Skip to content
← Isaiah

Chapter 66 · Amharic

Isaiah

1እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሰማይ፡ዙፋኔ፡ነው፥ምድርም፡የእግሬ፡መረገጫ፡ናት፤የምትሠሩልኝ፡ ቤት፡ምን፡ዐይነት፡ነው፧የማርፍበትስ፡ስፍራ፡ምንድር፡ነው፧

2እነዚህን፡ዅሉ፡እጄ፡ሠርታለችና፡እነዚህ፡ዅሉ፡የእኔ፡ናቸው፡ይላል፡እግዚአብሔር፤ነገር፡ግን፥ወደዚህ፡ ወደ፡ትሑት፥መንፈሱም፡ወደተሰበረ፥በቃሌም፡ወደሚንቀጠቀጥ፡ሰው፡እመለከታለኹ።

3በሬን፡የሚያርድልኝ፡ሰውን፡እንደሚገድል፡ነው፤ጠቦትንም፡የሚሠዋ፡የውሻውን፡ዐንገት፡እንደሚሰብር፡ ነው፤የእኽልን፡ቍርባን፡የሚያቀርብ፡የዕሪያን፡ደም፡እንደሚያቀርብ፡ነው፤ዕጣንን፡የሚያጥን፡ጣዖትን፡ እንደሚባርክ፡ነው።እነዚህ፡የገዛ፡መንገዳቸውን፡መረጡ፤ነፍሳቸውም፡በርኵሰታቸው፡ደስ፡ይላታል፤

4እኔ፡ደግሞ፡የተሳለቀባቸውን፡እመርጣለኹ፥የፈሩትንም፡ነገር፡አመጣባቸዋለኹ፤በፊቴ፡ክፉ፡ነገርን፡ አደረጉ፥ያልወደድኹትንም፡መረጡ፡እንጂ፡በጠራኹ፡ጊዜ፡አልመለሱልኝምና፥በተናገርኹም፡ጊዜ፡ አልሰሙኝምና።

5በቃሉ፡የምትንቀጠቀጡ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፦የጠሏችኹ፡ስለ፡ስሜም፡ያባረሯችኹ፡ ወንድሞቻችኹ፦ደስታችኹን፡እናይ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ይክበር፡ብለዋል፤ነገር፡ግን፥ያፍራሉ።

6የጩኸት፡ድምፅ፡ከከተማ፥ድምፅም፡ከመቅደስ፥በጠላቶቹ፡ላይ፡ፍዳን፡የሚያመጣ፡የእግዚአብሔር፡ ድምፅ፡ተሰምቷል።

7ሳታምጥ፡ወለደች፤ምጥም፡ሳያገኛት፡ወንድ፡ልጅን፡ወለደች።

8ከቶ፡እንዲህ፡ያለ፡ነገር፡ማን፡ሰምቷል፧እንዲህስ፡ያለ፡ነገር፡ማን፡አይቷል፧በእውኑ፡አገር፡ባንድ፡ቀን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ታምጣለችን፧ወይስ፡ባንድ፡ጊዜ፡ሕዝብ፡ይወለዳልን፧ጽዮን፡እንዳማጠች፡ወዲያው፡ልጆቿን፡ወልዳለችና።

9በእውኑ፡ወደ፡መውለድ፡የማደርስ፡እኔ፡አላስወልድምን፧ይላል፡እግዚአብሔር፤የማስወልድስ፡ማሕፀንን፡ እኔ፡እዘጋለኹን፧ይላል፡አምላክሽ።

10እናንተ፡የምትወዷ፟ት፡ዅሉ፥ከኢየሩሳሌም፡ጋራ፡ሐሤትን፡አድርጉ፥ስለ፡ርሷም፡ደስ፡ ይበላችኹ፤እናንተም፡የምታለቅሱላት፡ዅሉ፥ከርሷ፡ጋራ፡በደስታ፡ሐሤትን፡አድርጉ፥

11ትጠቡ፡ዘንድ፡ከማጽናናቷም፡ጡት፡ትጠግቡ፡ዘንድ፤እጅግ፡ጠጥታችኹ፡በክብሯ፡ሙላት፡ደስ፡ ይላችኹ፡ዘንድ።

12እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦እንሆ፥ሰላምን፡እንደ፡ወንዝ፥የአሕዛብንም፡ክብር፡እንደሚጐርፍ፡ ፈሳሽ፡እመልስላታለኹ፤ከዚያም፡ትጠባላችኹ፥በጫንቃ፡ላይ፡ይሸከሟችዃል፡በጕልበትም፡ላይ፡እያስቀመጡ፡ ያቀማጥሏችዃል።

13እናት፡ልጇን፡እንደምታጽናና፡እንዲሁ፡አጽናናችዃለኹ፥በኢየሩሳሌምም፡ውስጥ፡ትጽናናላችኹ።

14ታያላችኹ፥ልባችኹም፡ሐሤት፡ታደርጋለች፥ዐጥንታችኹም፡እንደ፡ለምለም፡ሣር፡ ትበቅላለች፤የእግዚአብሔርም፡እጅ፡ለሚፈሩት፡ትታወቃለች፥በጠላቶቹም፡ላይ፡ይቈጣል።

15እንሆ፥እግዚአብሔር፡መዓቱን፡በቍጣ፥ዘለፋውንም፡በእሳት፡ነበልባል፡ይመልስ፡ዘንድ፡ከእሳት፡ጋራ፡ ይመጣል፥ሠረገላዎቹም፡እንደ፡ዐውሎ፡ነፋስ፡ይኾናሉ።

16እግዚአብሔርም፡በሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡ላይ፡በእሳትና፡በሰይፉ፡ይፈርዳል፤በእግዚአብሔርም፡ተወግተው፡ የሞቱት፡ይበዛሉ።

17በመካከላቸው፡ያለውን፡አንዱን፡ተከትለው፡ወደ፡ገነቱ፡ይገቡ፡ዘንድ፡ሰውነታቸውን፡የሚቀድሱና፡ የሚያነጹ፥የዕሪያንም፡ሥጋ፡አስጸያፊ፡ነገርንም፡ዐይጥንም፡የሚበሉ፡በአንድነት፡ይጠፋሉ፥ይላል፡ እግዚአብሔር።

18ሥራቸውንና፡ዐሳባቸውን፡ዐውቄያለኹና፤አሕዛብንና፡ልሳናትን፡ዅሉ፡የምሰበስብበት፡ጊዜ፡ ይደርሳል፥እነርሱም፡ይመጣሉ፡ክብሬንም፡ያያሉ።

19በመካከላቸውም፡ምልክት፡አደርጋለኹ፥ከነርሱም፡የዳኑትን፡ዝናዬን፡ወዳልሰሙ፥ክብሬንም፡ወዳላዩ፡ወደ፡ አሕዛብ፡ወደ፡ተርሴስ፡ወደ፡ፉጥ፡ወደ፡ሉድ፡ወደ፡ሞሳሕ፡ወደ፡ቶቤል፡ወደ፡ያዋን፡በሩቅ፡ወዳሉ፡ደሴቶች፡ እልካቸዋለኹ፥በአሕዛብም፡መካከል፡ክብሬንም፡ይናገራሉ።

20የእስራኤል፡ልጆች፡ቍርባናቸውን፡በጥሩ፡ዕቃ፡አድርገው፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ እንደሚያመጡ፥እንዲሁ፡ለእግዚአብሔር፡ቍርባን፡ይኾን፡ዘንድ፡ወንድሞቻችኹን፡ዅሉ፥በፈረሶችና፡ በሠረገላዎች፥በዐልጋዎችና፡በበቅሎዎች፡በጠያር፡ግመሎችም፡ላይ፡አድርገው፥ከአሕዛብ፡ዅሉ፡ ወደተቀደሰው፡ተራራዬ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ያመጧቸዋል፥ይላል፡እግዚአብሔር።

21ካህናትና፡ሌዋውያን፡እንዲኾኑ፡ከነርሱ፡እወስዳለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

22እኔ፡የምሠራቸው፡ዐዲስ፡ሰማይና፡ዐዲስ፡ምድር፡ከፊቴ፡ጸንተው፡እንደሚኖሩ፥እንዲሁ፡ዘራችኹና፡ ስማችኹ፡ጸንተው፡ይኖራሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

23እንዲህ፡ይኾናል፤በየመባቻውና፡በየሰንበቱ፡ሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡በፊቴ፡ይሰግድ፡ዘንድ፡ዘወትር፡ ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር።

24ወጥተውም፡በእኔ፡ያመፁብኝን፡ሰዎች፡ሬሳቸውን፡ያያሉ፤ትላቸው፡አይሞትምና፥እሳታቸውም፡ አይጠፋምና፤ለሥጋ፡ለባሽም፡ዅሉ፡አስጸያፊ፡ነገር፡ይኾናሉ፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source