1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2ኺድ፥በኢየሩሳሌም፡ዦሮ፡ጩኽ፥እንዲህም፡በል፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የብላቴንነትሽን፡ ምሕረት፡የታጨሽበትንም፡ፍቅር፥በምድረ፡በዳ፡ዘር፡ባልተዘራበት፡ምድር፡እንደ፡ተከተልሽኝ፡ዐስቤያለኹ።
3እስራኤል፡ለእግዚአብሔር፡ቅዱስ፡ነበረ፥የቡቃያውም፡በኵራት፡ነበረ፤የበሉት፡እንደ፡በደለኛዎች፡ ይቈጠራሉ፥ክፉም፡ነገር፡ያገኛቸዋል፥ይላል፡እግዚአብሔር።
4የያዕቆብ፡ቤት፡የእስራኤልም፡ቤት፡ወገኖች፡ዅሉ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ።
5እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦አባቶቻችኹ፡ከእኔ፡ዘንድ፡የራቁ፥ከንቱነትንም፡የተከተሉ፥ከንቱም፡የኾኑ፡ ምን፡ክፋት፡አግኝተውብኝ፡ነው፧
6እነርሱም፦ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣን፥በምድረ፡በዳም፡በባድማ፡ጕድጓድም፡ባለበት፡ምድር፥በውሃ፡ ጥምና፡በሞት፡ጥላ፡ምድር፥ማንም፡በማያልፍበትና፡ማንም፡በማይቀመጥበት፡ምድር፡የመራን፡እግዚአብሔር፡ ወዴት፡አለ፧አላሉም።
7ፍሬዋንና፡በረከቷንም፡ትበሉ፡ዘንድ፡ወደ፡ፍሬያማ፡ምድር፡አገባዃችኹ፤ነገር፡ግን፥በገባችኹ፡ጊዜ፡ ምድሬን፡አረከሳችኹ፥ርስቴንም፡አጐሳቈላችኹ።
8ካህናቱም፦እግዚአብሔር፡ወዴት፡አለ፧አላሉም፥ባለኦሪቶችም፡አላወቁኝም፤ገዢዎችም፡ ዐመፁብኝ፥ነቢያትም፡በበዓል፡ትንቢት፡ተናገሩ፥የማይረባንም፡ነገር፡ተከተሉ።
9ስለዚህ፥ከእናንተ፡ጋራ፡እከራከራለኹ፥ከልጆቻችኹም፡ልጆች፡ጋራ፡እከራከራለኹ።
10ወደኪቲም፡ደሴቶች፡ዕለፉና፡ተመልከቱ፥ወደ፡ቄዳርም፡ላኩና፡እጅግ፡መርምሩ፥እንደዚህም፡ያለ፡ነገር፡ ኾኖ፡እንደ፡ኾነ፡እዩ።
11በእውኑ፡አማልክት፡ያልኾኑትን፡አማልክቱን፡የለወጣቸው፡አንድ፡ሕዝብ፡አለን፧ነገር፡ግን፡ሕዝቤ፡ ክብሩን፡ለማይረባ፡ነገር፡ለወጠ።
12ሰማያት፡ሆይ፥በዚህ፡ተደነቁ፥እጅግም፡ደንግጡና፡ተንቀጥቀጡ፡ይላል፡እግዚአብሔር።
13ሕዝቤ፡ኹለቱን፡ክፉ፡ነገሮች፡አድርገዋልና፤እኔን፡የሕያውን፡ውሃ፡ምንጭ፡ትተውኛል፥የተቀደዱትንም፡ ጕድጓዶች፥ውሃውን፡ይይዙ፡ዘንድ፡የማይችሉትን፡ጕድጓዶች፥ለራሳቸው፡ቈፍረዋል።
14በእውኑ፡እስራኤል፡ባሪያ፡ነውን፧ወይስ፡የቤት፡ውላጅ፡ነውን፧ስለ፡ምን፡ብዝበዛ፡ኾነ፧
15የአንበሳ፡ደቦሎች፡በርሱ፡ላይ፡አገሡ፥ድምፃቸውንም፡ሰጡ፤ምድሩንም፡ባድማ፡አደረጉ፥ከተማዎቹም፡ ተቃጠሉ፡የሚቀመጥባቸውም፡የለም።
16የሜምፎስና፡የጣፍናስ፡ልጆች፡አስነወሩሽ፡አላገጡብሽም።
17ይህ፡ዅሉ፡የኾነብሽ፡እኔን፡ስለ፡ተውሽ፡አይደለምን፧ይላል፡እግዚአብሔር፡አምላክሽ።
18አኹንስ፡የሺሖርን፡ውሃ፡ትጠጪ፡ዘንድ፡በግብጽ፡መንገድ፡ምን፡ጕዳይ፡አለሽ፧የኤፍራጥስንም፡ውሃ፡ ትጠጪ፡ዘንድ፡በአሶር፡መንገድ፡ምን፡ጕዳይ፡አለሽ፧
19ክፋትሽ፡ይገሥጽሻል፡ክዳትሽም፡ይዘልፍሻል፤አምላክሽንም፡እግዚአብሔርን፡የተውሽ፡እኔንም፡መፍራት፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የሌለብሽ፡ክፉና፡መራራ፡ነገር፡እንደ፡ኾነ፡ዕወቂ፥ተመልከቺ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
20ከጥንት፡ዠምሮ፡ቀንበርሽን፡ሰብሬያለኹ፡እስራትሽንም፡ቈርጫለኹ፤አንቺም፦አላገለግልም፡ አልሽ፥ነገር፡ግን፥ከፍ፡ባለው፡ኰረብታ፡ዅሉ፡ላይ፡ከለምለምም፡ዛፍ፡ዅሉ፡በታች፡ለማመንዘር፡ ተጋደምሽ።
21እኔ፡የተመረጠች፡ወይን፡ፍጹምም፡እውነተኛ፡ዘር፡አድርጌ፡ተክዬሽ፡ነበር፤አንቺ፡ግን፡ክፉ፡የእንግዳ፡ ወይን፡ግንድ፡ኾነሽ፡እንዴት፡ተለወጥሽብኝ፧
22በእንዶድ፡ብትታጠቢም፥ለራስሽም፡ሳሙና፡ብታበዢ፥በእኔ፡ፊት፡በኀጢአትሽ፡ረክሰሻል፡ይላል፡ጌታ፡ እግዚአብሔር።
23አንቺስ፦አልረከስኹም፥በዓሊምንም፡አልተከተልኹም፡እንዴት፡ትያለሽ፧በቈላ፡ያለውን፡መንገድሽን፡ ተመልከቺ፥ያደረግሽውንም፡ዕወቂ፤በመንገድም፡ላይ፡እንደ፡ተለቀቀች፡እንደ፡ፈጣን፡ግመል፡ኾነሻል፤
24በምኞቷ፡ነፋስን፡እንደምታሸት፟፥በምድረ፡በዳ፡እንደ፡ለመደች፡እንደ፡ሜዳ፡አህያ፡ነሽ፤ከምኞቷ፡ የሚመልሳት፡ማን፡ነው፧የሚሿት፡ዅሉ፡አይደክሙም፥በወራቷ፡ያገኟታል።
25እግርሽን፡ከሻካራ፡መንገድ፡ጕረሮሽንም፡ከውሃ፡ጥም፡ከልክዪ፤አንቺ፡ግን፦እጨክናለኹ፥እንግዳዎችን፡ ወድጃለኹና፥እከተላቸዋለኹም፡አልሽ።
26ሌባ፡በተያዘ፡ጊዜ፡እንደሚያፍር፡እንዲሁ፡የእስራኤል፡ቤት፥እነርሱና፡ንጉሦቻቸውም፡አለቃዎቻቸውም፡ ካህናታቸውም፡ነቢያታቸውም፡ያፍራሉ።
27ግንዱን፦አንተ፡አባቴ፡ነኽ፤ድንጋዩንም፦አንተ፡ወለድኸኝ፡ይላሉ፤ፊታቸውንም፡ሳይኾን፡ዠርባቸውን፡ ሰጡኝ፥በመከራቸው፡ጊዜ፡ግን፦ተነሥተኽ፡አድነን፡ይላሉ።
28ለአንተ፡የሠራኻቸው፡አማልክትኽ፡ወዴት፡ናቸው፧ይሁዳ፡ሆይ፥አማልክትኽ፡እንደ፡ከተማዎችኽ፡ ቍጥር፡እንዲሁ፡ናቸውና፥ይነሡ፡በመከራኽም፡ጊዜ፡ያድኑኽ።
29ከእኔ፡ጋራ፡የምትከራከሩ፡ለምንድር፡ነው፧ዅላችኹ፡ዐምፃችኹብኛል፡ይላል፡እግዚአብሔር።
30ልጆቻችኹን፡በከንቱ፡ቀሥፌአቸዋለኹ፤ተግሣጽን፡አልተቀበሉም፤ሰይፋችኹ፡እንደሚሰብር፡አንበሳ፡ ነቢያታችኹን፡በልቷል።
31ትውልድ፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ተመልከቱ፦በእውኑ፡ለእስራኤል፡ምድረ፡በዳ፡ወይስ፡ የጨለመች፡ምድር፡ኾንኹባትን፧ሕዝቤስ፡ስለ፡ምን፦እኛ፡ፈርጥጠናል፤ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ወዳንተ፡ አንመለስም፡ይላል፧
32በእውኑ፡ቈንዦ፡ጌጧን፡ወይስ፡ሙሽራ፡ዝርግፍ፡ጌጧን፡ትረሳለችን፧ሕዝቤ፡ግን፡የማይቈጠር፡ወራት፡ ረስቶኛል።
33ፍቅርን፡ለመሻት፡መንገድሽን፡እንዴት፡ታቀኛለሽ! ስለዚህ፡ለክፉዎች፡ሴቶች፡እንኳ፡መንገድሽን፡ አስተምረሻል።
34በእጆችሽም፡የንጹሓን፡ድኻዎች፡ደም፡ተገኝቷል፤በእነዚህ፡ዅሉ፡ላይ፡በግልጥ፡አገኘኹት፡እንጂ፡ በስውር፡ፈልጌ፡አላገኘኹትም።
35አንቺ፡ግን፦ንጹሕ፡ነኝ፤በእውነት፡ቍጣው፡ከእኔ፡ተመልሷል፡አልሽ።እንሆ፦ኀጢአት፡አልሠራኹም፡ ብለሻልና፥በፍርድ፡እከስ፟ሻለኹ።
36መንገድሽን፡ትለውጪ፡ዘንድ፡ለምን፡እጅግ፡ትሮጫለሽ፧አሶር፡እንዳሳፈረሽ፡ግብጽ፡ያሳፍርሻል።
37እግዚአብሔር፡የታመንሽባቸውን፡ጥሏልና፥በእነርሱም፡አይከናወንልሽምና፡እጅሽን፡በራስሽ፡ላይ፡አድርገሽ፡ ከዚያ፡ደግሞ፡ትወጫለሽ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org