Skip to content
← Ezra

Chapter 10 · Amharic

Ezra

1ዕዝራም፡እያለቀሰና፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ፊት፡እየወደቀ፡በጸለየና፡በተናዘዘ፡ጊዜ፡ከእስራኤል፡ዘንድ፡ የወንድና፡የሴት፡የሕፃናትም፡እጅግ፡ታላቅ፡ጉባኤ፡ወደ፡ርሱ፡ተሰበሰበ፤ሕዝቡም፡እጅግ፡አለቀሱ።

2ከዔላም፡ልጆች፡ወገን፡የነበረም፡የይሒኤል፡ልጅ፡ሴኬንያ፡ዕዝራን፡እንዲህ፡ብሎ፡ ተናገረው፦አምላካችንን፡በድለናል፤የምድርን፡አሕዛብ፡እንግዳዎች፡ሴቶችን፡አግብተናል፤አኹን፡ግን፡ ስለዚህ፡ነገር፡ገና፡ለእስራኤል፡ተስፋ፡አለ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

3አኹንም፡እንደ፡ጌታዬና፡የአምላካችንን፡ትእዛዝ፡እንደሚፈሩት፡ምክር፥ሴቶችን፡ዅሉ፡ከነርሱም፡ የተወለዱትን፡እንሰድ፟፡ዘንድ፡ከአምላካችን፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡እናድርግ፤እንደ፡ሕጉም፡ይደረግ።

4ይህም፡ነገር፡ለአንተ፡ይገ፟ባ፟ልና፥እኛም፡ከአንተ፡ጋራ፡ነንና፡ተነሣ፥አይዞኽ፥አድርገው።

5ዕዝራም፡ተነሣ፤አለቃዎቹንና፡ካህናቱን፡ሌዋውያኑንም፡እስራኤልንም፡ዅሉ፡እንደዚህ፡ቃል፡ያደርጉ፡ዘንድ፡ አማለ፤እነርሱም፡ማሉ።

6ዕዝራም፡ከእግዚአብሔር፡ቤት፡ፊት፡ተነሥቶ፡ወደኤልያሴብ፡ልጅ፡ወደዮሐናን፡ጓዳ፡ ገባ፤ስለምርኮኛዎቹም፡ኀጢአት፡ያለቅስ፡ነበርና፥ገብቶ፡እንጀራ፡አልበላም፥ውሃም፡አልጠጣም።

8ምርኮኛዎቹም፡ዅሉ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡እንዲሰበሰቡ፥እንደ፡አለቃዎቹና፡እንደ፡ሽማግሌዎችም፡ምክር፡ በሦስት፡ቀን፡ውስጥ፡ያልመጣ፡ዅሉ፡ንብረቱ፡ዅሉ፡እንዲወረስ፥ርሱም፡ከምርኮው፡ጉባኤ፡እንዲለይ፡ በይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡ዐዋጅ፡ነገሩ።

9ሦስት፡ቀንም፡ሳያልፍ፡በዘጠነኛው፡ወር፡ከወሩም፡በኻያኛው፡ቀን፡የይሁዳና፡የብንያም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ተሰበሰቡ።ሕዝቡም፡ዅሉ፡ስለዚህ፡ነገርና፡ስለ፡ታላቁ፡ዝናብ፡እየተንቀጠቀጡ፡ በእግዚአብሔር፡ቤት፡ፊት፡ባለው፡አደባባይ፡ተቀመጡ።

10ካህኑም፡ዕዝራ፡ተነሥቶ፦ተላልፋችዃል፤የእስራኤልን፡በደል፡ታበዙ፡ዘንድ፡እንግዳዎችን፡ሴቶች፡ አግብታችዃል።

11አኹንም፡ለአባቶቻችኹ፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡ተናዘዙ፥ደስ፡የሚያሠኘውንም፡አድርጉ፤ከምድርም፡ አሕዛብና፡ከእንግዳዎች፡ሴቶች፡ተለዩ፡አላቸው።

12ጉባኤውም፡ዅሉ፡በታላቅ፡ድምፅ፡መልሰው፡እንዲህ፡አሉ፦እንደ፡ተናገርኸን፡እናደርግ፡ዘንድ፡ ይገ፟ባ፟ናል።

13ነገር፡ግን፥የሕዝቡ፡ቍጥር፡ብዙ፡ነው፥ጊዜውም፡የትልቅ፡ዝናብ፡ጊዜ፡ነው፥በሜዳም፡ልንቆም፡ አንችልም፤በዚህም፡ነገር፡እጅግ፡በድለናልና፥ይህ፡ሥራ፡የአንድ፡ወይም፡የኹለት፡ቀን፡ሥራ፡አይደለም።

14አለቃዎቻችንም፡በጉባኤው፡ዅሉ፡ፋንታ፡ይቁሙ፤ስለዚህም፡ነገር፡የአምላካችን፡ጽኑ፡ቍጣ፡ከእኛ፡ ይመለስ፡ዘንድ፡እንግዳዎቹን፡ሴቶች፡ያገቡት፡በከተማዎቻችን፡ያሉት፡ዅሉ፡በተቀጠረው፡ጊዜ፡ ይምጡ፥ከነርሱም፡ጋራ፡የከተማ፡ዅሉ፡ሽማግሌዎችና፡ፈራጆች፡ይምጡ።

15ነገር፡ግን፥የዐሳሄል፡ልጅ፡ዮናታንና፡የቴቁዋ፡ልጅ፡የሕዝያ፡ይህን፡ነገር፡ተቃወሙ፤ሜሱላምና፡ ሌዋዊውም፡ሳባታይ፡ረዷቸው።

16ምርኮኛዎቹም፡እንዲህ፡አደረጉ፤ካህኑ፡ዕዝራም፡የአባቶችም፡ቤቶች፡አለቃዎች፡በያባቶቻቸው፡ቤቶች፡ ተለዩ፥ዅሉም፡በየስማቸው፡ተጻፉ፤በዐሥረኛውም፡ወር፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ነገሩን፡ይመረምሩ፡ዘንድ፡ ተቀመጡ።

17እስከመዠመሪያው፡ወር፡እስከመዠመሪያው፡ቀን፡ድረስ፡ሠረተው፡እንግዳዎቹን፡ሴቶች፡ያገቡትን፡ ሰዎች፡ዅሉ፡መርምረው፡ጨረሱ።

18ከካህናቱም፡ወገን፡ልጆች፡እንግዳዎቹን፡ሴቶች፡ያገቡ፡ሰዎች፡ተገኙ፤ከኢዮሴዴቅ፡ልጅ፡ከኢያሱ፡ ልጆችና፡ከወንድሞቹ፥መዕሴያ፥አልዓዛር፥ያሪብ፥ጎዶልያስ።

19ሚስቶቻቸውን፡ይፈቱ፡ዘንድ፡እጃቸውን፡ሰጡ፤ስለ፡በደላቸውም፡ከመንጋው፡አንድ፡አውራ፡በግ፡ ለበደል፡መሥዋዕት፡አቀረቡ።

20ከኢሜር፡ልጆችም፤ዐናኒና፡ዝባድያ።

21ከካሪም፡ልጆችም፡መዕሴያ፥ኤልያስ፥ሸማያ፥ይሒኤል፥ዖዝያ።

22ከፋስኩር፡ልጆችም፤ኤልዮዔናይ፥መዕሴያ፥ይስማኤል፥ናትናኤል፥ዮዛባት፥ኤልዓሣ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

23ከሌዋውያንም፤ዮዛባት፥ሰሜኢ፥ቆሊጣስ፡የሚባል፡ቆልያ፥ፈታያ፥ይሁዳ፥አልዓዛር።

24ከመዘምራንም፤ኤልያሴብ፤ከበረኛዎችም፤ሰሎም፥ጤሌም፥ኡሪ።

25ከእስራኤልም፡ከፋሮስ፡ልጆች፤ራምያ፥ይዝያ፥መልክያ፥ሚያሚን፥አልዓዛር፥መልክያ፥በናያስ።

26ከዔላም፡ልጆችም፤ሙታንያ ፥ዘካርያስ፥ይሒኤል ፥ዐብዲ፥ይሬሞት፥ኤልያ።

27ከዛቱዕ፡ልጆችም፤ዔሊዮዔናይ፥ኢልያሴብ፥ሙታንያ፥ይሬሞት፥ዛባድ፥ዓዚዛ።

28ከቤባይ፡ልጆችም፤ይሆሐናን፥ሐናንያ፥ዘባይ፥ዐጥላይ።

29ከባኒ፡ልጆችም፤ሜሱላም፥መሉክ፥ዓዳያ፥ያሱብ፥ሸዓል፥ራሞት።

30ከፈሐት፡ሞዐብ፡ልጆችም፤ዓድና፥ክላል፥በናያስ፥መዕሴያ፥ሙታንያ፥ባስልኤል፥ቢንዊ፥ምናሴ።

31ከካሪም፡ልጆችም፤አልዓዛር፥ይሺያ፥መልክያ፥ሸማያ፥ስምዖን፥

32ብንያም፥መሉክ፥ሰማራያ።

33ከሐሱም፡ልጆችም፤መትናይ፥መተታ፥ዛባድ፥ኤሊፋላት፥ይሬማይ፥ምናሴ፥ሰሜኢ።

34ከባኒ፡ልጆችም፤መዕዳይ ፥ዓምራም ፥ኡኤል፥

35በናያስ፥ቤድያ፥ኬልቅያ፡

36ወንያ፥ሜሪሞት፥ኤልያሴብ፥

37መታንያ፥መትናይ፥የዕሱ፥

38ባኒ፥ቢንዊ፥ሰሜኢ፥

39ሰሌምያ፥ናታን፥ዓዳያ፥

40መክነድባይ፥ሴሴይ፥ሸራይ፥

41ዔዝርኤል፥ሰሌምያ፥ሰማራያ፥

42ሰሎም፥አማርያ፥ዮሴፍ።

43ከናባው፡ልጆችም፤ይዔኤል፥መቲትያ፥ዛባድ፥ዘቢና፥ያዳይ፥ኢዮኤል፥በናያስ።

44እነዚህ፡ዅሉ፡እንግዳዎቹን፡ሚስቶች፡አግብተው፡ነበር፤ከነዚህም፡ሚስቶች፡ዐያሌዎቹ፡ልጆችን፡ ወልደው፡ነበር፨ 235 ዕብ.፥መታንያህ፡(መባአ፡አምላክ፥ያምላክ፡ስጦታ፣መጥን)። 236 ዕብ.፥ይሒኤል፡(የሐዩ፡እግዚእ፥ጌታ፡ይኖራል)። 237 ዕብ.፥መዐዳይ፡(ምዕዳው•መሻገሪያ)። 238ዕብ.፥ዐምራም፡(ዐመ፡ራማ•የልዕልና፣የከፍታ፡ሕዝብ) http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source