Skip to content
← Haggai

Chapter 2 · Amharic

Haggai

1በሰባተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በኻያ፡አንደኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡በነቢዩ፡በሐጌ፡እጅ፡እንዲህ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ሲል፡መጣ፦

2ለይሁዳ፡አለቃ፡ለሰላትያል፡ልጅ፡ለዘሩባቤል፥ለታላቁም፡ካህን፡ለኢዮሴዴቅ፡ልጅ፡ለኢያሱ፥ለቀሩትም፡ ሕዝብ፡እንዲህ፡ስትል፡ተናገር።

3በቀድሞ፡ክብሩ፡ሳለ፡ይህን፡ቤት፡ያየ፡በእናንተ፡መካከል፡የቀረ፡ማን፡ነው፧ዛሬስ፡እንዴት፡ኾኖ፡ አያችኹት፧በዐይናችኹ፡እንደ፡ምናምን፡አይደለምን፧

4አኹን፡ግን፥ዘሩባቤል፡ሆይ፥በርታ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ታላቁም፡ካህን፡የኢዮሴዴቅ፡ልጅ፡ኢያሱ፡ ሆይ፥በርታ፥እናንተም፡የአገሩ፡ሕዝብ፡ሆይ፥በርቱና፡ሥሩ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤እኔ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ ነኝና፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

5መንፈሴም፡በመካከላችኹ፡ይኖራልና፥አትፍሩ።

6የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ገና፡አንድ፡ጊዜ፡በቅርብ፡ዘመን፡እኔ፡ሰማያትንና፡ ምድርን፡ባሕርንና፡የብስንም፡አናውጣለኹ፤

7አሕዛብን፡ዅሉ፡አናውጣለኹ፥በአሕዛብ፡ዅሉ፡የተመረጠውም፡ዕቃ፡ይመጣል፤ይህንም፡ቤት፡በክብር፡ እሞላዋለኹ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

8ብሩ፡የእኔ፡ነው፥ወርቁም፡የእኔ፡ነው፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

9ከፊተኛው፡ይልቅ፡የዚህ፡የኹለተኛው፡ቤት፡ክብር፡ይበልጣል፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡ እግዚአብሔር፤በዚህም፡ስፍራ፡ሰላምን፡እሰጣለኹ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

10በዳርዮስም፡በኹለተኛው፡ዓመት፡በዘጠነኛው፡ወር፡በኻያ፡አራተኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡በነቢዩ፡ በሐጌ፡እጅ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

11የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ካህናቱን፡ስለ፡ሕጉ፡ጠይቅ፤

12አንድ፡ሰው፡የተቀደሰ፡ሥጋ፡በልብሱ፡ዘርፍ፡ቢይዝ፥በዘርፉም፡እንጀራ፡ወይም፡ወጥ፥ወይም፡የወይን፡ ጠጅ፥ወይም፡ዘይት፥ወይም፡ማናቸውም፡መብል፡ቢነካ፡ያ፡የተነካው፡በእውኑ፡ይቀደሳልን፧ብለኽ፡ካህናቱን፡ ጠይቃቸው፤ካህናቱም፦አይኾንም፡ብለው፡መለሱ።

13ሐጌም፦በሬሳ፡የረከሰ፡ሰው፡ከነዚህ፡አንዱን፡ቢነካ፡ያ፡የተነካው፡በእውኑ፡ ይረክሳልን፧አለ።ካህናቱም፦አዎን፡ይረክሳል፡ብለው፡መለሱ።

14ሐጌም፡መልሶ፡እንዲህ፡አለ፦ይህ፡ሕዝብና፡ይህ፡ወገን፡በፊቴ፡እንዲሁ፡ነው፥ይላል፡ እግዚአብሔር፤የእጃቸውም፡ሥራ፡ዅሉ፡እንዲሁ፡ነው፤በዚያም፡ያቀረቡት፡ነገር፡ርኩስ፡ነው።

15አኹንም፡ድንጋይ፡በድንጋይ፡ላይ፡በእግዚአብሔር፡መቅደስ፡ሳይነባበር፥ከዛሬ፡ዠምራችኹ፡ወዳለፈው፡ ዘመን፡ልብ፡አድርጉ።

16በዚያን፡ዘመን፡ዅሉ፡ሰው፡ኻያ፡መስፈሪያ፡ወዳለበት፡ምርት፡በመጣ፡ጊዜ፥የተገኘው፡ዐሥር፡ መስፈሪያ፡ብቻ፡ነው፤ዐምሳ፡ማድጋም፡ይቀዳ፡ዘንድ፡ወደ፡መጥመቂያው፡በመጣ፡ጊዜ፥የተገኘው፡ኻያ፡ ብቻ፡ነው።

17በእጃችኹ፡ሥራ፡ዅሉ፡ላይ፡በዋግና፡በዐረማሞ፡በበረዶም፡መታዃችኹ፤እናንተ፡ግን፡ወደ፡እኔ፡ አልተመለሳችኹም፥ይላል፡እግዚአብሔር።

18ከዛሬው፡ከዘጠነኛው፡ወር፡ከኻያ፡አራተኛው፡ቀን፡ዠምራችኹ፡የሚመጣውን፡ዘመን፡ልብ፡ አድርጉ፤የእግዚአብሔር፡መቅደስ፡መሠረት፡ከተተከለበት፡ቀን፡ዠምሮ፡ልብ፡አድርጉ።

19ዘር፡በጐተራ፡ገና፡ይኖራልን፧ወይንና፡በለስ፡ሮማንና፡ወይራ፡አላፈሩም፤ከዚች፡ቀን፡ዠምሬ፡ እባርካችዃለኹ።

20በወሩ፡በኻያ፡አራተኛው፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ኹለተኛ፡ወደ፡ሐጌ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

21ለይሁዳ፡አለቃ፡ለዘሩባቤል፡ተናገር፡እንዲህም፡በል፦ሰማያትንና፡ምድርን፡አናውጣለኹ፤

22የመንግሥታትንም፡ዙፋን፡እገለብጣለኹ፥የአሕዛብንም፡መንግሥታት፡ኀይል፡አጠፋለኹ፤ሠረገላዎችንና፡ የሚቀመጡባቸውንም፡እገለብጣለኹ፤ፈረሶችና፡ፈረሰኛዎቻቸውም፡እያንዳንዳቸው፡በወንድማቸው፡ሰይፍ፡ ይወድቃሉ።

23ባሪያዬ፡የሰላትያል፡ልጅ፡ዘሩባቤል፡ሆይ፥በዚያ፡ቀን፡እወስድኻለኹ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡ እግዚአብሔር፤እኔ፡መርጬኻለኹና፥ይላል፡እግዚአብሔር፥እንደ፡ቀለበት፡ማተሚያ፡አደርግኻለኹ፥ይላል፡ የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source