Skip to content
← Jeremiah

Chapter 52 · Amharic

Jeremiah

1ሴዴቅያስ፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡አንድ፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡አንድ፡ ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡ዐሚጣል፡የተባለች፡የሊብና፡ሰው፡የኤርምያስ፡ልጅ፡ነበረች። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

2ኢዮአቄምም፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ።

3ከፊቱም፡አውጥቶ፡እስኪጥላቸው፡ድረስ፡ይህ፡በእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በኢየሩሳሌምና፡በይሁዳ፡ላይ፡ ኾኗልና፤ሴዴቅያስም፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡ላይ፡ዐመፀ።

4ሴዴቅያስም፡በነገሠ፡በዘጠነኛው፡ዓመት፡በዐሥረኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥረኛው፡ቀን፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ ናቡከደነጾርና፡ሰራዊቱ፡ዅሉ፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡መጥተው፡ከበቧት፡በዙሪያዋም፡ዕርድ፡አደረገ።

5ከተማዪቱም፡እስከ፡ንጉሡ፡እስከ፡ሴዴቅያስ፡እስከ፡ዐሥራ፡አንደኛው፡ዓመት፡ድረስ፡ተከባ፟፡ነበር።

6በአራተኛውም፡ወር፡በዘጠነኛው፡ቀን፡በከተማዪቱ፡ራብ፡ጸንቶ፡ነበር፥ለአገሩም፡ሰዎች፡እንጀራ፡ታጣ።

7ከተማዪቱም፡ተሰበረች፥ሰልፈኛዎችም፡ዅሉ፡ሸሹ፥በኹለቱም፡ቅጥር፡መካከል፡ባለው፡በር፡ወደንጉሡ፡ አትክልት፡በሚወስደው፡መንገድ፡በሌሊት፡ከከተማዪቱ፡ወጡ።ከለዳውያንም፡በከተማዪቱ፡ዙሪያ፡ ነበሩ፤በዐረባም፡መንገድ፡ኼዱ።

8የከለዳውያንም፡ሰራዊት፡ንጉሡን፡ተከታተሉት፥በኢያሪኮም፡ሜዳ፡ሴዴቅያስን፡ያዙ፤ሰራዊቱም፡ዅሉ፡ ከርሱ፡ዘንድ፡ተበትነው፡ነበር።

9ንጉሡንም፡ይዘው፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ወዳለባት፡በሐማት፡ምድር፡ወዳለችው፡ወደ፡ሪብላ፡ አመጡት፤ርሱም፡ፍርድን፡በርሱ፡ላይ፡ተናገረ።

10የባቢሎንም፡ንጉሥ፡የሴዴቅያስን፡ልጆች፡በፊቱ፡ገደላቸው፥የይሁዳንም፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ደግሞ፡በሪብላ፡ ገደላቸው።

11የሴዴቅያስንም፡ዐይኖች፡አወጣ፤የባቢሎንም፡ንጉሥ፡በሰንሰለት፡አሰረው፡ወደ፡ባቢሎንም፡ ወሰደው፥እስኪሞትም፡ድረስ፡በግዞት፡ቤት፡አኖረው።

12በባቢሎን፡ንጉሥ፡በናቡከደነጾር፡በዐሥራ፡ዘጠነኛው፡ዓመት፡በዐምስተኛው፡ወር፡ከወሩም፡በዐሥረኛው፡ ቀን፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡ፊት፡የቆመው፡የዘበኛዎቹ፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጣ።

13የእግዚአብሔርን፡ቤትና፡የንጉሡን፡ቤት፡አቃጠለ፤የኢየሩሳሌምንም፡ቤቶች፡ዅሉ፥ታላላቆችን፡ቤቶች፡ ዅሉ፥በእሳት፡አቃጠለ።

14ከዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ጋራ፡የነበረው፡የከለዳውያን፡ሰራዊት፡ዅሉ፡የኢየሩሳሌምን፡ቅጥር፡ዅሉ፡ዙሪያዋን፡ አፈረሱ።

15የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡የሕዝቡን፡ድኻዎች፥በከተማም፡ውስጥ፡የቀረውን፡ሕዝብ፥ሸሽተውም፡ ወደባቢሎን፡ንጉሥ፡የተጠጉትን፥የሕዝቡንም፡ቅሬታ፡አፈለሰ።

16የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፥ከአገሩ፡ድኻዎች፥ወይን፡ተካዮችና፡ዐራሾች፡እንዲኾኑ፥አስቀረ።

17ከለዳውያንም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡የነበሩትን፡የናስ፡ዐምዶች፡በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የነበሩትን፡ መቀመጫዎችና፡የናሱን፡ኵሬ፡ሰባበሩ፥ናሱንም፡ወደ፡ባቢሎን፡ወሰዱ።

18ምንቸቶቹንና፡መጫሪያዎችንም፡መኰስተሪያዎችንና፡ድስቶችን፡ጭልፋዎችንም፡የሚያገለግሉበትንም፡የናስ፡ ዕቃ፡ዅሉ፡ወሰዱ።

19የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ጽዋዎቹንና፡ማንደጃዎቹን፡ድስቶቹንና፡ምንቸቶችን፡መቅረዞችንና፡ጭልፋዎቹን፡ መንቀሎችንም፥የወርቁን፡ዕቃ፡በወርቅ፥የብሩንም፡ዕቃ፡በብር፡አድርጎ፥ወሰደ።

20ንጉሡ፡ሰሎሞንም፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡ያሠራቸውን፡ኹለቱን፡ዐምዶች፥አንዱንም፡ ኵሬ፥ከመቀመጫዎቹም፡በታች፡የነበሩትን፡ዐሥራ፡ኹለቱን፡የናስ፡በሬዎች፡ወሰደ፤ለእነዚህ፡ዕቃዎች፡ዅሉ፡ ናስ፡ሚዛን፡አልነበረም።

21ዐምዶቹም፥የአንዱ፡ዐምድ፡ቁመት፡ዐሥራ፡ስምንት፡ክንድ፡ነበረ፥የዙሪያውም፡መጠን፡ዐሥራ፡ኹለት፡ ክንድ፡ነበረ፤ውፍረቱም፡አራት፡ጣት፡ያኽል፡ነበረ፥ባዶም፡ነበረ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

22የናሱም፡ጕልላት፡በላዩ፡ነበረ፤የአንዱም፡ጕልላት፡ቁመት፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ፥በጕልላቱም፡ላይ፡ በዙሪያው፡ዅሉ፡ከናስ፡የተሠሩ፡መረበብና፡ሮማኖች፡ነበሩበት፤በኹለተኛውም፡ዐምድ፡ደግሞ፡እንደዚህ፡ያለ፡ ነገርና፡ሮማኖች፡ነበሩበት።

23በስተውጭም፡ዘጠና፡ስድስት፡ሮማኖች፡ነበሩ።በመረበቡም፡ዙሪያ፡የነበሩ፡ሮማኖች፡ዅሉ፡አንድ፡መቶ፡ ነበሩ።

24የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ታላቁን፡ካህን፡ሰራያን፡ኹለተኛውንም፡ካህን፡ሶፎንያስን፡ሦስቱንም፡በረኛዎች፡ ወሰደ፤

25ከከተማዪቱም፡በሰልፈኛዎች፡ላይ፡ተሾመው፡ከነበሩት፡አንዱን፡ጃን፡ደረባ፥በከተማዪቱም፡ከሚገኙት፡ በንጉሡ፡ፊት፡ከሚቆሙት፡ሰባቱን፡ሰዎች፥የአገሩንም፡ሕዝብ፡የሚያሰልፈውን፡የሰራዊቱን፡አለቃ፡ ጸሓፊ፥በከተማዪቱም፡ከተገኙት፡ከአገሩ፡ሕዝብ፡ስድሳ፡ሰዎች፡ወሰደ።

26የዘበኛዎቹም፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡ወስዶ፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡ወዳለበት፡ወደ፡ሪብላ፡አመጣቸው።

27የባቢሎንም፡ንጉሥ፡መታቸው፥በሐማትም፡ምድር፡ባለችው፡በሪብላ፡ገደላቸው።እንዲሁ፡ይሁዳ፡ከአገሩ፡ ተማረከ።

28ናቡከደነጾር፡የማረከው፡ሕዝብ፡ይህ፡ነው፤በሰባተኛው፡ዓመት፡ሦስት፡ሺሕ፡ኻያ፡ሦስት፡አይሁድ፤

29ናቡከደነጾርም፡በዐሥራ፡ስምንተኛው፡ዓመት፡ስምንት፡መቶ፡ሠላሳ፡ኹለት፡ነፍስ፡ከኢየሩሳሌም፡ ማርኳል፤

30በናቡከደነጾር፡በኻያ፡ሦስተኛው፡ዓመት፡የዘበኛዎቹ፡አለቃ፡ናቡዘረዳን፡ከአይሁድ፡ሰባት፡መቶ፡አርባ፡ ዐምስት፡ነፍስ፡ማርኳል፤ሰዎች፡ዅሉ፡አራት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ነበሩ።

31እንዲህም፡ኾነ፤የይሁዳ፡ንጉሥ፡ዮአኪን፡በተማረከ፡በሠላሳ፡ሰባተኛው፡ዓመት፡በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ ወር፡ከወሩም፡በኻያ፡ዐምስተኛው፡ቀን፥የባቢሎን፡ንጉሥ፡ዮርማሮዴክ፡በነገሠ፡በአንደኛው፡ዓመት፡ የይሁዳን፡ንጉሥ፡የዮአኪንን፡ራስ፡ከፍ፡ከፍ፡አደረገ፡ከወህኒም፡አወጣው፤

32በመልካምም፡ተናገረው፥ዙፋኑንም፡ከርሱ፡ጋራ፡በባቢሎን፡ከነበሩት፡ነገሥታት፡ዙፋን፡በላይ፡አደረገለት።

33በወህኒም፡ውስጥ፡ለብሶት፡የነበረውን፡ልብስ፡ለወጠለት፥ዮአኪንም፡በሕይወቱ፡ዘመን፡ዅሉ፡በፊቴ፡ ዅልጊዜ፡እንጀራ፡ይበላ፡ነበር።

34የባቢሎንም፡ንጉሥ፡በሕይወቱ፡ዘመን፡ዅሉ፡እስኪሞት፡ድረስ፡የዘወትር፡ቀለብ፡ዕለት፡ዕለት፡ይሰጠው፡ ነበር፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source