Skip to content
← Ezra

Chapter 5 · Amharic

Ezra

1ነቢያቱም፡ሐጌና፡የአዶ፡ልጅ፡ዘካርያስ፡በይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡ለነበሩ፡አይሁድ፡በእስራኤል፡አምላክ፡ ስም፡ትንቢት፡ተናገሩላቸው።

2በዚያን፡ጊዜ፡የሰላትያል፡ልጅ፡ዘሩባቤል፡የኢዮሴዴቅም፡ልጅ፡ኢያሱ፡ተነሥተው፡በኢየሩሳሌም፡ያለውን፡ የእግዚአብሔርን፡ቤት፡መሥራት፡ዠመሩ፤የሚያግዟቸውም፡የእግዚአብሔር፡ነቢያት፡ከነርሱ፡ጋራ፡ነበሩ።

3በዚያም፡ዘመን፡በወንዝ፡ማዶ፡የነበረው፡ገዢ፡ተንትናይ፥ደግሞ፡ሰተርቡዝናይ፥ተባባሪዎቻቸውም፡ወደ፡ እነርሱ፡መጥተው፦ይህን፡ቤት፡ትሠሩ፡ዘንድ፥ይህንኑም፡ቅጥር፡ታድሱ፡ዘንድ፡ያዘዛችኹ፡ማን፡ ነው፧አሏቸው።

4ደግሞም፦ይህንስ፡ሥራ፡የሚሠሩት፡ሰዎች፡ስም፡ማን፡ነው፧ብለው፡ጠየቋቸው።

5የአምላካቸው፡ዐይን፡ግን፡በአይሁድ፡ሽማግሌዎች፡ላይ፡ነበረ፥ይህም፡ነገር፡ወደ፡ዳርዮስ፡እስኪደርስ፡ ድረስ፥መልሱም፡በደብዳቤ፡እስኪመጣ፡ድረስ፡አልከለከሏቸውም።

6በወንዙ፡ማዶ፡የነበረው፡ገዢ፡ተንትናይ፡ደግሞ፡ሰተርቡዝናይ፡ተባባሪዎቹም፡በወንዙ፡ማዶ፡የነበሩት፡ አፈርሥካውያን፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ዳርዮስ፡የላኩት፡የደብዳቤው፡ግልባጭ፡ይህ፡ነበረ።

7እንዲህም፡የሚል፡ደብዳቤ፡ላኩለት፦ለንጉሡ፡ለዳርዮስ፡ሙሉ፡ሰላም፡ይኹን፤

8ወደይሁዳ፡አገር፡ወደታላቁም፡አምላክ፡ቤት፡እንደ፡ኼድን፡ንጉሡ፡ይወቅ፤ርሱም፡በትልቅ፡ድንጋይ፡ ተሠራ፥በቅጥሩም፡ውስጥ፡ዕንጨት፡ተደረገ፥ያም፡ሥራ፡በትጋት፡ይሠራል፥በእጃቸውም፡ይከናወናል።

9እነዚያንም፡ሽማግሌዎች፦ይህን፡ቤት፡ትሠሩ፡ዘንድ፥ይህንስ፡ቅጥር፡ታድሱ፡ዘንድ፡ያዘዛችኹ፡ማን፡ ነው፧ብለን፡ጠየቅናቸው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

10ደግሞም፡እናስታውቅኽ፡ዘንድ፥በእነርሱም፡ያሉትን፡ሹሞች፡ስም፡እንጽፍልኽ፡ዘንድ፡ስማቸውን፡ ጠየቅን።

11እንደዚህም፡ብለው፡መለሱልን፦እኛ፡የሰማይና፡የምድር፡አምላክ፡ባሪያዎች፡ነን፥ከብዙም፡ዘመን፡ ዠምሮ፡ተሠርቶ፡የነበረውን፥ታላቁም፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡ሠርቶ፡የፈጸመውን፡ቤት፡እንሠራለን።

12አባቶቻችንም፡የሰማይን፡አምላክ፡ካስቈጡ፡በዃላ፡በከለዳዊው፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡በናቡከደነጾር፡እጅ፡ አሳልፎ፡ሰጣቸው፥ርሱም፡ይህን፡ቤት፡አፈረሰ፥ሕዝቡንም፡ወደ፡ባቢሎን፡አፈለሰ።

13ነገር፡ግን፥በባቢሎን፡ንጉሥ፡በቂሮስ፡በመዠመሪያው፡ዓመት፡ንጉሡ፡ቂሮስ፡ይህን፡የእግዚአብሔርን፡ ቤት፡ይሠሩ፡ዘንድ፡አዘዘ።

14ናቡከደነጾርም፡በኢየሩሳሌም፡ከነበረው፡መቅደስ፡የወሰደውን፥ወደባቢሎንም፡መቅደስ፡ያፈለሰውን፡ የእግዚአብሔርን፡ቤት፡የወርቅንና፡የብርን፡ዕቃ፡ንጉሡ፡ቂሮስ፡ከባቢሎን፡መቅደስ፡አውጥቶ፡ሰሳብሳር፡ ለተባለው፡ለሹሙ፡ሰጠውና፦

15ይህን፡ዕቃ፡ይዘኽ፡ኺድ፥በኢየሩሳሌምም፡ባለው፡መቅደስ፡አኑረው፤የእግዚአብሔርም፡ቤት፡በስፍራው፡ ይሠራ፡አለው።

16በዚያ፡ጊዜም፡ይህ፡ሰሳብሳር፡መጣ፥በኢየሩሳሌምም፡ያለውን፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡መሠረተ፤ከዚያም፡ ጊዜ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡እየተሠራ፡አልተጨረሰም።

17አኹንም፡ይህ፡ነገር፡በንጉሡ፡ዐይን፡መልካም፡ቢኾን፡ይህ፡የእግዚአብሔር፡ቤት፡በኢየሩሳሌም፡ይሠራ፡ ዘንድ፡ከንጉሡ፡ከቂሮስ፡ታዞ፟፡እንደ፡ኾነ፡በባቢሎን፡ባለው፡በንጉሡ፡ቤተ፡መዛግብት፡ ይመርመር፤ስለዚህም፡ነገር፡ንጉሡ፡ፈቃዱን፡ይላክልን።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source