1ወደመቅደሱም፡መዝጊያ፡መለሰኝ፤እንሆም፥ውሃ፡ከቤቱ፡መድረክ፡በታች፡ወደ፡ምሥራቅ፡ይወጣ፡ ነበር፥የቤቱ፡ፊት፡ወደ፡ምሥራቅ፡ይመለከት፡ነበርና፤ውሃውም፡ከቤቱ፡ከቀኝ፡ወገን፡በታች፡በመሠዊያው፡ በደቡብ፡በኩል፡ይወርድ፡ነበር።
2በሰሜኑም፡በር፡በኩል፡አወጣኝ፤በስተውጭ፡ባለው፡መንገድ፥ወደ፡ምሥራቅ፡ወደሚመለከት፡በስተውጭ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ወዳለው፡በር፡አዞረኝ፤እንሆም፥ውሃው፡በቀኙ፡ወገን፡ይፈስ፟፡ነበር።
3ሰውዬውም፡ገመዱን፡በእጁ፡ይዞ፡ወደ፡ምሥራቅ፡ወጣ፡አንድ፡ሺሕም፡ክንድ፡ለካ፥በውሃውም፡ውስጥ፡ አሻገረኝ፥ውሃም፡እስከ፡ቍርጭምጭሚት፡ደረሰ።
4ደግሞ፡አንድ፡ሺሕ፡ለካ፡በውሃውም፡ውስጥ፡አሻገረኝ፥ውሃውም፡እስከ፡ጕልበት፡ደረሰ።ደግሞም፡ አንድ፡ሺሕ፡ለካ፡በውሃውም፡ውስጥ፡አሻገረኝ፥ውሃውም፡እስከ፡ወገብ፡ደረሰ።
5ደግሞ፡አንድ፡ሺሕ፡ለካ፡ልሻገረውም፡የማልችለው፡ወንዝ፡ኾነ፤ውሃውም፡ጥልቅ፡ነበረ፥የሚዋኝበትም፡ ውሃ፡ነበረ፤ሰው፡ሊሻገረው፡የማይችለው፡ወንዝ፡ነበረ።
6ርሱም፦የሰው፡ልጅ፡ሆይ፥አይተኻልን፧አለኝ።አመጣኝም፥ወደወንዙም፡ዳር፡መለሰኝ።
7በተመለስኹም፡ጊዜ፥እንሆ፥በወንዙ፡ዳር፡በዚህና፡በዚያ፡እጅግ፡ብዙ፡ዛፎች፡ነበሩ።
8ርሱም፡እንዲህ፡አለኝ፦ይህ፡ውሃ፡ወደምሥራቅ፡ምድር፡ይወጣል፡ወደ፡ዐረባም፡ይወርዳል፡ወደ፡ ባሕሩም፡ይገባል፤ወደ፡ባሕሩም፡ወደረከሰው፡ውሃ፡በገባ፡ጊዜ፡ውሃው፡ይፈወሳል።
9ሕያው፡ነፍስ፡ያለው፡ተንቀሳቃሽ፡ዅሉ፡ወንዙ፡በመጣበት፡ስፍራ፡ዅሉ፡በሕይወት፡ይኖራል፤ይህም፡ ውሃ፡በዚያ፡ስለ፡ደረሰ፡ዓሣዎች፡እጅግ፡ይበዛሉ፤የባሕሩም፡ውሃ፡ይፈወሳል፥ወንዙም፡በሚመጣበት፡ያለው፡ ዅሉ፡በሕይወት፡ይኖራል።
10አጥማጆችም፡በዚያ፡ይቆማሉ፤ከዐይንጋዲ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዐይንኤግላይም፡ድረስ፡መረብ፡መዘርጊያ፡ ይኾናል፤ዓሣዎችም፡እንደ፡ታላቁ፡ባሕር፡ዓሣዎች፡በየወገናቸው፡እጅግ፡ይበዛሉ።
11ረግረጉና፡ዕቋሪው፡ውሃ፡ግን፡ጨው፡እንደ፡ኾነ፡ይኖራል፡እንጂ፡አይፈወስም።
12በወንዙም፡አጠገብ፡በዳሩ፡ላይ፡በዚህና፡በዚያ፡ፍሬው፡የሚበላ፡ዛፍ፡ዅሉ፡ይበቅላል፥ቅጠሉም፡ አይረግፍም፡ፍሬውም፡አይጐድልም፤ውሃውም፡ከመቅደስ፡ይወጣልና፥በየወሩ፡ዅሉ፡የፍሬ፡በኵር፡ ያገኛል፤ፍሬውም፡ለመብል፡ቅጠሉም፡ለመድኀኒት፡ይኾናል።
13ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ርስት፡አድርጋችኹ፡ለዐሥራ፡ኹለቱ፡የእስራኤል፡ነገዶች፡ ምድሪቱን፡የምትከፍሉበት፡ድንበር፡ይህ፡ነው።ለዮሴፍ፡ኹለት፡ዕድል፡ፈንታ፡ይኾናል።
14ለአባቶቻችኹ፡እሰጣቸው፡ዘንድ፥ምዬ፡ነበርና፥እናንተ፡እኩል፡አድርጋችኹ፡ተካፈሉት፡ይህችም፡ምድር፡ ርስት፡ትኾናችዃለች።
15የምድሪቱም፡ድንበር፡ይህ፡ነው።በሰሜኑ፡ወገን፡ከታላቁ፡ባሕር፡ዠምሮ፡በሔትሎን፡መንገድ፡ወደጽዳድ፡ መግቢያ፤
16ሐማት፥ቤሮታ፥በደማስቆ፡ድንበርና፡በሐማት፡ድንበር፡መካከል፡ያለው፡ሲብራይም፥በሐውራን፡ድንበር፡ አጠገብ፡ያለው፡ሐጸርሃቲኮን።
17ድንበሩ፡ከባሕሩ፡በደማስቆ፡ድንበር፡ላይ፡ያለው፡ሐጻረ፡ዔኖን፡ይኾናል፥በሰሜንም፡በኩል፡የሐማት፡ ድንበር፡አለ።የሰሜኑ፡ድንበር፡ይህ፡ነው።
18የምሥራቁም፡ድንበር፡በሐውራን፡በደማስቆና፡በገለዓድ፡በእስራኤልም፡ምድር፡መካከል፡ዮርዳኖስ፡ ይኾናል።ከሰሜኑ፡ድንበር፡ዠምሮ፡እስከምሥራቁ፡ባሕር፡እስከ፡ታማር፡ድረስ፡የምሥራቁ፡ድንበር፡ይህ፡ነው።
19የደቡቡም፡ድንበር፡ከታማር፡ዠምሮ፡እስከሜርባ፡ቃዴስ፡ውሃ፡እስከግብጽ፡ወንዝ፡እስከ፡ታላቁ፡ባሕር፡ ድረስ፡ይኾናል።የደቡቡ፡ድንበር፡ይህ፡ነው።
20የምዕራቡም፡ድንበር፡ከደቡቡ፡ድንበር፡ዠምሮ፡እስከሐማት፡መግቢያ፡አንጻር፡ድረስ፡ታላቁ፡ባሕር፡ ይኾናል።የምዕራቡ፡ድንበር፡ይህ፡ነው።
21እንዲሁ፡ይህችን፡ምድር፡እንደ፡እስራኤል፡ነገዶች፡መጠን፡ለእናንተ፡ትካፈላላችኹ።
22ለእናንተና፡በእናንተ፡መካከል፡ለሚቀመጡ፡በእናንተም፡መካከል፡ልጆችን፡ለሚወልዱ፡መጻተኛዎች፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ርስት፡አድርጋችኹ፡በዕጣ፡ትካፈሏታላችኹ፤እነርሱም፡በእስራኤል፡ልጆች፡መካከል፡እንዳሉ፡የአገር፡ልጆች፡ ይኾኑላችዃል፥በእስራኤልም፡ነገዶች፡መካከል፡ከእናንተ፡ጋራ፡ርስትን፡ይወርሳሉ።
23መጻተኛውም፡በማናቸውም፡ነገድ፡መካከል፡ቢቀመጥ፡በዚያ፡ርስቱን፡ትሰጡታላችኹ፥ይላል፡ጌታ፡ እግዚአብሔር።