Skip to content
← Ezekiel

Chapter 48 · Amharic

Ezekiel

1የነገዶችም፡ስም፡ይህ፡ነው።በሔትሎን፡መንገድ፡አጠገብ፡ወደሐማት፡መግቢያ፡በደማስቆም፡ድንበር፡ ባለው፡በሐጻረ፡ዔኖን፥በሐማትም፡አጠገብ፡በሰሜን፡በኩል፡ካለው፡ከሰሜን፡ድንበር፡ ይዠምራል።ወርዳቸውም፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ይኾናል።ለዳን፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ ይኾናል።

2ከዳንም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለአሴር፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ ይኾናል።

3ከአሴርም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለንፍታሌም፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ ይኾናል።

4ከንፍታሌም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለምናሴ፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ ይኾናል።

5ከምናሴም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለኤፍሬም፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ ይኾናል።

6ከኤፍሬምም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለሮቤል፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ ይኾናል።

7ከሮቤልም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለይሁዳ፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ ይኾናል።

8ከይሁዳም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለመባ፡የኾነ፡የዕጣ፡ክፍል፡ ይኾናል፤ወርዱ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ክንድ፡ይኾናል፡ርዝመቱም፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ ከዕጣ፡ክፍሎች፡እንደ፡አንዱ፡ይኾናል፥መቅደሱም፡በመካከሉ፡ይኾናል።

9ለእግዚአብሔር፡የምታቀርቡት፡መባ፡ርዝመቱ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ወርዱም፡ኻያ፡ሺሕ፡ክንድ፡ይኾናል።

10ለእነዚህም፡ለካህናቱ፡የተቀደሰ፡መባ፡ይኾናል፤በሰሜን፡በኩል፡ርዝመቱ፡ኻያ፡ዐምስት፡ ሺሕ፥በምዕራብም፡በኩል፡ወርዱ፡ዐሥር፡ሺሕ፥በምሥራቅም፡በኩል፡ወርዱ፡ዐሥር፡ሺሕ፥በደቡብም፡በኩል፡ ርዝመቱ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ክንድ፡ይኾናል።የእግዚአብሔርም፡መቅደስ፡በመካከሉ፡ይኾናል።

11የእስራኤልም፡ልጆች፡በሳቱ፡ጊዜ፥ሌዋውያን፡እንደ፡ሳቱ፡ላልሳቱት፡ሥርዐቴን፡ለጠበቁት፡ከሳዶቅ፡ልጆች፡ ወገን፡ለተቀደሱት፡ካህናት፡ይኾናል።

12ከምድርም፡መባ፡የተለየ፡መባ፡ይኾንላቸዋል፥ከዅሉም፡ይልቅ፡የተቀደሰ፡ይኾናል፤በሌዋውያን፡ድንበር፡ አጠገብ፡ይኾናል።

13በካህናቱም፡ድንበር፡አንጻር፡ርዝመቱ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ወርዱም፡ዐሥር፡ሺሕ፡የኾነ፡ዕጣ፡ ለሌዋውያን፡ይኾናል፤ርዝመቱ፡ዅሉ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ወርዱም፡ኻያ፡ሺሕ፡ክንድ፡ይኾናል።

14ለእግዚአብሔርም፡የተቀደሰ፡ነውና፥ከርሱ፡ምንም፡አይሸጡም፡አይለውጡምም፥የምድሩም፡በኵራት፡ አይፋለስም።

15በኻያ፡ዐምስቱም፡ሺሕ፡አንጻር፡ዐምስት፡ሺሕ፡ወርድ፡ያለው፡የቀረ፡ስፍራ፡ለከተማዪቱ፡ለጋራ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ጕዳይዋ፥ለመኖሪያ፡ለማስማርያም፡ይኾናል፤ከተማዪቱም፡በመካከሉ፡ትኾናለች።

16ልኳም፡ይህ፡ነው፤በሰሜን፡በኩል፡አራት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፥በደቡብም፡በኩል፡አራት፡ሺሕ፡ ዐምስት፡መቶ፥በምሥራቅም፡በኩል፡አራት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፥በምዕራብም፡በኩል፡አራት፡ሺሕ፡ዐምስት፡ መቶ፡ክንድ፡ይኾናል።

17ለከተማዪቱም፡ማሰማሪያ፡ይኖራታል፤በሰሜን፡በኩል፡ኹለት፡መቶ፡ዐምሳ፥በደቡብም፡በኩል፡ኹለት፡ መቶ፡ዐምሳ፥በምሥራቅም፡በኩል፡ኹለት፡መቶ፡ዐምሳ፥በምዕራብም፡በኩል፡ኹለት፡መቶ፡ዐምሳ፡ክንድ፡ ይኾናል።

18በተቀደሰው፡መባ፡አንጻር፡የተረፈው፡ርዝመቱ፡ወደ፡ምሥራቅ፡ዐሥር፡ሺሕ፡ወደ፡ምዕራብም፡ዐሥር፡ ሺሕ፡ክንድ፡ይኾናል።በተቀደሰው፡መባ፡አንጻር፡ይኾናል።ፍሬውም፡ከተማዪቱን፡ለሚያገለግሉ፡ለመብል፡ ይኾናል።

19ከእስራኤል፡ነገድ፡ዅሉ፡ከተማዪቱን፡የሚያገለግሉ፡ያርሱታል።

20መባው፡ዅሉ፡ርዝመቱ፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ወርዱም፡ኻያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ክንድ፡ ይኾናል፤የተቀደሰውን፡መባ፡ከከተማዪቱ፡ይዞታ፡ጋራ፡አራት፡ማእዘን፡አድርጋችኹ፡ትሰጣላችኹ።

21በተቀደሰው፡መባና፡በከተማዪቱ፡ይዞታ፡በዚህና፡በዚያ፡ወገን፡የቀረው፡ለአለቃው፡ይኾናል፤በመባው፡ በኻያ፡ዐምስቱ፡ሺሕ፡ፊት፡ወደ፡ምሥራቁ፡ድንበር፥በምዕራብም፡በኩል፡በኻያ፡ዐምስቱ፡ሺሕ፡ፊት፡ወደ፡ ምዕራቡ፡ድንበር፥እንደ፡ዕጣ፡ክፍል፡ዅሉ፡መጠን፥ለአለቃው፡ይኾናል፤የተቀደሰውም፡መባና፡ቤተ፡ መቅደሱ፡በመካከሉ፡ይኾናል።

22የሌዋውያንም፡ርስት፡የከተማዪቱም፡ይዞታ፡ለአለቃው፡በኾነው፡መካከል፡ይኾናል፤በይሁዳ፡ድንበርና፡ በብንያም፡ድንበር፡መካከል፡የአለቃ፡ዕጣ፡ክፍል፡ይኾናል።

23ለቀሩትም፡ነገዶች፡እንዲህ፡ይኾናል፤ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለብንያም፡አንድ፡የዕጣ፡ ክፍል፡ይኾናል።

24ከብንያምም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለስምዖን፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ ይኾናል።

25ከስምዖንም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለይሳኮር፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ ይኾናል።

26ከይሳኮርም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለዛብሎን፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ ይኾናል።

27ከዛብሎንም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡ከምሥራቅ፡ዠምሮ፡እስከ፡ምዕራብ፡ድረስ፡ለጋድ፡አንድ፡የዕጣ፡ክፍል፡ ይኾናል።

28ከጋድም፡ድንበር፡ቀጥሎ፡በደቡብ፡በኩል፡ድንበሩ፡ከታማር፡ዠምሮ፡እስከሜሪባ፡ቃዴስ፡ውሃ፡ እስከግብጽ፡ወንዝ፡እስከ፡ታላቁ፡ባሕር፡ድረስ፡ይኾናል።

29ርስት፡አድርጋችኹ፡ለእስራኤል፡ነገዶች፡በዕጣ፡የምታካፍሏት፡ምድር፡ይህች፡ናት፥የያንዳንዱም፡ዕጣ፡ እንደዚህ፡ነው፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

30የከተማዪቱም፡መውጫዎች፡እነዚህ፡ናቸው።በሰሜን፡ወገን፡ልኩ፡አራት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፡ ነው።

31የከተማዪቱ፡በሮች፡እንደ፡እስራኤል፡ነገዶች፡ስም፡ይኾናሉ፤በሰሜን፡በኩል፡አንዱ፡የሮቤል፡በር፡ አንዱም፡የይሁዳ፡በር፡አንዱም፡የሌዊ፡በር፥ሦስት፡በሮች፡ይኾናሉ።

32በምሥራቁም፡ወገን፡አራት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፥ሦስትም፡በሮች፡አሉ፤አንዱ፡የዮሴፍ፡በር፡ አንዱም፡የብንያም፡በር፡አንዱም፡የዳን፡በር፡ነው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

33በደቡቡም፡ወገን፡ልኩ፡አራት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፥ሦስትም፡በሮች፡አሉ፤አንዱ፡የስምዖን፡ በር፡አንዱም፡የይሳኮር፡በር፡አንዱም፡የዛብሎን፡በር፡ነው።

34በምዕራቡም፡ወገን፡ልኩ፡አራት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ክንድ፥ሦስትም፡በሮች፡አሉ፤አንዱ፡የጋድ፡በር፡ አንዱም፡የአሴር፡በር፡አንዱም፡የንፍታሌም፡በር፡ነው።

35ዙሪያዋም፡ዐሥራ፡ስምንት፡ሺሕ፡ክንድ፡ይኾናል፥ከዚያም፡ቀን፡ዠምሮ፡የከተማዪቱ፡ ስም፦እግዚአብሔር፡በዚያ፡አለ፡ተብሎ፡ይጠራል፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source