Skip to content
← Ezra

Chapter 6 · Amharic

Ezra

1በዚያ፡ጊዜም፡ንጉሡ፡ዳርዮስ፡መዛግብት፡ባሉበት፡በባቢሎን፡ቤተ፡መጻሕፍት፡እንዲመረመር፡አዘዘ።

2በሜዶን፡አውራጃ፡ባለው፡አሕምታ፡በሚባል፡ከተማ፡በንጉሡ፡ቤት፡ውስጥ፡አንድ፡ጥቅል፟፡ ተገኘ፥በውስጡም፡ይህ፡ነገር፡ለመታሰቢያ፡ተጽፎ፡ነበር።

3በንጉሡ፡በቂሮስ፡በመዠመሪያው፡ዓመት፡ንጉሡ፡ቂሮስ፡እንዲህ፡ብሎ፡አዘዘ፤በኢየሩሳሌም፡ያለው፡ የእግዚአብሔር፡ቤት፥መሥዋዕት፡የሚቀርብበት፡ቦታ፥ይህ፡ቤት፡ይሠራ፥በጽኑም፡ይመሥረት፤ቁመቱ፡ስድሳ፡ ክንድ፡ወርዱም፡ስድሳ፡ክንድ፡ይኹን።

4በሦስት፡ተራ፡ታላላቅ፡ድንጋይ፥ባንድ፡ተራ፡ዕንጨት፡ይደረግ፤ውጪውም፡ከንጉሡ፡ቤት፡ይሰጥ።

5ናቡከደነጾርም፡በኢየሩሳሌም፡ካለው፡መቅደስ፡ወስዶ፡ወደ፡ባቢሎን፡ያመጣው፡የእግዚአብሔር፡ቤት፡ የወርቅና፡የብር፡ዕቃ፡ይመለስ፤በኢየሩሳሌምም፡ወዳለው፡መቅደስ፡ወደ፡ስፍራው፡ይወሰድ፥በእግዚአብሔር፡ ቤት፡ይኑር።

6አኹንም፡አንተ፡በወንዝ፡ማዶ፡ያለኸው፡የአገሩ፡ገዢ፡ተንትናይ፡ደግሞ፡ሰተርቡዝናይ፡በወንዝ፡ማዶም፡ ያሉ፡ተባባሪዎቻችኹ፡አፈርሥካውያን፥ከዚያ፡ራቁ፤

7ይህም፡የእግዚአብሔር፡ቤት፡ይሠራ፡ዘንድ፡ተዉ፤የአይሁድም፡አለቃና፡የአይሁድም፡ሽማግሌዎች፡ይህን፡ የእግዚአብሔርን፡ቤት፡በስፍራው፡ይሠሩ፡ዘንድ፡ተዉአቸው።

8ይህን፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ይሠሩ፡ዘንድ፡ለአይሁድ፡ሽማግሌዎች፡የምታደርጉትን፥በወንዝ፡ማዶ፡ ካለው፡አገር፡ከሚመጣው፡ግብር፡ከንጉሡ፡ገንዘብ፡ለእነዚህ፡ሰዎች፡ወጪውን፡በትጋት፡እንድትሰጧቸው፡ ሥራም፡እንዳታስፈቷቸው፡አዝዣለኹ።

9ለሰማይ፡አምላክ፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡የሚያስፈልገውን፥ወይፈኖችና፡አውራ፡በጎች፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ጠቦቶችም፥በኢየሩሳሌምም፡እንዳሉ፡እንደ፡ካህናቱ፡ቃል፡ስንዴና፡ጨው፡የወይን፡ጠጅና፡ዘይት፡ዕለት፡ዕለት፡ ያለማቋረጥ፡ስጧቸው።

10ይኸውም፡ለሰማይ፡አምላክ፡ጣፋጭ፡ሽቱ፡የኾነውን፡መሥዋዕት፡ያቀረቡ፡ዘንድ፡ለንጉሡና፡ለልጆቹም፡ ዕድሜ፡ይጸልዩ፡ዘንድ፡ነው።

11ይህንም፡ትእዛዝ፡የሚለውጥ፡ዅሉ፥ምሰሶው፡ከቤቱ፡ተነቅሎ፡ርሱ፡ይሰቀልበት፤ቤቱም፡የጕድፍ፡መጣያ፡ ይደረግ፡ብዬ፡አዝዣለኹ።

12ስሙንም፡በዚያ፡ያኖረው፡አምላክ፡ይህን፡ይለውጡ፡ዘንድ፡በኢየሩሳሌም፡ያለውንም፡የእግዚአብሔርን፡ ቤት፡ያፈርሱት፡ዘንድ፡እጃቸውን፡የሚዘረጉትን፡ነገሥታትና፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ያጥፋ።እኔ፡ዳርዮስ፡ይህን፡ አዝዣለኹ፤በትጋት፡ይፈጸም።

13ንጉሡም፡ዳርዮስ፡እንደ፡ላከው፡ቃል፥በዚያን፡ጊዜ፡በወንዝ፡ማዶ፡ያለ፡ገዢ፡ተንትናይ፡ደግሞ፡ ሰተርቡዝናይ፡ተባባሪዎቻቸውም፡እንዲሁ፡ተግተው፡አደረጉ።

14የአይሁድም፡ሽማግሌዎች፡በነቢዩ፡በሐጌና፡በአዶ፡ልጅ፡በዘካርያስ፡ትንቢት፡ሠሩ፡ ተከናወነላቸውም።እንደ፡እስራኤልም፡አምላክ፡ትእዛዝ፥እንደ፡ፋርስም፡ነገሥታት፡እንደ፡ቂሮስና፡እንደ፡ ዳርዮስ፡እንደ፡አርጤክስስም፡ትእዛዝ፡ሠርተው፡ፈጸሙ።

15ይህም፡ቤት፡በንጉሡ፡በዳርዮስ፡መንግሥት፡በስድስተኛው፡ዓመት፡አዳር፡በሚባል፡ወር፡በሦስተኛው፡ ቀን፡ተፈጸመ።

16የእስራኤልም፡ልጆች፥ካህናትና፡ሌዋውያን፡የቀሩትም፡ምርኮኛዎች፥የዚህን፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ቅዳሴ፡ በደስታ፡አደረጉ።

17በዚህም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ቅዳሴ፡መቶ፡ወይፈኖችና፡ኹለት፡መቶ፡አውራ፡በጎች፡አራት፡መቶም፡ ጠቦቶች፡አቀረቡ፡፤ስለኀጢአትም፡መሥዋዕት፡እንደ፡እስራኤል፡ነገዶች፡ቍጥር፡ለእስራኤል፡ዅሉ፡ዐሥራ፡ ኹለት፡አውራ፡ፍየሎች፡አቀረቡ።

18በሙሴም፡መጽሐፍ፡እንደተጻፈው፡በኢየሩሳሌም፡ባለው፡በእግዚአብሔር፡አገልግሎት፡ላይ፡ካህናቱን፡ በየማዕርጋቸው፡ሌዋውያኑም፡በየክፍላቸው፡አቆሙ።

19ምርኮኛዎቹም፡በመዠመሪያው፡ወር፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ቀን፡ፋሲካውን፡አደረጉ።

20ካህናቱና፡ሌዋውያኑም፡አንድ፡ኾነው፡ነጽተው፡ነበር፤ዅሉም፡ንጹሓን፡ነበሩ፤ለምርኮኛዎቹም፡ ዅሉ፥ለወንድሞቻቸውም፡ለካህናቱ፥ለራሳቸውም፡ፋሲካውን፡ዐረዱ።

21ከምርኮም፡ተመልሰው፡የመጡት፡የእስራኤል፡ልጆች፥የእስራኤልንም፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ይፈልጉ፡ ዘንድ፡ራሳቸውን፡ከምድር፡አሕዛብ፡ርኵሰት፡ለይተው፡ወደ፡እነርሱ፡መጥተው፡የነበሩት፡ዅሉ፡በሉ፤

22እግዚአብሔር፡ደስ፡አሠኝቷቸዋልና፥የእስራኤልንም፡አምላክ፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ለመሥራት፡ እጃቸውን፡ያጸና፡ዘንድ፡የአሶርን፡ንጉሥ፡ልብ፡ወደ፡እነርሱ፡መልሷልና፥የቂጣውን፡በዓል፡ሰባት፡ቀን፡ በደስታ፡አደረጉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source