1በንጉሡ፡በዳርዮስ፡በኹለተኛው፡ዓመት፡በስድስተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ የእግዚአብሔር፡ቃል፡በነቢዩ፡በሐጌ፡እጅ፡ወደይሁዳ፡አለቃ፡ወደሰላትያል፡ልጅ፡ወደ፡ዘሩባቤል፥ወደ፡ ታላቁም፡ካህን፡ወደኢዮሴዴቅ፡ልጅ፡ወደ፡ኢያሱ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፦ይህ፡ሕዝብ፦ዘመኑ፡አልደረሰም፥የእግዚአብሔር፡ቤት፡የሚሠራበት፡ ዘመን፡አልደረሰም፡ይላል፡ብሎ፡ተናገረ።
3የእግዚአብሔርም፡ቃል፡በነቢዩ፡በሐጌ፡እጅ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
4በእውኑ፡ይህ፡ቤት፡ፈርሶ፡ሳለ፡እናንተ፡ራሳችኹ፡በተሸለሙ፡ቤቶቻችኹ፡ለመኖር፡ጊዜው፡ነውን፧
5አኹንም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ልባችኹን፡በመንገዳችኹ፡ላይ፡አድርጉ።
6ብዙ፡ዘራችኹ፥ጥቂትም፡አገባችኹ፤በላችኹ፥ነገር፡ግን፥አልጠገባችኹም፤ጠጣችኹ፥ነገር፡ ግን፥አልረካችኹም፤ለበሳችኹ፥ነገር፡ግን፥አልሞቃችኹም፤ደመ፡ወዙን፡የተቀበለ፡ሰው፡በቀዳዳ፡ከረጢት፡ ያደርገው፡ዘንድ፡ደመ፡ወዙን፡ተቀበለ።
7የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ልባችኹን፡በመንገዳችኹ፡ላይ፡አድርጉ።
8ወደ፡ተራራው፡ውጡ፥ዕንጨትንም፡አምጡ፥ቤቱንም፡ሥሩ፤እኔም፡በርሱ፡ደስ፡ይለኛል፥እኔም፡ እመሰገናለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
9እናንተ፡ብዙ፡ነገርን፡ተስፋ፡አደረጋችኹ፥እንሆም፥ጥቂት፡ኾነ፤ወደ፡ቤትም፡ባገባችኹት፡ጊዜ፡እፍ፡ አልኹበት፦ይህ፡ስለ፡ምንድር፡ነው፧ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፦እናንተ፡ዅሉ፡ወደ፡ እየቤታችኹ፡እየሮጣችኹ፡የእኔ፡ቤት፡ፈርሶ፡ስለ፡ተቀመጠ፡ነው።
10ስለዚህ፥ሰማያት፡በላያችኹ፡ጠልን፡ከልክለዋል፥ምድሪቱም፡ፍሬዋን፡ከልክላለች።
11እኔም፡በምድርና፡በተራራዎች፥በእኽልና፡በወይንም፥በዘይትና፡ምድርም፡በምታበቅለው፡ላይ፥በሰዎችና፡ በእንስሳዎችም፡ላይ፥እጅም፡በሚደክምበት፡ዅሉ፡ላይ፡ድርቅን፡ጠርቻለኹ።
12የሰላትያልም፡ልጅ፡ዘሩባቤል፥ታላቁም፡ካህን፡የኢዮሴዴቅ፡ልጅ፡ኢያሱ፥የቀሩትም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ የአምላካቸውን፡የእግዚአብሔርን፡ድምፅ፡የነቢዩንም፡የሐጌን፡ቃል፥አምላካቸው፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ላከው፡ ዅሉ፡ሰሙ፤ሕዝቡም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ፈሩ።
13የእግዚአብሔርም፡መልእክተኛ፡ሐጌ፡በእግዚአብሔር፡መልእክት፡ሕዝቡን፦እኔ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ ነኝ፥ይላል፡እግዚአብሔር፡ብሎ፡ተናገረ።
15እግዚአብሔርም፡የይሁዳን፡አለቃ፡የሰላትያልን፡ልጅ፡የዘሩባቤልን፡መንፈስ፥የታላቁንም፡ካህን፡ የኢዮሴዴቅን፡ልጅ፡የኢያሱን፡መንፈስ፥የቀሩትንም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡መንፈስ፡አስነሣ፤በንጉሡም፡በዳርዮስ፡ በኹለተኛው፡ዓመት፡በስድስተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በኻያ፡አራተኛው፡ቀን፡መጡ፥የአምላካቸውንም፡ የሰራዊትን፡ጌታ፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ሠሩ።