Skip to content
← Isaiah

Chapter 2 · Amharic

Isaiah

1የዓሞጽ፡ልጅ፡ኢሳይያስ፡ስለ፡ይሁዳና፡ስለ፡ኢየሩሳሌም፡ያየው፡ቃል።

2በዘመኑም፡ፍጻሜ፡የእግዚአብሔር፡ቤት፡ተራራ፡በተራራዎች፡ራስ፡ላይ፡ጸንቶ፡ይቆማል፥ከኰረብታዎችም፡ በላይ፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል፥አሕዛብም፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡ይሰበሰባሉ።

3ሕግ፡ከጽዮን፡የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ከኢየሩሳሌም፡ይወጣልና፥ብዙዎች፡አሕዛብ፡ ኼደው፦ኑ፥ወደእግዚአብሔር፡ተራራ፥ወደያዕቆብ፡አምላክ፡ቤት፡እንውጣ፤ርሱም፡መንገዱን፡ ያስተምረናል፥በጐዳናውም፡እንኼዳለን፡ይላሉ።

4በአሕዛብም፡መካከል፡ይፈርዳል፥በብዙ፡አሕዛብም፡ላይ፡ይበይናል፤ሰይፋቸውንም፡ማረሻ፡ጦራቸውንም፡ ማጭድ፡ለማድረግ፡ይቀጠቅጣሉ፤ሕዝብም፡በሕዝብ፡ላይ፡ሰይፍ፡አያነሣም፥ሰልፍም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ አይማሩም።

5እናንተ፡የያዕቆብ፡ቤት፡ሆይ፥ኑ፥በእግዚአብሔር፡ብርሃን፡እንኺድ።

6ሕዝብኽን፡የያዕቆብን፡ቤት፡ትተኻልና፤ይኸውም፡የምሥራቅን፡ሰዎች፡ዐመል፡ስለ፡ተሞሉ፥እንደ፡ ፍልስጥኤማውያንም፡ሟርተኛዎች፡ስለ፡ኾኑ፥ከባዕድ፡ልጆችም፡ጋራ፡ስለ፡ተባበሩ፡ነው።

7ምድራቸው፡በብርና፡በወርቅ፡ተሞልታለች፥ለመዛግብቶቻቸውም፡ፍጻሜ፡የለውም፤ምድራቸውም፡ደግሞ፡ በፈረሶች፡ተሞልታለች፥ለሠረገላዎቻቸውም፡ፍጻሜ፡የለውም። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

8ምድራቸው፡ደግሞ፡በጣዖታት፡ተሞልታለች፤ጣቶቻቸውም፡ላደረጉት፡ለእጃቸው፡ሥራ፡ይሰግዳሉ።

9ታናሹም፡ሰው፡ዝቅ፡ብሏል፥ጨዋውም፡ተዋርዷል፤ኀጢአታቸውንም፡ይቅር፡አትበላቸው።

10ከእግዚአብሔር፡ማስደንገጥና፡ከግርማው፡ክብር፡የተነሣ፡ወደድንጋይ፡ዋሻ፡ግባ፥በመሬትም፡ውስጥ፡ ተሸሸግ።

11ከፍ፡ያለችውም፡የሰው፡ዐይን፡ትዋረዳለች፥የሰዎችም፡ኵራት፡ትወድቃለች፥በዚያም፡ቀን፡እግዚአብሔር፡ ብቻውን፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል።

12የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡ቀን፡በትዕቢተኛውና፡በኵራተኛው፡ዅሉ፡ላይ፡ከፍ፡ባለውም፡ላይ፡ ይኾናል፥ርሱም፡ይዋረዳል፤

13ደግሞም፡በረዥሙ፡ከፍ፡ባለው፡በሊባኖስ፡ዝግባ፡ዅሉ፡ላይ፥በባሳንም፡ዛፍ፡ዅሉ፡ላይ፥

14በረዥሙም፡ተራራ፡ዅሉ፡ላይ፥ከፍ፡ባለውም፡ኰረብታ፡ዅሉ፡ላይ፥

15በረዥሙም፡ግንብ፡ዅሉ፡ላይ፥በተመሸገውም፡ቅጥር፡ዅሉ፡ላይ፥

16በተርሴስም፡መርከብ፡ዅሉ፡ላይ፥በሚያማምሩ፡ጣዖታትም፡ዅሉ፡ላይ፡ይኾናል።

17ሰውም፡ዅሉ፡ይዋረዳል፥የሰውም፡ኵራት፡ይወድቃል፥በዚያም፡ቀን፡እግዚአብሔር፡ብቻ፡ከፍ፡ከፍ፡ ይላል።

18ጣዖቶቻቸውም፡ዅሉ፡ፈጽመው፡ይጠፋሉ።

19እግዚአብሔርም፡ምድርን፡ያናውጥ፡ዘንድ፡በተነሣ፡ጊዜ፥ሰዎች፡ከማስደንገጡና፡ከግርማው፡ክብሩ፡ የተነሣ፥ወደድንጋይ፡ዋሻና፡ወደምድር፡ንቃቃት፡ውስጥ፡ይገባሉ።

20በዚያን፡ቀን፡ሰው፡ይሰግድላቸው፡ዘንድ፡ያበጇቸውን፡የብሩንና፡የወርቁን፡ጣዖቶቹን፡ለፍልፈልና፡ ለሌሊት፡ወፍ፡ይጥላል።

21እግዚአብሔርም፡ምድርን፡ያናውጥ፡ዘንድ፡በተነሣ፡ጊዜ፡ከማስደንገጡና፡ከግርማው፡ክብር፡የተነሣ፡ ወደድንጋይ፡ዋሻና፡ወደተሰነጠቁ፡አለቶች፡ውስጥ፡ይገባሉ።

22እስትንፋሱ፡በአፍንጫው፡ውስጥ፡ያለበትን፡ሰው፡ተዉት፤ርሱ፡ስለ፡ምን፡ይቈጠራል፧

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source