Skip to content
← Ezra

Chapter 4 · Amharic

Ezra

1የይሁዳና፡የብንያምም፡ጠላቶች፡ምርኮኛዎቹ፡ለእስራኤል፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡መቅደስ፡እንደ፡ሠሩ፡ ሰሙ።

2ወደ፡ዘሩባቤልና፡ወዳባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ቀርበው፦የአሶር፡ንጉሥ፡አስራዶን፡ወደዚህ፡ካመጣን፡ ቀን፡ዠምሮ፡ለአምላካችኹ፡እንሠዋለንና፥እንደናንተም፡እንፈልገዋለንና፡ከእናንተ፡ጋራ፡እንሥራ፡አሏቸው።

3ዘሩባቤልና፡ኢያሱም፡የቀሩትም፡የእስራኤል፡አባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፦የአምላካችንን፡ቤት፡መሥራት፡ ለእኛና፡ለእናንተ፡አይደለም፤እኛ፡ለብቻችን፡ግን፡የፋርስ፡ንጉሥ፡ቂሮስ፡እንዳዘዘን፡ለእስራኤል፡አምላክ፡ ለእግዚአብሔር፡ቤት፡እንሠራለን፡አሏቸው።

4የምድሩም፡ሕዝብ፡የይሁዳን፡ሕዝብ፡እጅ፡ያደክሙ፡ነበር፥እንዳይሠሩም፡አስፈራሯቸው፥

5ምክራቸውንም፡ያፈርሱ፡ዘንድ፡በፋርሱ፡ንጉሥ፡በቂሮስ፡ዘመን፡ዅሉ፡እስከፋርስ፡ንጉሥ፡እስከዳርዮስ፡ መንግሥት፡ድረስ፡መካሪዎችን፡ገዙባቸው።

6በአርጤክስስ ም፡መንግሥት፥በመንግሥቱም፡በመዠመሪያ፡ዘመን፥በይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡በሚኖሩት፡ ላይ፡የክስ፡ነገር፡ጻፉ።

7በአርጤክስስ፡ዘመን፡ቢሽላም፥ሚትሪዳጡ፥ጣብኤል፡ተባባሪዎቹም፡ለፋርስ፡ንጉሥ፡ለአርጤክስስ፡ ጻፉ፤ደብዳቤውም፡በሶርያ፡ፊደልና፡በሶርያ፡ቋንቋ፡ተጽፎ፡ነበር።

8አዛዡ፡ሬሁም፡ጸሓፊውም፡ሲምሳይ፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡ለንጉሡ፡ለአርጤክስስ፡እንዲህ፡የሚል፡ደብዳቤ፡ ጻፉ።

9አዛዡ፡ሬሁም፥ጸሓፊውም፡ሲምሳይ፥የቀሩትም፡ ተባባሪዎቻቸው፥ዲናውያን፣አፈርሣትካውያን፣ጠርፈላውያን፣አፈርሣውያን፣አርካውያን፣ባቢሎናውያን፣ሱስናካው ያን፣ዴሐውያን፣ኤላማውያን፥

10ታላቁና፡ኀይለኛው፡አስናፈር፡ያፈለሳቸው፡በሰማርያና፡በወንዝ፡ማዶ፡ያኖራቸው፡የቀሩትም፡አሕዛብ፡ ደብዳቤውን፡ጻፉ።

11ለንጉሡ፡ለአርጤክስስ፡የላኩት፡የደብዳቤ፡ግልባጭ፡ይህ፡ነው፦በወንዝ፡ማዶ፡ያሉት፡ሰዎች፡ ባሪያዎችኽ፤

12አኹንም፡ከአንተ፡ዘንድ፡የወጡ፡አይሁድ፡ወደ፡እኛ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡እንደ፡መጡ፡ንጉሡ፡ ይወቅ፤ዐመፀኛዪቱንና፡እጅግም፡የከፋቺቱን፡ከተማ፡ይሠራሉ፥ቅጥሯንም፡ያድሳሉ፥መሠረቷንም፡ጠገኑ።

13አኹንም፡ይህች፡ከተማ፡የተሠራች፡እንደ፡ኾነ፥ቅጥሯም፡የታደሰ፡እንደ፡ኾነ፥ግብርና፡ቀረጥ፡መጥንም፡ እንዳይሰጡ፥የንጉሡም፡ግቢው፡እንዲጐድል፡ንጉሡ፡ይወቅ።

14የንጉሡንም፡ጨው፡እንበላለንና፥ንጉሡንም፡ሲያቃልሉት፡ማየት፡አይገ፟ባ፟ንምና፡ስለዚህ፡ልከን፡ለንጉሡ፡ አስታውቀናል፤

15በአባቶችኽ፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ምርመራ፡ይደረግ፤በዚያም፡በታሪክ፡መጽሐፍ፡ይህች፡ከተማ፡ዐመፀኛ፡ 234ዕብ.፥አሐሽቬሮሽ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እንደ፡ኾነች፥ነገሥታትንና፡አውራጃዎችንም፡እንደ፡ጐዳች፥ከጥንቱም፡ሽፍትነት፡በርሷ፡እንደ፡ተዠመረ፡ ታገኛለኽ፥ታውቃለኽም፤ስለዚህም፡ይህች፡ከተማ፡ፈርሳ፡ነበር።

16ይህችም፡ከተማ፡የተሠራች፡እንደ፡ኾነ፥ቅጥሯም፡የታደሰ፡እንደ፡ኾነ፥በወንዝ፡ማዶ፡ክፍል፡እንደሌለኽ፡ ለንጉሡ፡እናስታውቃለን።

17ንጉሡም፡ለአዛዡ፡ለሬሁም፥ለጸሓፊውም፡ለሲምሳይ፥በሰማርያና፡በወንዝ፡ማዶም፡ለተቀመጡ፡ለቀሩት፡ ተባባሪዎቻቸው፡እንዲህ፡የሚለውን፡መልስ፡ላከ፦

18ሰላም፤አኹንም፡ወደ፡እኛ፡የላካችኹት፡ደብዳቤ፡በፊቴ፡ተተርጕሞ፡ተነበበ።

19እኔም፡አዝዣለኹ፥ተመረመረም፤ይህችም፡ከተማ፡ከጥንት፡ዠምራ፡በነገሥታት፡ላይ፡ዐመፀኛ፡እንደ፡ ነበረች፥በርሷም፡ዐመፅና፡ሽፍትነት፡እንደ፡ተደረገ፡ተገኘ።

20በኢየሩሳሌምም፡እጅግ፡ኀያላን፡ነገሥታት፡ነበሩ፥በወንዝም፡ማዶ፡ያለውን፡አገር፡ዅሉ፡ይገዙ፡ ነበር፤ግብርንና፡ቀረጥን፡መጥንንም፡ይቀበሉ፡ነበር።

21አኹንም፡እነዚህ፡ሰዎች፡ሥራውን፡እንዲተዉ፥እኔም፡እስካዝ፟፡ድረስ፡ይህች፡ከተማ፡እንዳትሠራ፡ ትእዛዝ፡ስጡ።

22ቸልም፡እንዳትሉ፡ተጠንቀቁ፤ለነገሥታቱ፡ጕዳትና፡ጥፋት፡እየበዛ፡ስለ፡ምን፡ይኼዳል፧

23የንጉሡም፡የአርጤክስስ፡ደብዳቤ፡ግልባጭ፡በሬሁምና፡በጸሓፊው፡በሲምሳይ፡በተባባሪዎቻቸውም፡ፊት፡ በተነበበ፡ጊዜ፥ፈጥነው፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ወደ፡አይሁድ፡ኼዱ፤በግድና፡በኀይልም፡አስተዉአቸው።

24በዚያን፡ጊዜም፡በኢየሩሳሌም፡ያለው፡የእግዚአብሔር፡ቤት፡ሥራ፡ቀረ፤እስከፋርስም፡ንጉሥ፡እስከዳርዮስ፡ መንግሥት፡እስከ፡ኹለተኛው፡ዓመት፡ድረስ፡ተጓጐለ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source