1እስራኤል፡ሆይ፥በኀጢአትኽ፡ወድቀኻልና፥ወደ፡አምላክኽ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ተመለስ።
2ከእናንተ፡ጋራ፡ቃልን፡ውሰዱ፥ወደ፡እግዚአብሔርም፡ተመልሳችኹ፦ኀጢአትን፡ዅሉ፡ አስወግድ፥በቸርነትም፡ተቀበለን፥በወይፈንም፡ፋንታ፡የከንፈራችንን፡ፍሬ፡እንሰጣለን።
3አሶር፡አያድነንም፤በፈረስ፡ላይ፡አንቀመጥም፤ድኻ፡አደጉም፡ባንተ፡ዘንድ፡ምሕረትን፡ ያገኛልና፥ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ለእጆቻችን፡ሥራ።አምላኮቻችን፡ናችኹ፡አንላቸውም፡በሉት።
4ቍጣዬ፡ከርሱ፡ዘንድ፡ተመልሷልና፥ዐመፃቸውን፡እፈውሳለኹ፥በገዛ፡ፈቃዴ፡እወዳ፟ቸዋለኹ።
5ለእስራኤልም፡እንደ፡ጠል፡እኾነዋለኹ፤እንደ፡አበባም፡ያብባል፥እንደ፡ሊባኖስም፡ሥሩን፡ይሰዳ፟ል።
6ቅርንጫፎቹም፡ይዘረጋሉ፥ውበቱም፡እንደ፡ወይራ፥ሽታውም፡እንደ፡ሊባኖስ፡ይኾናል።
7ከጥላውም፡በታች፡የሚቀመጡ፡ይመለሳሉ፤ከእኽሉም፡የተነሣ፡ይጠግባሉ፤እንደ፡ወይንም፡ዐረግ፡ ያብባሉ፤መታሰቢያውም፡እንደ፡ሊባኖስ፡ወይን፡ጠጅ፡ይኾናል።
8ከእንግዲህ፡ወዲያ፡ጣዖት፡ለኤፍሬም፡ምንድር፡ነው፧እኔ፡ሰምቼዋለኹ፥ወደ፡ርሱም፡እመለከታለኹ፤እኔ፡ እንደ፡ለመለመ፡ጥድ፡ነኝ፤ፍሬኽ፡በእኔ፡ዘንድ፡ይገኛል።
9ይህን፡ነገር፡የሚያስተውል፡ጠቢብ፥የሚያውቃትም፡አስተዋይ፡ማን፡ነው፧የእግዚአብሔር፡መንገድ፡ቅን፡ ነው፥ጻድቃንም፡ይኼዱበታል፤ተላላፊዎች፡ግን፡ይወድቁበታል፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org