Skip to content
← Jeremiah

Chapter 1 · Amharic

Jeremiah

1በብንያም፡አገር፡በዐናቶት፡ከነበሩ፡ካህናት፡የኾነ፡የኬልቅያስ፡ልጅ፡የኤርምያስ፡ቃል።

2በይሁዳ፡ንጉሥ፡በዓሞጽ፡ልጅ፡በኢዮስያስ፡ዘመን፡በመንግሥቱ፡በዐሥራ፡ሦስተኛው፡ዓመት፡ የእግዚአብሔር፡ቃል፡መጣለት።

3በይሁዳም፡ንጉሥ፡በኢዮስያስ፡ልጅ፡በኢዮአቄም፡ዘመን፥እስከይሁዳ፡ንጉሥ፡እስከኢዮስያስ፡ልጅ፡እስከ፡ ሴዴቅያስ፡እስከ፡ዐሥራ፡አንደኛው፡ዓመት፡ፍጻሜ፥ኢየሩሳሌም፡እስከተማረከችበት፡እስከ፡ዐምስተኛው፡ወር፡ ድረስ፡መጣ።

4የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

5በሆድ፡ሳልሠራኽ፡ዐውቄኻለኹ፥ከማሕፀንም፡ሳትወጣ፡ቀድሼኻለኹ፥ለአሕዛብም፡ነቢይ፡አድርጌኻለኹ።

6እኔም፦ወዮ፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥እንሆ፥ብላቴና፡ነኝና፡እናገር፡ዘንድ፡አላውቅም፡አልኹ።

7እግዚአብሔር፡ግን፡እንዲህ፡አለኝ፦ወደምሰድ፟ኽ፡ዅሉ፡ዘንድ፡ትኼዳለኽና፥የማዝ፟ኽንም፡ዅሉ፡ ትናገራለኽና፦ብላቴና፡ነኝ፡አትበል።

8እኔ፡አድንኽ፡ዘንድ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝና፡ከፊታቸው፡አትፍራ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

9እግዚአብሔርም፡እጁን፡ዘርግቶ፡አፌን፡ዳሰሰ፥እግዚአብሔርም፦እንሆ፥ቃሌን፡በአፍኽ፡ውስጥ፡ አኑሬያለኹ፤

10እንሆ፦ትነቅልና፡ታፈርስ፡ዘንድ፥ታጠፋና፡ትገለብጥ፡ዘንድ፥ትሠራና፡ትተክል፡ዘንድ፡በአሕዛብና፡ በመንግሥታት፡ላይ፡ዛሬ፡አድርጌኻለኹ፡አለኝ።

11ደግሞ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፦ኤርምያስ፡ሆይ፥ምን፡ታያለኽ፧እያለ፡ወደ፡እኔ፡ መጣ።እኔም፦የለውዝ፡በትር፡አያለኹ፡አልኹ።

12እግዚአብሔርም፦እፈጽመው፡ዘንድ፡በቃሌ፡እተጋለኹና፡መልካም፡አይተኻል፡አለኝ።

13ኹለተኛም፡ጊዜ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፦ምን፡ታያለኽ፧እያለ፡ወደ፡እኔ፡መጣ።እኔም፦የሚፈላ፡ አፍላል፡አያለኹ፥ፊቱም፡ከሰሜን፡ወገን፡ነው፡አልኹ።

14እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አለኝ፦ከሰሜን፡ወገን፡ክፉ፡ነገር፡በምድሪቱ፡በተቀመጡ፡ዅሉ፡ላይ፡ ይገለጣል።

15እንሆ፥እኔ፡በሰሜን፡ያሉትን፡የመንግሥታትን፡ወገኖች፡ዅሉ፡እጠራለኹ፥ይላል፡ እግዚአብሔር፤እነርሱም፡ይመጣሉ፡እያንዳንዳቸውም፡በኢየሩሳሌም፡በር፡መግቢያ፡በዙሪያዋ፡በቅጥሯ፡ዅሉ፡ ላይ፡በይሁዳም፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ላይ፡ዙፋናቸውን፡ያስቀምጣሉ።

16ስለ፡ክፋታቸውም፡ዅሉ፡እኔን፡ስለ፡ተዉ፥ለሌላዎችም፡አማልክት፡ስላጠኑ፥ለእጃቸውም፡ሥራ፡ስለ፡ ሰገዱ፥ፍርዴን፡በእነርሱ፡ላይ፡እናገራለኹ።

17አንተ፡ግን፡ወገብኽን፡ታጠቅ፥ተነሥም፥ያዘዝኹኽም፡ዅሉ፡ንገራቸው፤በፊታቸው፡እንዳላስፈራኽ፡ አትፍራቸው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

18እንሆ፥በምድሪቱ፡ዅሉ፡ላይ፡በይሁዳም፡ነገሥታት፡በአለቃዎቿና፡በካህናቷ፡ላይ፡በምድሪቱም፡ሕዝብ፡ ላይ፡እንደ፡ተመሸገ፡ከተማ፡እንደ፡ብረትም፡ዐምድ፡እንደ፡ናስም፡ቅጥር፡ዛሬ፡አድርጌኻለኹ።

19ከአንተ፡ጋራ፡ይዋጋሉ፥ነገር፡ግን፥አድንኽ፡ዘንድ፡እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝና፡ድል፡አይነሡኽም፥ይላል፡ እግዚአብሔር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source