Skip to content
← Ezra

Chapter 9 · Amharic

Ezra

1ይህም፡ከተፈጸመ፡በዃላ፡አለቃዎቹ፡ወደ፡እኔ፡ቀርበው፦የእስራኤል፡ሕዝብ፡ካህናቱም፡ሌዋውያኑም፡ እንደ፡ከነዓናውያን፡እንደ፡ኬጢያውያን፡እንደ፡ፌርዛውያን፡እንደ፡ኢያቡሳውያን፡እንደ፡አሞናውያን፡እንደ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ሞዐባውያን፡እንደ፡ግብጻውያንና፡እንደ፡አሞራውያን፡ርኵሰት፡ያደርጋሉ፡እንጂ፡ከምድር፡አሕዛብ፡አልተለዩም፤

2ለራሳቸውና፡ለልጆቻቸውም፡ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡ወስደዋል፥የተቀደሰውንም፡ዘር፡ከምድር፡አሕዛብ፡ጋራ፡ ደባልቀዋል፤አስቀድሞም፡አለቃዎቹና፡ሹማምቶቹ፡በዚህ፡መተላለፍ፡መዠመሪያ፡ኾነዋል፡አሉኝ።

3ይህንም፡ነገር፡በሰማኹ፡ጊዜ፡ልብሴንና፡መጐናጸፊያዬን፡ቀደድኹ፥የራሴንና፡የጢሜንም፡ጠጕር፡ ነጨኹ፥ደንግጬም፡ተቀመጥኹ።

4ስለምርኮኛዎቹም፡መተላለፍ፡የእስራኤልን፡አምላክ፡ቃል፡የሚፈሩ፡ዅሉ፡ወደ፡እኔ፡ተሰበሰቡ፤እኔም፡ እስከሠርክ፡መሥዋዕት፡ድረስ፡ደንግጬ፡ተቀመጥኹ።

5በሠርክም፡መሥዋዕት፡ጊዜ፡ልብሴና፡መጐናጸፊያዬ፡እንደ፡ተቀደደ፡ኾኖ፡ከመዋረዴ፡ ተነሣኹ፤በጕልበቴም፡ተንበርክኬ፡ወደ፡አምላኬ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እጄን፡ዘረጋኹ።

6እንዲህም፡አልኹ፦አምላኬ፡ሆይ፥ኀጢአታችን፡በራሳችን፡ላይ፡በዝቷልና፥በደላችንም፡ወደ፡ሰማይ፡ከፍ፡ ከፍ፡ብሏልና፥አምላኬ፡ሆይ፥ፊቴን፡ወዳንተ፡አነሣ፡ዘንድ፡ዐፍራለኹ፥እፈራማለኹ።

7ከአባቶቻችን፡ዘመን፡ዠምረን፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡እጅግ፡በድለናል፤ዛሬም፡እንደኾነው፡ስለ፡ኀጢአታችን፡ እኛና፡ንጉሦቻችን፡ካህናታችንም፡ለሰይፍና፡ለምርኮ፡ለብዝበዛና፡ለዕፍረት፡በምድር፡ነገሥታት፡እጅ፡ተጣልን።

8አኹንም፡ቅሬታ፡ይተውልን፡ዘንድ፥በተቀደሰውም፡ስፍራው፡ችንካርን፡ይሰጠን፡ዘንድ፥አምላካችንም፡ ዐይናችንን፡ያበራ፡ዘንድ፥በባርነትም፡ሳለን፡ጥቂት፡የሕይወት፡መታደስን፡ይሰጠን፡ዘንድ፡ለጥቂት፡ጊዜ፡ ከአምላካችን፡ከእግዚአብሔር፡ሞገስ፡ተሰጥቶናል።

9ባሪያዎች፡ነንና፥አምላካችን፡ግን፡በባርነታችን፡አልተወንም፤የሕይወት፡መታደስን፡ይሰጠን፡ ዘንድ፥የአምላካችንንም፡ቤት፡እንሠራ፡ዘንድ፥የተፈታውንም፡እንጠግን፡ዘንድ፥በይሁዳና፡በኢየሩሳሌምም፡ ቅጥር፡ይደረግልን፡ዘንድ፡በፋርስ፡ነገሥታት፡ፊት፡ምሕረቱን፡ሰጠን።

12አኹንስ፡አምላካችን፡ሆይ፦ትወርሷት፡ዘንድ፡የምትገቡባት፡ምድር፡በምድር፡አሕዛብ፡ርኵሰት፡ ረክሳለች፥ከዳር፡እስከ፡ዳርም፡ድረስ፡ከርኵሰታቸው፡ከጸያፍ፡ሥራቸውም፡ተሞልታለች፤አኹንም፡ትበረቱ፡ ዘንድ፥የምድሩንም፡ፍሬ፡ትበሉ፡ዘንድ፥ለዘለዓለም፡ለልጆቻችኹ፡ታወርሷት፡ዘንድ፡ሴቶች፡ልጆቻችኹን፡ ለልጆቻቸው፡አትስጡ፥ሴቶች፡ልጆቻቸውንም፡ለልጆቻችኹ፡አትውሰዱ፥ሰላማቸውንና፡ደኅንነታቸውንም፡ ለዘለዓለም፡አትሹ፡ብለኽ፡በባሪያዎችኽ፡በነቢያት፡ያዘዝኸውን፡ትእዛዝ፡ትተናልና፥ከዚህ፡በዃላ፡ምን፡ እንላለን፧

13ስለ፡ክፉ፡ሥራችንና፡ስለ፡ታላቁ፡በደላችን፡ካገኘን፡ነገር፡ዅሉ፡በዃላ፥አንተ፡አምላካችን፡እንደ፡ ኀጢአታችን፡ብዛት፡አልቀሠፍኸንም፥ነገር፡ግን፥ቅሬታን፡ሰጠኸን።

14በእውኑ፡ተመልሰን፡ትእዛዝኽን፡እናፈርስ፡ዘንድ፥ርኩስ፡ሥራን፡ከሚሠሩ፡ከነዚህም፡አሕዛብ፡ጋራ፡ እንገባ፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟ናልን፧አንተስ፡ቅሬታ፡የሌለንና፡የማናመልጥ፡እስክንኾን፡ድረስ፡እንድታጠፋን፡ አትቈጣንም፧

15አቤቱ፡የእስራኤል፡አምላክ፡ሆይ፥አንተ፡ጻድቅ፡ነኽ፤ዛሬም፡እንደኾነው፡እኛ፡አምልጠን፡ ቀርተናል፤እንሆ፥በፊትኽ፡በበደላችን፡አለን፤ስለዚህ፥በፊትኽ፡ሊቆም፡የሚችል፡የለም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source