1ከዚህም፡ነገር፡በዃላ፡በፋርስ፡ንጉሥ፡በአርጤክስስ፡መንግሥት፡ዕዝራ፡የሰራያ፡ልጅ፥
2የዐዛርያስ፡ልጅ፥የኬልቅያስ፡ልጅ፥የሰሎም፡ልጅ፥የሳዶቅ፡ልጅ፥የአኪጦብ፡ልጅ፥
3የአማርያ፡ልጅ፥የዐዛርያስ፡ልጅ፥የመራዮት፡ልጅ፥
4የዘራእያ፡ልጅ፥የዖዚ፡ልጅ፥የቡቂ፡ልጅ፥
5የአቢሱ፡ልጅ፥የፊንሐስ፡ልጅ፥የአልዓዛር፡ልጅ፥የታላቁ፡ካህን፡የአሮን፡ልጅ፥ይህ፡ዕዝራ፡ከባቢሎን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ወጣ፤
6የእስራኤልም፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡በሰጠው፡በሙሴ፡ሕግ፡ፈጣን፡ጸሓፊ፡ነበረ፤የአምላኩም፡ የእግዚአብሔር፡እጅ፡በርሱ፡ላይ፡ነበረችና፡ንጉሡ፡የሻውን፡ዅሉ፡ሰጠው።
7ከእስራኤልም፡ልጆች፡ከካህናቱም፡ከሌዋውያኑም፡ከመዘምራኑም፡ከበረኛዎቹም፡ከናታኒምም፡በንጉሡ፡ በአርጤክስስ፡በሰባተኛው፡ዓመት፡ዐያሌዎች፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ወጡ።
8በንጉሡም፡በሰባተኛው፡ዓመት፡በዐምስተኛው፡ወር፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ደረሰ።
9በመዠመሪያውም፡ወር፡በአንደኛው፡ቀን፡ከባቢሎን፡ሊወጣ፡ዠመረ፥መልካሚቱም፡የአምላኩ፡እጅ፡ በርሱ፡ላይ፡ነበረችና፡በዐምስተኛ፡ወር፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ደረሰ።
10ዕዝራም፡የእግዚአብሔርን፡ሕግ፡ይፈልግና፡ያደርግ፡ዘንድ፥ለእስራኤልም፡ሥርዐትንና፡ፍርድን፡ያስተምር፡ ዘንድ፡ልቡን፡አዘጋጅቶ፡ነበር።
11ንጉሡም፡አርጤክስስ፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ቃልና፡ለእስራኤል፡የኾነውን፡ሥርዐት፡ይጽፍ፡ለነበረው፡ ለጸሓፊው፡ለካህኑ፡ለዕዝራ፡የሰጠው፡የደብዳቤው፡ግልባጭ፡ይህ፡ነው።
12ከንጉሠ፡ነገሥት፡ከአርጤክስስ፡ለሰማይ፡አምላክ፡ሕግ፡ጸሓፊ፡ለካህኑ፡ለዕዝራ፥ሙሉ፡ሰላም፡ይኹን፤
13በመንግሥቴ፡ውስጥ፡ካሉ፡ከእስራኤል፡ሕዝብ፡ከካህናቱና፡ከሌዋውያኑም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ይኼድ፡ ዘንድ፡የሚወድ፟፡ዅሉ፡ከአንተ፡ጋራ፡እንዲኼድ፡አዝዣለኹ።
14በእጅኽ፡እንዳለችው፡እንደ፡አምላክኽ፡ሕግ፡ይሁዳንና፡ኢየሩሳሌምን፡ትጐበኝ፡ዘንድ፥
15ንጉሡንና፡አማካሪዎቹም፡መኖሪያው፡በኢየሩሳሌም፡ለኾነው፡ለእስራኤል፡አምላክ፡በፈቃዳቸው፡ያቀረቡትን፡ ብርና፡ወርቅ፥
16በባቢሎንም፡አውራጃ፡ዅሉ፡የምታገኘውን፡ብርና፡ወርቅ፡ዅሉ፥ሕዝቡና፡ካህናቱም፡በኢየሩሳሌም፡ላለው፡ ለአምላካቸው፡ቤት፡በፈቃዳቸው፡የሚያቀርቡትን፡ትወስድ፡ዘንድ፡በንጉሡና፡በሰባቱ፡አማካሪዎች፡ተልከኻልና፤
17ስለዚህ፥በዚህ፡ገንዘብ፡ወይፈኖችንና፡አውራ፡በጎችን፥ጠቦቶችንም፥የእኽላቸውንና፡የመጠጣቸውን፡ ቍርባን፡ተግተኽ፡ግዛ፤በኢየሩሳሌምም፡ባለው፡በአምላካችኹ፡ቤት፡መሠዊያ፡ላይ፡አቅርባቸው።
18ከቀረውም፡ብርና፡ወርቅ፡አንተና፡ወንድሞችኽ፡ለማድረግ፡ደስ፡የሚያሠኛችኹን፡ነገር፡እንደ፡ አምላካችኹ፡ፈቃድ፡አድርጉ።
19ስለአምላክኽም፡ቤት፡አገልግሎት፡የተሰጠኽን፡ዕቃ፡በኢየሩሳሌም፡አምላክ፡ፊት፡አሳልፈኽ፡ስጥ።
20ከዚህም፡በላይ፡ለማውጣት፡የሚያስፈልግኽን፡ለአምላክኽ፡ቤት፡የሚያሻውን፡ነገር፡ከንጉሡ፡ቤተ፡ መዛግብት፡አውጣ።
21እኔም፡ንጉሡ፡አርጤክስስ፡በወንዝ፡ማዶ፡ላሉት፡በጅሮንዶች፡ዅሉ፡ይህን፡ትእዛዝ፡ሰጥቻለኹ።የሰማይ፡ አምላክ፡ሕግ፡ጸሓፊ፡ካህኑ፡ዕዝራ፡ከእናንተ፡የሚፈልገውን፡ዅሉ፡አዘጋጁለት፤
22እስከ፡መቶ፡መክሊት፡ብርም፡ቢኾን፥እስከ፡መቶ፡የቈሬስ፡መስፈሪያ፡ስንዴ፥እስከ፡መቶም፡የባዶስ፡ መስፈሪያ፡የወይን፡ጠጅ፥እስከ፡መቶም፡የባዶስ፡መስፈሪያ፡ዘይት፡ቢኾን፥ጨውም፡ያለልክ፡ቢኾን፡ስጡ።
23በንጉሡና፡በልጆቹ፡መንግሥት፡ላይ፡ቍጣ፡እንዳይኾን፥የሰማይ፡አምላክ፡ያዘዘው፡ዅሉ፡ለሰማይ፡ አምላክ፡ቤት፡በሙሉ፡ይደረግ።
24ደግሞም፡በካህናቱና፡በሌዋውያን፡በመዘምራኑም፡በበረኛዎቹም፡በናታኒምም፡በዚህም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ በሚሠሩ፡አገልጋዮች፡ላይ፡ግብርና፡ቀረጥ፡መጥንም፡እንዳይጣል፡ብለን፡እናስታውቃችዃለን።
25አንተም፡ዕዝራ፥በእጅኽ፡እንዳለው፡እንደ፡አምላክኽ፡ጥበብ፡መጠን፡በወንዝ፡ማዶ፡ባሉ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ የአምላክኽን፡ሕግ፡በሚያውቁ፡ዅሉ፡ላይ፡ይፈርዱ፡ዘንድ፡ዳኛዎችንና፡ፈራጆች፡አስነሣ፤የማያውቁትንም፡ አስተምሯቸው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
26የአምላክኽንም፡ሕግ፥የንጉሡንም፡ሕግ፡በማያደርግ፡ዅሉ፡ላይ፡ሞት፡ወይም፡ስደት፡ወይም፡ገንዘብን፡ መወረስ፡ወይም፡ግዞት፡በፍጥነት፡ይፈረድበት።
28በኢየሩሳሌም፡ያለውን፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ያሳምር፡ዘንድ፡እንደዚህ፡ያለውን፡ነገር፡በንጉሡ፡ ልብ፡ያኖረ፥በንጉሡም፡በአማካሪዎቹም፡በንጉሡም፡ኀያላን፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ፊት፡ምሕረቱን፡ወደ፡እኔ፡ የላከ፡የአባቶቻችን፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ይባረክ።እኔም፡በላዬ፡ባለችው፡በአምላኬ፡በእግዚአብሔር፡እጅ፡ በረታኹ፤ከእኔም፡ጋራ፡እንዲወጡ፡ከእስራኤል፡ዘንድ፡አለቃዎችን፡ሰበሰብኹ።