Skip to content
← Ezra

Chapter 1 · Amharic

Ezra

1በኤርምያስም፡አፍ፡የተናገረው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ይፈጸም፡ዘንድ፡በፋርስ፡ንጉሥ፡በቂሮስ፡ በመዠመሪያው፡ዓመት፡እግዚአብሔር፡የፋርስን፡ንጉሥ፡የቂሮስን፡መንፈስ፡አስነሣ፤ርሱም፡በመንግሥቱ፡ ዅሉ፡ዐዋጅ፡አስነገረ፥ደግሞም፡በጽሕፈት፡አድርጎ፡እንዲህ፡አለ።

2የፋርስ፡ንጉሥ፡ቂሮስ፡እንዲህ፡ይላል፦የሰማይ፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡የምድርን፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ ሰጥቶኛል፤በይሁዳም፡ባለችው፡በኢየሩሳሌም፡ቤት፡እሠራለት፡ዘንድ፡አዞ፟ኛል፤

3ከሕዝቡ፡ዅሉ፡በእንናተ፡ዘንድ፡ማንም፡ቢኾን፡አምላኩ፡ከርሱ፡ጋራ፡ይኹን፥ርሱም፡በይሁዳ፡ወዳለችው፡ ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ይውጣ፥በኢየሩሳሌምም፡ለሚኖረው፡አምላክ፥ለእስራኤል፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡ ይሥራ፤

4በሚኖርበትም፡ስፍራ፡ዅሉ፡ለቀረው፡ሰው፡የአገሩ፡ሰዎች፡በብርና፡በወርቅ፡በዕቃም፡በእንስሳም፡ ይርዱት፤ይህም፡በኢየሩሳሌም፡ላለው፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡በፈቃዳቸው፡ከሚያቀርቡት፡ሌላ፡ይኹን።

5የይሁዳና፡የብንያም፡የአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎችም፥ካህናቱም፥ሌዋውያኑም፥በኢየሩሳሌም፡ያለውን፡ የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ለመሥራት፡ይወጡ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡መንፈሳቸውን፡ያነሣሣው፡ዅሉ፡ተነሡ።

6በዙሪያቸውም፡ያሉ፡ዅሉ፡በፈቃዳቸው፡ካቀረቡት፡ዅሉ፡ሌላ፡በብር፡ዕቃና፡በወርቅ፡በገንዘቦችና፡ በእንስሳዎች፡በሌላም፡ስጦታ፡አገዟቸው።

7ንጉሡ፡ቂሮስም፡ናቡከደነጾር፡ከኢየሩሳሌም፡ወስዶ፡በአማልክቱ፡ቤት፡ያኖራቸውን፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ ዕቃዎች፡አወጣ።

8የፋርስ፡ንጉሥ፡ቂሮስም፡በመዝገቡ፡ላይ፡በነበረው፡በሚትሪዳጡ፡እጅ፡አወጣቸው፥ለይሁዳም፡መስፍን፡ ለሰሳብሳር፡ቈጠራቸው።

9ቍጥራቸውም፡ይህ፡ነው፤ሠላሳ፡የወርቅ፡አንድ፡ሺሕም፡የብር፡ሣሕኖች፥ኻያ፡ዘጠኝም፡ቢላዎች፥

10ሠላሳ፡የወርቅ፡ደካዎች፥አራት፡መቶ፡ዐሥርም፡ሌላ፡ዐይነት፡የብር፡ደካዎች፥አንድ፡ሺሕም፡ሌላ፡ ዕቃ፡ነበረ።

11የወርቁና፡የብሩ፡ዕቃዎች፡ዅሉ፡ዐምስት፡ሺሕ፡አራት፡መቶ፡ነበሩ፤እነዚህንም፡ዅሉ፡ሰሳብሳር፡ ከባቢሎን፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ከተመለሱ፡ምርኮኛዎቹ፡ጋራ፡ወሰደ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source