Skip to content
← Ezra

Chapter 8 · Amharic

Ezra

1በንጉሡ፡በአርጤክስስ፡መንግሥት፡ከእኔ፡ጋራ፡ከባቢሎን፡የወጡ፡የአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡እነዚህ፡ ናቸው፡ትውልዳቸውም፡ይህ፡ነው፤

2ከፊንሐስ፡ልጆች፡ጌርሶን፥ከኢታምር፡ልጆች፡ዳንኤል፥ከዳዊት፡ልጆች፡ሐጡስ፥ከሴኬንያ፡ልጆች፥

3ከፋሮስ፡ልጆች፡ዘካርያስ፥ከርሱም፡ጋራ፡መቶ፡ዐምሳ፡ወንዶች፡በትውልድ፡ተቈጠሩ።

4ከፋሐት፡ሞዐብ፡ልጆች፡የዘራእያ፡ልጅ፡ኤሊሆዔናይ፥ከርሱም፡ጋራ፡ኹለት፡መቶ፡ወንዶች።

5ከሴኬንያ፡ልጆች፡የየሕዚኤል፡ልጅ፥ከርሱም፡ጋራ፡ሦስት፡መቶ፡ወንዶች።

6ከዓዲን፡ልጆች፡የዮናታን፡ልጅ፡ዔቤድ፥ከርሱም፡ጋራ፡ዐምሳ፡ወንዶች።

7ከዔላም፡ልጆች፡የጎቶልያ፡ልጅ፡የሻያ፥ከርሱም፡ጋራ፡ሰባ፡ወንዶች።

8የሰፋጥያስ፡ልጆች፡የሚካኤል፡ልጅ፡ዝባድያ፥ከርሱም፡ጋራ፡ሰማንያ፡ወንዶች።

9ከኢዮአብ፡ልጆች፡የይሒኤል፡ልጅ፡ዐብድዩ፥ከርሱም፡ጋራ፡ኹለት፡መቶ፡ዐሥራ፡ስምንት፡ወንዶች።

10ከሰሎሚት፡ልጆች፡የዮሲፍያ፡ልጅ፥ከርሱም፡ጋራ፡መቶ፡ስድሳ፡ወንዶች።

11ከቤባይ፡ልጆች፡የቤባይ፡ልጅ፡ዘካርያስ፥ከርሱም፡ጋራ፡ኻያ፡ስምንት፡ወንዶች።

12ከዓዝጋድ፡ልጆች፡የሃቃጣን፡ልጅ፡ዮሐናን፥ከርሱም፡ጋራ፡መቶ፡ዐሥር፡ወንዶች።

13ከዃለኛዎቹ፡ከአዶኒቃም፡ልጆች፡ስማቸው፡ይህ፡ነው፤ኤሊፋላት፥ይዑኤል፥ሸማያ፥ከነርሱም፡ጋራ፡ ስድሳ፡ወንዶች።

14ከበጉዋይ፡ልጆች፡ዑታይና፡ዘቡድ፥ከነርሱም፡ጋራ፡ሰባ፡ወንዶች።

15ወደ፡አህዋም፡ወደሚፈስ፟፡ወንዝ፡ሰበሰብዃቸው፥በዚያም፡ሦስት፡ቀን፡ሰፈርን፤ሕዝቡንና፡ካህናቱን፡ ስቈጥራቸው፡በዚያ፡ከሌዊ፡ልጆች፡ማንንም፡አላገኘኹም።

16ወደ፡አለቃዎቹም፡ወደ፡አልዓዛር፥ወደ፡አርኤል፥ወደ፡ሸማያ፥ወደ፡ኤልናታን፥ወደ፡ያሪብ፥ወደ፡ ኤልናታን፥ወደ፡ናታን፥ወደ፡ዘካርያስ፥ወደ፡ሜሱላም፥ደግሞም፡ወደ፡ዐዋቂዎቹ፡ወደ፡ዮያሪብና፡ወደ፡ ኤልናታን፡ላክኹ።

17በካሲፍያ፡ስፍራ፡ወደነበረው፡ወደ፡አለቃው፡ወደ፡አዶ፡ላክዃቸው፤ለአምላካችን፡ቤት፡አገልጋዮችን፡ ያመጡልን፡ዘንድ፡በካሲፍያ፡ስፍራ፡ለሚኖሩት፡ለአዶና፡ለወንድሞቹ፡ለናታኒም፡የሚነግሯቸውን፡በአፋቸው፡ አደረግኹ።

18በላያችንም፡መልካም፡በኾነው፡በአምላካችን፡እጅ፡ከእስራኤል፡ልጅ፡ከሌዊ፡ልጅ፡ከሞሖሊ፡ልጆች፡ ወገን፡የነበረውን፡አስተዋይ፡ሰው፡ሰራብያን፥ከርሱም፡ጋራ፡ዐሥራ፡ስምንቱን፡ልጆቹንና፡ወንድሞቹን፡ አመጡልን።

19ደግሞም፡ሐሸብያን፡ከርሱም፡ጋራ፡ከሜራሪ፡ልጆች፡ወገን፡የነበረውን፡የሻያንና፡ኻያውን፡ወንድሞቹንና፡ ልጆቻቸውን። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

20ሌዋውያንንም፡እንዲያገለግሉ፡ዳዊትና፡አለቃዎቹ፡ከሰጧቸው፡ናታኒም፡ውስጥ፡ኹለት፡መቶ፡ኻያ፡ ናታኒም፡አመጡ፤እነዚህም፡ዅሉ፡በስም፡በስማቸው፡ተጠሩ።

21በአምላካችን፡ፊት፡ራሳችንን፡እናዋርድ፡ዘንድ፥ከርሱም፡የቀናውን፡መንገድ፡ለእኛና፡ለልጆቻችን፡ ለንብረታችንም፡ዅሉ፡እንለምን፡ዘንድ፡በዚያ፡በአህዋ፡ወንዝ፡አጠገብ፡ጾም፡ዐወጅኹ።

22ንጉሡንም፦የአምላካችን፡እጅ፡በሚሹት፡ዅሉ፡ላይ፡ለመልካም፡ነው፤ኀይሉና፡ቍጣው፡ግን፡ርሱን፡ በሚተዉ፡ዅሉ፡ላይ፡ነው፡ብለን፡ተናግረን፡ነበርና፥በመንገድ፡ካለው፡ጠላት፡ያድኑን፡ዘንድ፥ጭፍራና፡ ፈረሰኛዎች፡ከንጉሡ፡እለምን፡ዘንድ፡ዐፍሬ፡ነበርና።

23ስለዚህም፡ነገር፡ጾምን፥ወደ፡እግዚአብሔርም፡ለመንን፤ርሱም፡ተለመነን።

24ከካህናቱም፡አለቃዎች፡ዐሥራ፡ኹለት፡ሰዎችን፥ሰራብያንና፡ሐሸቢያን፡ከነርሱም፡ጋራ፡ዐሥር፡ ወንድሞቻቸውን፡ለየኹ፤

25ንጉሡና፡አማካሪዎቹ፡አለቃዎቹም፡በዚያም፡የተገኙት፡እስራኤል፡ዅሉ፡ያቀረቡትን፡ለአምላካችን፡ቤት፡ የቀረበውን፡ብሩንና፡ወርቁን፡ዕቃውንም፡መዝኜ፡ሰጠዃቸው።

26ስድስት፡መቶ፡ዐምሳ፡መክሊት፡ብር፥አንድ፡መቶም፡መክሊት፡የብር፡ዕቃዎች፥አንድ፡መቶም፡ መክሊት፡ወርቅ፥

27ኻያም፡ባለሺሕ፡ዳሪክ፡የወርቅ፡ጽዋዎች፥ኹለትም፡እንደ፡ወርቅ፡የከበሩ፡ከጥሩ፡ከሚያንጸባርቅ፡ናስ፡ የተሠሩ፡ዕቃዎች፡መዝኜ፡በእጃቸው፡ሰጠኹ።

28እኔም፦እናንተ፡ለእግዚአብሔር፡ተቀድሳችዃል፥ዕቃዎቹም፡ቅዱስ፡ናቸው፤ብሩና፡ወርቁም፡ለአባቶቻችን፡ አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡በፈቃድ፡የቀረበ፡ነው፤

29በካህናትና፡በሌዋውያን፡አለቃዎች፡በእስራኤልም፡አባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ፊት፡በኢየሩሳሌም፡ በእግዚአብሔር፡ቤት፡ጓዳዎች፡ውስጥ፡እስክትመዝኑ፡ድረስ፡ተግታችኹ፡ጠብቁ፡አልዃቸው።

30ካህናቱና፡ሌዋውያኑም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ወደአምላካችን፡ቤት፡ይወስዱት፡ዘንድ፡ብሩንና፡ወርቁን፡ ዕቃዎቹንም፡በሚዛን፡ተቀበሉ።

31በመዠመሪያውም፡ወር፡በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ቀን፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡እንኼድ፡ዘንድ፡ከአህዋ፡ወንዝ፡ ተነሣን፡የአምላካችንም፡እጅ፡በላያችን፡ነበረ፥በመንገድም፡ከጠላትና፡ከሚሸምቅ፡ሰው፡እጅ፡አዳነን።

32ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ደረስን፥በዚያም፡ሦስት፡ቀን፡ተቀመጥን።

33በአራተኛውም፡ቀን፡ብሩና፡ወርቁ፡ዕቃዎቹም፡በአምላካችን፡ቤት፡በካህኑ፡በኦርዮ፡ልጅ፡በሜሪሞት፡እጅ፡ ተመዘኑ፤ከርሱም፡ጋራ፡የፊንሐስ፡ልጅ፡አልዓዛር፡ነበረ፡ከነርሱም፡ጋራ፡ሌዋውያን፡የኢያሱ፡ልጅ፡ዮዛባትና፡ የቢንዊ፡ልጅ፡ኖዓድያ፡ነበሩ።

34ዅሉም፡በቍጥርና፡በሚዛን፡ተመዘነ፤ሚዛኑም፡ዅሉ፡በዚያን፡ጊዜ፡ተጻፈ።

35ከምርኮም፡የወጡት፡ምርኮኛዎች፡ለእስራኤል፡አምላክ፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ስለ፡እስራኤል፡ዅሉ፡ ዐሥራ፡ኹለት፡ወይፈኖች፥ዘጠና፡ስድስትም፡አውራ፡በጎች፥ሰባ፡ሰባትም፡ጠቦቶች፥ለኀጢአት፡መሥዋዕት፡ ዐሥራ፡ኹለት፡አውራ፡ፍየሎች፡አቀረቡ።ይህ፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ነበረ።

36የንጉሡንም፡ትእዛዝ፡በወንዙ፡ማዶ፡ላሉት፡ለንጉሡ፡ሹማምቶችና፡ገዢዎች፡ሰጡ፤እነርሱም፡ሕዝቡንና፡ የእግዚአብሔርን፡ቤት፡አገዙ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source