክዮስን፦እንሆ፥የሐማን፡ቤት፡ ለአስቴር፡ሰጥቻለኹ፥ርሱም፡እጆቹን፡በአይሁድ፡ላይ፡ስለ፡ዘረጋ፡በግንድ፡ላይ፡ተሰቀለ።

8በንጉሡ፡ስም፡የተጻፈና፡በንጉሡ፡ቀለበት፡የታተመ፡አይገለበጥምና፥እናንተ፡ደግሞ፡ደስ፡የሚያሠኛችኹን፡ በንጉሡ፡ስም፡ስለ፡አይሁድ፡ጻፉ፥በንጉሡም፡ቀለበት፡ዐትሙ፡አላቸው።

9በዚያን፡ጊዜም፡ኒሳን፡በተባለው፡በመዠመሪያው፡ወር፡ከወሩም፡በኻያ፡ሦስተኛው፡ቀን፡የንጉሡ፡ ጸሓፊዎች፡ተጠሩ፤መርዶክዮስም፡ስለ፡አይሁድ፡እንዳዘዘው፡ዅሉ፡ከህንድ፡ዠምሮ፡እስከ፡ኢትዮጵያ፡ድረስ፡ በመቶ፡ኻያ፡ሰባቱ፡አገሮች፡ላሉ፡ሹማምትና፡አለቃዎች፡ዐዛውንትም፡ለያንዳንዱም፡አገር፡እንደ፡ጽሕፈቱ፡ ለያንዳንዱም፡ሕዝብ፡እንደ፡ቋንቋው፡ለአይሁድም፡እንደ፡ጽሕፈታቸውና፡እንደ፡ቋንቋቸው፡ተጻፈ።

10በንጉሡም፡በአርጤክስስ፡ስም፡አስጻፈው፥በንጉሡም፡ቀለበት፡አሳተመው፤ደብዳቤውንም፡በንጉሡ፡ፈረስ፡ ቤት፡በተወለዱት፥ለንጉሡም፡አገልግሎት፡በተለዩ፡በፈጣን፡ፈረሶች፡በተቀመጡ፡መልእክተኛዎች፡እጅ፡ ሰደደው።

11በዚያም፡ደብዳቤ፡በከተማዎቹ፡ዅሉ፡የሚኖሩት፡አይሁድ፡እንዲሰበሰቡ፥ለሕይወታቸውም፡ እንዲቆሙ፥በጥል፡የሚነሡባቸውን፡የሕዝቡንና፡የአገሩን፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ከሕፃናታቸውና፡ከሴቶቻቸው፡ጋራ፡ እንዲያጠፉና፡እንዲገድሉ፡እንዲደመስሱም፥ምርኳቸውንም፡እንዲዘርፉ፡ንጉሡ፡ፈቀደላቸው።

12ይህም፡አዳር፡በሚባለው፡በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ወር፡በዐሥራ፡ሦስተኛው፡ቀን፡በንጉሡ፡በአርጤክስስ፡ አገሮች፡ዅሉ፡ባንድ፡ቀን፡እንዲኾን፡ነው።

13አይሁድም፡ጠላቶቻቸውን፡እንዲበቀሉ፡በዚያ፡ቀን፡ይዘጋጁ፡ዘንድ፡የደብዳቤው፡ቅጅ፡በያገሩ፡ላሉ፡ አሕዛብ፡ዅሉ፡ታወጀ።

14ለንጉሡ፡አገልግሎት፡በተለዩ፡በፈጣን፡ፈረሶች፡የተቀመጡት፡መልእክተኛዎች፡በንጉሡ፡ትእዛዝ፡ ተርበትብተውና፡ቸኵለው፡ወጡ፤ዐዋጁም፡በሱሳ፡ግንብ፡ተነገረ።

15መርዶክዮስም፡በሰማያዊና፡በነጭ፡ሐር፡የተሠራውን፡የንጉሡን፡የክብር፡ልብስ፡ለብሶ፡ታላቅም፡የወርቅ፡ አክሊል፡ደፍቶ፡ከጥሩ፡በፍታና፡ከሐምራዊ፡ግምጃ፡የተሠራ፡መጐናጸፊያ፡ተጐናጽፎ፡ከንጉሡ፡ፊት፡ ወጣ፤የሱሳም፡ከተማ፡ደስ፡አላት፥እልልም፡አለች።

16ለአይሁድም፡ብርሃንና፡ደስታ፡ተድላና፡ክብርም፡ኾነ።

17የንጉሡም፡ትእዛዝና፡ዐዋጅ፡በደረሰበት፡አገርና፡ከተማ፡ዅሉ፡ለአይሁድ፡ደስታና፡ተድላ፥የግብዣም፡ ቀን፡መልካምም፡ቀን፡ኾነ።አይሁድንም፡መፍራት፡ስለ፡ወደቀባቸው፡ከምድር፡አሕዛብ፡ብዙ፡ሰዎች፡ አይሁድ፡ኾኑ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source