Skip to content
← Habakkuk

Chapter 3 · Amharic

Habakkuk

1የነቢዩ፡የዕንባቆም፡ጸሎት፡በመዝሙር።

2አቤቱ፥ዝናኽን፡ሰምቼ፡ፈራኹ፤አቤቱ፥በዓመታት፡መካከል፡ሥራኽን፡ፈጽም፤በዓመታት፡መካከል፡ ትታወቅ፤በመዓት፡ጊዜ፡ምሕረትን፡ዐስብ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

3እግዚአብሔር፡ከቴማን፥ቅዱሱም፡ከፋራን፡ተራራ፡ይመጣል።ክብሩ፡ሰማያትን፡ከድኗል፥ምስጋናውም፡ ምድርን፡ሞልቷል።

4ጸዳሉም፡እንደ፡ብርሃን፡ነው፤ጨረር፡ከእጁ፡ወጥቷል፤ኀይሉም፡በዚያ፡ተሰውሯል።

5ቸነፈር፡በፊቱ፡ይኼዳል፥የእሳትም፡ነበልባል፡ከእግሩ፡ይወጣል።

6ቆመ፥ምድርንም፡አወካት፤ተመለከተ፥አሕዛብንም፡አናወጠ፤የዘለዓለምም፡ተራራዎች፡ ተቀጠቀጡ፥የዘለዓለምም፡ኰረብታዎች፡ቀለጡ፤መንገዱ፡ከዘለዓለም፡ነው።

7የኢትዮጵያ፡ድንኳኖች፡ሲጨነቁ፡አየኹ፤የምድያም፡አገር፡መጋረጃዎች፡ተንቀጠቀጡ።

8በእውኑ፡እግዚአብሔር፡በወንዞች፡ላይ፡ተቈጥቷልን፧ቍጣኽ፡በወንዞች፡ላይ፥መዓትኽም፡በባሕር፡ላይ፡ ነውን፧በፈረሶችኽና፡በማዳንኽ፡ሠረገላዎች፡ላይ፡ተቀምጠኻልና።

9በቃልኽ፡እንደ፡ማልኽ፡መቅሠፍትኽን፡አወጣኽ፤ቀስትኽንም፡ገተርኽ፤ምድርን፡ሰንጥቀኽ፡ፈሳሾችን፡ አወጣኽ።

10ተራራዎች፡አንተን፡አይተው፡ተጨነቁ፤የውሃ፡ሞገድ፡ዐልፏል፤ቀላዩም፡ድምፁን፡ሰጥቷል፥እጁንም፡ ወደ፡ላይ፡አንሥቷል።

11ፍላጻዎችኽ፡ከወጡበት፡ብርሃን፡የተነሣ፥ከሚንቦገቦገውም፡ከጦርኽ፡ጸዳል፡የተነሣ፥ፀሓይና፡ጨረቃ፡ በመኖሪያቸው፡ቆሙ።

12በምድር፡ላይ፡በመዓት፡ተራመድኽ፤አሕዛብን፡በቍጣ፡አኼድኻቸው።

13ሕዝብኽን፡ለመታደግ፥የቀባኸውንም፡ለማዳን፡ወጣኽ፤የኀጢአተኛውን፡ቤት፡ራስ፡ ቀጠቀጥኽ፤መሠረቱን፡እስከ፡ዐንገቱ፡ድረስ፡ገለጥኽ።

14የአለቃዎችን፡ራስ፡በገዛ፡በትራቸው፡ወጋኽ፤እኔን፡ይበትኑ፡ዘንድ፡እንደ፡ዐውሎ፡ነፋስ፡ መጡ፤ችግረኛውን፡በስውር፡ለመዋጥ፡ደስታቸው፡ነው።

15ፈረሶችኽን፡በባሕር፥በብዙ፡ውሃዎችም፡ላይ፡አስረገጥኽ።

16እኔ፡ሰምቻለኹ፥ልቤም፡ደነገጠብኝ፤ከድምፁ፡የተነሣ፡ከንፈሮቼ፡ተንቀጠቀጡ፤መንቀጥቀጥ፡ወደ፡ ዐጥንቶቼ፡ውስጥ፡ገባ፤በስፍራዬ፡ኾኜ፡ተናወጥኹ፤በሚያስጨንቁን፡ሕዝብ፡ላይ፡እስኪመጣ፡ድረስ፡ የመከራን፡ቀን፡ዝም፡ብዬ፡እጠብቃለኹ።

17ምንም፡እንኳ፡በለስም፡ባታፈራ፥በወይንም፡ሐረግ፡ፍሬ፡ባይገኝ፥የወይራ፡ሥራ፡ቢጐድል፥ዕርሾችም፡ መብልን፡ባይሰጡ፥በጎች፡ከበረቱ፡ቢጠፉ፥ላሞችም፡በጋጡ፡ውስጥ፡ባይገኙ፥

18እኔ፡ግን፡በእግዚአብሔር፡ደስ፡ይለኛል፤በመድኀኒቴ፡አምላክ፡ሐሤት፡አደርጋለኹ።

19ጌታ፡እግዚአብሔር፡ኀይሌ፡ነው፤እግሮቼን፡እንደ፡ዋላ፡እግሮች፡ያደርጋል፤በከፍታዎችም፡ላይ፡ ያስኼደኛል፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source