Skip to content
← Isaiah

Chapter 1 · Amharic

Isaiah

1በይሁዳ፡ነገሥታት፡በዖዝያንና፡በኢዮአታም፡በአካዝና፡በሕዝቅያስ፡ዘመን፡ስለ፡ይሁዳና፡ስለ፡ኢየሩሳሌም፡ ያየው፡የዓሞጽ፡ልጅ፡የኢሳይያስ፡ራእይ።

2እግዚአብሔር፡ተናግሯልና፥ሰማያት፡ስሙ፥ምድርም፡አድምጪ፤ልጆችን፡ወለድኹ፡ አሳደግኹም፥እነርሱም፡ዐመፁብኝ።

3በሬ፡የገዢውን፡አህያም፡የጌታውን፡ጋጣ፡ዐወቀ፤እስራኤል፡ግን፡አላወቀም፥ሕዝቤም፡አላስተዋለም።

4ኀጢአተኛ፡ወገንና፡በደል፡የተሞላበት፡ሕዝብ፥የክፉዎች፡ዘር፥ርኵሰትን፡የምታደርጉ፡ልጆች፡ ሆይ፥ወዮላችኹ! እግዚአብሔርን፡ትተዋል፡የእስራኤልንም፡ቅዱስ፡አቃለ፟ዋል፥ወደ፡ዃላቸውም፡እየኼዱ፡ ተለይተዋል።

5ደግሞስ፡ዐመፃ፡እየጨመራችኹ፡ለምን፡ገና፡ትቀሰፋላችኹ፧ራስ፡ዅሉ፡ለሕመም፥ልብም፡ዅሉ፡ ለድካም፡ኾኗል።

6ከእግር፡ጫማ፡አንሥቶ፡እስከ፡ራስ፡ድረስ፡ጤና፡የለውም፤ቍስልና፡ዕበጥ፡የሚመግልም፡ ነው፤አልፈረጠም፥አልተጠገነም፥በዘይትም፡አልለዘበም።

7ምድራችኹ፡ባድማ፡ናት፤ከተማዎቻችኹ፡በእሳት፡ተቃጠሉ፤ዕርሻችኹንም፡በፊታችኹ፡ሌላዎች፡ ይበሉታል፤ባዕድ፡እንዳፈረሳት፡ምድር፡ባድማ፡ኾነች።

8የጽዮንም፡ሴት፡ልጅ፡በወይን፡ቦታ፡እንዳለ፡ዳስ፥በዱባ፡አትክልትም፡እንዳለ፡ጐዦ፥አንደ፡ተከበበችም፡ ከተማ፡ኾና፡ቀረች።

9የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ዘርን፡ባያስቀርልን፡ኖሮ፥እንደ፡ሰዶም፡በኾንነ፡እንደ፡ገሞራም፡በመሰልነ፡ ነበር።

10እናንተ፡የሰዶም፡አለቃዎች፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤እናንተ፡የገሞራ፡ሕዝብ፡ ሆይ፥የአምላካችንን፡ሕግ፡አድምጡ።

11የመሥዋዕታችኹ፡ብዛት፡ለእኔ፡ምን፡ይጠቅመኛል፧ይላል፡እግዚአብሔር፤የሚቃጠለውን፡የአውራ፡በግ፡ መሥዋዕትንና፡የፍሪዳን፡ስብ፡ጠግቤያለኹ፤የበሬና፡የበግ፡ጠቦት፡የአውራ፡ፍየልም፡ደም፡ደስ፡አያሠኘኝም።

12በእኔ፡ፊት፡ልትታዩ፡ብትመጡ፡ይህን፡የመቅደሴን፡አደባባይ፡መርገጣችኹን፡ከእጃችኹ፡የሚሻ፡ማን፡ ነው፧

13ምናምንቴውን፡ቍርባን፡ጨምራችኹ፡አታምጡ፤ዕጣን፡በእኔ፡ዘንድ፡አጸያፊ፡ነው፤መባቻችኹንና፡ ሰንበታችኹን፡በጉባኤ፡መሰብሰባችኹን፡አልወድ፟ም፤በደልንም፡የተቀደሰውንም፡ጉባኤ፡አልታገሥም።

14መባቻችኹንና፡በዓላቶቻችኹን፡ነፍሴ፡ጠልታለች፤ሸክም፡ኾነውብኛል፥ልታገሣቸውም፡ደክሜያለኹ።

15እጃችኹንም፡ወደ፡እኔ፡ብትዘረጉ፡ዐይኔን፡ከእናንተ፡እሰውራለኹ፥ልመናንም፡ብታበዙ፡ አልሰማችኹም፤እጆቻችኹ፡ደም፡ተሞልተዋል።

16ታጠቡ፡ሰውነታችኹንም፡አንጹ፤የሥራችኹን፡ክፋት፡ከዐይኔ፡ፊት፡አስወግዱ፤ክፉ፡ማድረግን፡ተዉ፥

17መልካም፡መሥራትን፡ተማሩ፥ፍርድን፡ፈልጉ፥የተገፋውን፡አድኑ፥ለድኻ፡አደጉ፡ፍረዱለት፡ስለ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org መበለቲቱም፡ተሟገቱ።

18ኑና፡እንዋቀስ፡ይላል፡እግዚአብሔር፤ኀጢአታችኹ፡እንደ፡ዐለላ፡ብትኾን፡እንደ፡ዐመዳይ፡ ትነጻለች፤እንደ፡ደምም፡ብትቀላ፡እንደ፡ባዘቶ፡ትጠራለች።

19ዕሺ፡ብትሉ፡ለኔም፡ብትታዘዙ፥የምድርን፡በረከት፡ትበላላችኹ፤

20እምቢ፡ብትሉ፡ግን፡ብታምፁም፥ሰይፍ፡ይበላችዃል፤የእግዚአብሔር፡አፍ፡ይህን፡ተናግሯልና፦

21ፍርድ፡ሞልቶባት፡የነበረው፡የታመነችዪቱ፡ከተማ፡እንዴት፡ጋለሞታ፡ኾነች! ጽድቅ፡ዐድሮባት፡ ነበር፥አኹን፡ግን፡ገዳዮች፡አሉባት።

22ብርሽ፡ወደ፡ዝገት፡ተለወጠ፤የወይን፡ጠጅሽ፡ከውሃ፡ጋራ፡ተደባለቀ።

23አለቃዎችሽ፡ዐመፀኛዎችና፡የሌቦች፡ባልንጀራዎች፡ኾኑ፤ዅሉ፡ጕቦ፡ይወዳ፟ሉ፥ዋጋም፡ለማግኘት፡ ይሮጣሉ፤ለድኻ፡አደጉ፡አይፈርዱም፥የመበለቲቱም፡ሙግት፡ወደ፡እነርሱ፡አይደርስም።

24ስለዚህ፥የእስራኤል፡ኀያል፥የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በጠላቶቼ፡ላይ፡ቍጣዬን፡ እፈጽማለኹ፥የሚቋቋሙኝንም፡እበቀላለኹ።

25እጄንም፡ባንቺ፡ላይ፡አመጣለኹ፥ዝገትሽንም፡በጣም፡አነጻለኹ፥ቈርቈሮሽንም፡ዅሉ፡አወጣለኹ፤

26ፈራጆችሽንም፡እንደ፡ቀድሞ፡አማካሪዎችሽንም፡እንደ፡መዠመሪያው፡ጊዜ፡መልሼ፡አስነሣለኹ፤ከዚያም፡ በዃላ፡የጽድቅ፡ከተማ፡የታመነችም፡ከተማ፡ተብለሽ፡ትጠሪያለሽ።

27ጽዮን፡በፍርድ፡ከርሷም፡የሚመለሱ፡በጽድቅ፡ይድናሉ።

28በደለኛዎችና፡ኀጢአተኛዎች፡ግን፡በአንድነት፡ይሰበራሉ፥እግዚአብሔርንም፡የሚተዉ፡ይጠፋሉ።

29በወደዳችዃት፡የአድባር፡ዛፍ፡ታፍራላችኹና፥ስለ፡መረጣችዃትም፡አትክልት፡ዕፍረት፡ይይዛችዃልና፤

30ቅጠሏ፡እንደ፡ረገፈ፡ዛፍ፥ውሃም፡እንደሌለባት፡አትክልት፡ትኾናላችኹና።

31ኀይለኛውም፡እንደ፡ተልባ፡ጭረት፥ሥራውም፡እንደ፡ጠለሸት፡ይኾናል፤ዐብረውም፡ይቃጠላሉ፡ እነርሱንም፡የሚያጠፋ፡የለም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source