1እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በባቢሎን፡ላይና፡በከለዳውያን፡ምድር፡በሚኖሩት፡ላይ፡አጥፊውን፡ ነፋስ፡አስነሣለኹ።
2በባቢሎንም፡ላይ፡የሚያዘሩትን፡ሰዎች፡እሰዳ፟ለኹ፤እነርሱም፡ያዘሯታል፥ምድሯንም፡ባዶ፡ ያደርጋሉ፤በመከራም፡ቀን፡በዙሪያዋ፡ይከቧ፟ታል።
3በወርዋሪው፡ላይ፡በጥሩርም፡በሚነሣው፡ላይ፡ቀስተኛው፡ቀስቱን፡ይገትር፤ለጐበዛዝቷ፡አትዘኑ፡ ሰራዊቷንም፡ዅሉ፡አጥፉ።
4በከለዳውያንም፡ምድር፡ተገድለው፥በሜዳዋም፡ላይ፡ተወግተው፡ይወድቃሉ።
5ምድራቸው፡በእስራኤል፡ቅዱስ፡ላይ፡በተሠራው፡በደል፡ምንም፡እንኳ፡የተሞላች፡ብትኾን፥እስራኤልም፡ ኾነ፡ይሁዳ፡በአምላኩ፡በሰራዊት፡ጌታ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡አልተጣለም።
6ከባቢሎን፡ውስጥ፡ሽሹ፥እያንዳንዳችኹም፡ነፍሳችኹን፡አድኑ፤በበደሏ፡አትጥፉ፥የእግዚአብሔር፡በቀል፡ ጊዜ፡ነውና፥ርሱም፡ብድራቷን፡ይከፍላታልና። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
7ባቢሎን፡በእግዚአብሔር፡እጅ፡ውስጥ፡ምድርን፡ዅሉ፡ያሰከረች፡የወርቅ፡ጽዋ፡ነበረች፥አሕዛብም፡ከጠጇ፡ ጠጥተዋል፤ስለዚህ፥አሕዛብ፡አብደዋል።
8ባቢሎን፡በድንገት፡ወድቃ፡ጠፍታለች፤አልቅሱላት፥ትፈወስም፡እንደ፡ኾነ፡ለቍስሏ፡መድኀኒት፡ ውሰዱላት።
9ባቢሎንን፡ፈወስናት፥ርሷ፡ግን፡አልተፈወሰችም፤ፍርዷ፡እስከ፡ሰማይ፡ደርሷልና፥እስከ፡ደመናም፡ድረስ፡ ከፍ፡ከፍ፡ብሏልና፥ትታችዃት፡እያንዳንዳችን፡ወደ፡አገራችን፡እንኺድ።
10እግዚአብሔር፡ጽድቃችንን፡አውጥቷል፤ኑ፥በጽዮን፡የአምላካችንን፡የእግዚአብሔርን፡ሥራ፡እንናገር።
11ፍላጻዎችን፡ሳሉ፡ጋሻዎችንም፡አዘጋጁ፤እግዚአብሔር፡ያጠፋት፡ዘንድ፡ዐሳቡ፡በባቢሎን፡ላይ፡ ነውና፥የሜዶንን፡ነገሥታት፡መንፈስ፡አስነሥቷል፤የእግዚአብሔር፡በቀል፡የመቅደሱ፡በቀል፡ነውና።
12በባቢሎን፡ቅጥር፡ዐላማውን፡አንሡበት፥ጥበቃን፡አጽኑ፥ተመልካቾችን፡አቁሙ፥ድብቅ፡ጦር፡ አዘጋጁ።እግዚአብሔር፡በባቢሎን፡በሚኖሩት፡ላይ፡የተናገረውን፡ዐስቧልና፥አድርጓልምና።
13አንቺ፡በብዙ፡ውሃ፡አጠገብ፡የተቀመጥሽ፥በመዝገብም፡የበለጠግሽ፡ሆይ፥እንደ፡ሥሥትሽ፡መጠን፡ ፍጻሜሽ፡ደርሷል።
14የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ሲል፡በራሱ፡ምሏል፦በእውነት፡ሰዎችን፡እንደ፡አንበጣ፡ እሞላብሻለኹ፥እነርሱም፡ጩኸት፡ያነሡብሻል።
15ምድርን፡በኀይሉ፡የፈጠረ፥ዓለሙን፡በጥበቡ፡የመሠረተ፥ሰማያትንም፡በማስተዋሉ፡የዘረጋ፡ርሱ፡ነው።
16ድምፁን፡ባሰማ፡ጊዜ፡ውሃዎች፡በሰማይ፡ይታወካሉ፥ከምድርም፡ዳር፡ደመናትን፡ከፍ፡ ያደርጋል፤ለዝናብም፡መብረቅን፡ያደርጋል፥ነፍስንም፡ከቤተ፡መዛግብቱ፡ያወጣል።
17ሰው፡ዅሉ፡ዕውቀት፡ዐጥቶ፡ሰንፏል፥አንጥረኛም፡ዅሉ፡ከቀረጸው፡ምስል፡የተነሣ፡አፍሯል፤ቀልጦ፡ የተሠራ፡ምስሉ፡ውሸት፡ነውና፥እስትንፋስም፡የላቸውምና።
18እነርሱም፡ምናምንቴና፡የቀልድ፡ሥራ፡ናቸው፤በተጐበኙ፡ጊዜ፡ይጠፋሉ።
19የያዕቆብ፡ዕድል፡ፈንታ፡እንደ፡እነዚህ፡አይደለም፥ርሱ፡የዅሉ፡ፈጣሪ፡ነውና፤እስራኤልም፡የርስቱ፡ ነገድ፡ነው፥ስሙም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ነው።
20አንቺ፡መዶሻዬና፡የጦር፡መሣሪያዬ፡ነሽ፤ባንቺ፡አሕዛብን፡እሰባብራለኹ፤ባንቺም፡መንግሥታትን፡ አጠፋለኹ፤
21ባንቺ፡ፈረሱንና፡ፈረሰኛውን፡እሰባብራለኹ፤
22ባንቺም፡ሠረገላውንና፡በላዩ፡የሚቀመጠውን፡እሰባብራለኹ፤ባንቺም፡ወንድንና፡ሴትን፡ እሰባብራለኹ፤ባንቺም፡ሽማግሌውንና፡ብላቴናውን፡እሰባብራለኹ፤ባንቺም፡ጕልማሳውንና፡ቈንዦዪቱን፡ እሰባብራለኹ፤
23ባንቺም፡እረኛውንና፡መንጋውን፡እሰባብራለኹ፤ባንቺም፡አራሹንና፡ጥማጁን፡እሰባብራለኹ፤ባንቺም፡ አለቃዎችንና፡ሹማምቶችን፡እሰባብራለኹ።
24በጽዮን፡በዐይናችኹ፡ፊት፡ስለሠሩት፡ክፋታቸው፡ዅሉ፡በባቢሎንና፡በከለዳውያን፡ምድር፡በሚኖሩ፡ዅሉ፡ ላይ፡ፍዳቸውን፡እከፍላለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
25አንተ፡ምድርን፡ዅሉ፡የምታጠፋ፡አጥፊ፡ተራራ፡ሆይ፥እንሆ፥እኔ፡ባንተ፡ላይ፡ነኝ፥ይላል፡ እግዚአብሔር፤እጄንም፡እዘረጋብኻለኹ፥ከድንጋዮችም፡ላይ፡አንከባልልኻለኹ፥የተቃጠለም፡ተራራ፡ አደርግኻለኹ።
26ከአንተም፡ለማእዘንና፡ለመሠረት፡የሚኾን፡ድንጋይ፡አይወስዱም፥ለዘለዓለምም፡ባድማ፡ትኾናለኽ፥ይላል፡ እግዚአብሔር። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
27በምድር፡ላይ፡ዐላማን፡አንሡ፡በአሕዛብም፡መካከል፡መለከት፡ንፉ፥አሕዛብንም፡ አዘጋጁባት፤የአራራትንና፡የሚኒን፡የአስከናዝንም፡መንግሥታት፡ሰብስቡባት፡አለቃንም፡በላይዋ፡አቁሙ፤እንደ፡ ጠጕራም፡ኵብኵባ፡ፈረሶችን፡በላይዋ፡አውጡ።
28አሕዛብን፡የሚዶንንም፡ነገሥታት፡አለቃዎችንም፡ሹማምቶችንም፡ዅሉ፡የግዛታቸውንም፡ምድር፡ዅሉ፡ አዘጋጁባት።
29ማንም፡እንዳይቀመጥባት፡የባቢሎንን፡ምድር፡ባድማ፡ያደርጋት፡ዘንድ፡የእግዚአብሔር፡ዐሳብ፡በባቢሎን፡ ላይ፡ጸንቷልና፥ምድር፡ተናውጣለች፡ታመመችም።
30የባቢሎን፡ኀያላን፡መዋጋትን፡ትተዋል፡በዐምባዎቻቸውም፡ውስጥ፡ተቀምጠዋል፤ኀይላቸውም፡ጠፍቷል፡ እንደ፡ሴቶችም፡ኾነዋል፤ማደሪያዎቿም፡ነደ፟ዋል፡መወርወሪያዎቿም፡ተሰብረዋል። 31-
32ከዳር፡እስከ፡ዳር፡ድረስ፡ከተማው፡እንደ፡ተያዘች፡መልካሞቿም፡እንደ፡ተያዙ፥ቅጥሯም፡በእሳት፡ እንደ፡ተቃጠለ፥ሰልፈኛዎችም፡እንደ፡ደነገጡ፡ለባቢሎን፡ንጉሥ፡ይነግር፡ዘንድ፡ወሬኛው፡ወሬኛውን፡ መልእክተኛውም፡መልእክተኛውን፡ሊገናኝ፡ይሮጣል።
33የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ዐውድማ፡እንደ፡ተረገጠ፡ ጊዜ፥እንዲሁ፡የባቢሎን፡ልጅ፡ናት፤ጥቂት፡ቈይታ፡የመከር፡ጊዜ፡ይደርስባታል።
34የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡በላኝ፥ከፋፈለኝም፥እንደ፡ባዶ፡ዕቃም፡አደረገኝ፥እንደ፡ዘንዶም፡ ዋጠኝ፥ከሚጣፍጠውም፡ምግቤ፡ሆዱን፡ሞላ፥እኔንም፡ጣለኝ።
35በጽዮን፡የምትቀመጥ፦በእኔና፡በሥጋዬ፡የተደረገ፡ግፍ፡በባቢሎን፡ላይ፡ይኹን፡ ትላለች፤ኢየሩሳሌምም፦ደሜ፡በከለዳውያን፡ምድር፡በሚኖሩት፡ላይ፡ይኹን፡ትላለች።
36ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥እሟገትልሻለኹ፡በቀልሽንም፡እበቀልልሻለኹ፤ባሕሯንም፡ ድርቅ፡አደርገዋለኹ፡ምንጯንም፡አደርቀዋለኹ።
37ባቢሎንም፡የድንጋይ፡ቍልልና፡የቀበሮ፡ማደሪያ፡መደነቂያም፡ማፏጫም፡ትኾናለች፥የሚቀመጥባትም፡ ሰው፡አይገኝም።
38በአንድነትም፡እንደ፡አንበሳዎች፡ያገሣሉ፥እንደ፡አንበሳም፡ደቦሎች፡ያጕረመርማሉ።
39በሞቃቸው፡ጊዜ፡ደስ፡እንዲላቸው፡ለዘለዓለምም፡አንቀላፍተው፡እንዳይነቁ፡የመጠጥ፡ግብዣ፡ አደርግላቸዋለኹ፡አሰክራቸውማለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
40እንደ፡ጠቦቶችና፡እንደ፡አውራ፡በጎች፡እንደ፡አውራ፡ፍየሎችም፡ወደ፡መታረድ፡አወርዳቸዋለኹ።
41ሼሻክ፡እንዴት፡ተያዘች! የምድርም፡ዅሉ፡ምስጋና፡እንዴት፡ተወሰደች! ባቢሎንም፡በአሕዛብ፡መካከል፡ መደነቂያ፡እንዴት፡ኾነች!
42ባሕር፡በባቢሎን፡ላይ፡ወጣ፡በሞገዱም፡ብዛት፡ተከደነች።
43ከተማዎቿ፡ባድማና፡ደረቅ፡ምድር፡ምድረ፡በዳም፥ሰውም፡የማይቀመጥበት፡የሰውም፡ልጅ፡የማያልፍበት፡ ምድር፡ኾኑ።
44በባቢሎንም፡ውስጥ፡ቤልን፡እቀጣለኹ፡የዋጠውንም፡ከአፉ፡አስተፋዋለኹ፤አሕዛብም፡ከዚያ፡ወዲያ፡ ወደ፡ርሱ፡አይሰበሰቡም፥የባቢሎንም፡ቅጥር፡ይወድቃል።
45ሕዝቤ፡ሆይ፥ከመካከሏ፡ውጡ፡እያንዳንዳችኹም፡ከእግዚአብሔር፡ጽኑ፡ቍጣ፡ራሳችኹን፡አድኑ።
46በምድርም፡ከሚሰማ፡ወሬ፡የተነሣ፡አትፍሩ፡ልባችኹም፡የዛለ፡አይኹን፤ባንድ፡ዓመት፡ወሬ፡ ይመጣል፥ከዚያም፡በዃላ፡በሌላው፡ዓመት፡ወሬ፥በምድርም፡ላይ፡ግፍ፡ይመጣል፥አለቃም፡በአለቃ፡ላይ፡ ይነሣል።
47ስለዚህ፥እንሆ፥የተቀረጹትን፡የባቢሎን፡ምስሎች፡የምቀጣበት፡ዘመን፡ይመጣል፥ምድሯም፡ዅሉ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ታፍራለች፤ተወግተውም፡የሞቱት፡ዅሉ፡በመካከሏ፡ይወድቃሉ።
48አጥፊዎች፡ከሰሜን፡ይመጡባታልና፥ሰማይና፡ምድር፡በእነርሱም፡ያለው፡ዅሉ፡ስለ፡ባቢሎን፡እልል፡ ይላሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
49ባቢሎንም፡ከእስራኤል፡ተወግተው፡የሞቱት፡እንዲወድቁ፡እንዳደረገች፥እንዲሁ፡በባቢሎን፡ከምድሩ፡ ዅሉ፡ተወግተው፡የሞቱት፡ይወድቃሉ።
50ከሰይፍ፡ያመለጣችኹ፡ሆይ፥ኺዱ፥አትቁሙ፤እግዚአብሔርን፡ከሩቅ፡ዐስቡ፥ኢየሩሳሌምንም፡በልባችኹ፡ ዐስቡ።
51ስድብን፡ስለ፡ሰማን፡ዐፍረናል፤ባዕዳን፡ሰዎችም፡ወደእግዚአብሔር፡ቤተ፡መቅደስ፡ገብተዋልና፥ነውር፡ ፊታችንን፡ከድኖታል።
52ስለዚህ፥እንሆ፥የተቀረጹትን፡ምስሎቿ፡የምቀጣበት፡ዘመን፡ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር፡በምድሯም፡ ላይ፡ዅሉ፡የተወጉት፡ያንቋርራሉ።
53ባቢሎን፡ምንም፡ወደ፡ሰማይ፡ብትወጣ፥የኀይሏንም፡ከፍታ፡ብታጸና፥ከእኔ፡ዘንድ፡አጥፊዎች፡ ይመጡባታል፥ይላል፡እግዚአብሔር።
54ከባቢሎን፡ጩኸት፥ከከለዳውያንም፡ምድር፡የታላቅ፡ጥፋት፡ድምፅ፡ተሰምቷል።
55እግዚአብሔር፡ባቢሎንን፡አጥፍቷታልና፥ከርሷም፡ታላቁን፡ድምፅ፡ዝም፡አሠኝቷልና፤ሞገዳቸውም፡እንደ፡ ብዙ፡ውሃዎች፡ይተማ፟ል፥የድምፃቸውም፡ጩኸት፡ተሰምቷል።
56አጥፊው፡በባቢሎን፡ላይ፡መጥቶባታልና፥ኀያላኗ፡ተያዙ፥ቀስታቸውም፡ተሰባበረ፤እግዚአብሔር፡ፍዳን፡ የሚከፍል፡አምላክ፡ነውና፥ፍዳንም፡በርግጥ፡ይከፍላል።
57መሳፍንቷንና፡ጥበበኛዎቿንም፥አለቃዎቿንና፡ሹማምቷን፡ኀያላኗንም፡አሰክራለኹ፥ለዘለዓለምም፡ አንቀላፍተው፡አይነቁም፥ይላል፡ስሙ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡የተባለው፡ንጉሥ።
58የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሰፊው፡የባቢሎን፡ቅጥር፡ፈጽሞ፡ይፈርሳል፡ ረዣዥሞችም፡በሮቿ፡በእሳት፡ይቃጠላሉ፤የወገኖችም፡ድካም፡ከንቱ፡ትኾናለች፥የአሕዛብም፡ሥራ፡ለእሳት፡ ትኾናለች፤እነርሱም፡ይደክማሉ።
59የመሕሤያ፡ልጅ፡የኔርያ፡ልጅ፡ሰራያ፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሴዴቅያስ፡በነገሠ፡በአራተኛው፡ዓመት፡ከርሱ፡ ጋራ፡ወደ፡ባቢሎን፡በኼደ፡ጊዜ፡ነቢዩ፡ኤርምያስ፡ያዘዘው፡ቃል፡ይህ፡ነው።ሰራያም፡የቤት፡አዛዥ፡ነበረ።
60በባቢሎንም፡ላይ፡የሚመጣውን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፥ስለ፡ባቢሎን፡የተጻፈውን፡ይህን፡ቃል፡ ዅሉ፥ኤርምያስ፡በመጽሐፍ፡ላይ፡ጻፈው።
61ኤርምያስም፡ሰራያን፡እንዲህ፡አለው፦ወደ፡ባቢሎን፡በገባኽ፡ጊዜ፡እይ፥ይህንም፡ቃል፡ዅሉ፡አንብ፟ና፦
62አቤቱ፥ከሰው፡ዠምሮ፡እስከ፡እንስሳ፡ድረስ፡ማንም፡እንዳይቀመጥባት፥ለዘለዓለምም፡ባድማ፡እንድትኾን፡ ታጠፋት፡ዘንድ፡በዚች፡ስፍራ፡ላይ፡ተናግረኻል፡በል።
63ይህንም፡መጽሐፍ፡ማንበብ፡ከፈጸምኽ፡በዃላ፥ድንጋይን፡እሰርበት፡በኤፍራጥስም፡ውስጥ፡ጣለው፤
64አንተም፦እኔ፡ከማመጣባት፡ክፉ፡ነገር፡የተነሣ፡እንዲሁ፡ባቢሎን፡ትሰጥማለች፡አትነሣምም፡ በል።የኤርምያስ፡ቃል፡እስከዚህ፡ድረስ፡ነው።