Skip to content
← Jeremiah

Chapter 50 · Amharic

Jeremiah

1እግዚአብሔር፡ስለከለዳውያን፡ምድር፡ስለ፡ባቢሎን፡በነቢዩ፡በኤርምያስ፡የተናገረው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦

2በአሕዛብ፡መካከል፡ተናገሩ፡አውሩም፥ዐላማውንም፡አንሡ፤አውሩ፥አትደብቁ።ባቢሎን፡ተወሰደች፥ቤል፡ ዐፈረ፥ሜሮዳክ፡ደነገጠ፤ምስሎቿ፡ዐፈሩ፥ጣዖታቷ፡ደነገጡ፡በሉ።

3ሕዝብ፡ከሰሜን፡ወጥቶባታል፡ምድሯንም፡ባድማ፡ያደርጋል፥የሚቀመጥባትም፡አይገኝም፤ከሰው፡ዠምሮ፡ እስከ፡እንስሳ፡ድረስ፡ሸሽተው፡ኼደዋል።

4በዚያም፡ወራት፡በዚያም፡ጊዜ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥የእስራኤል፡ልጆችና፡የይሁዳ፡ልጆች፡በአንድነት፡ ኾነው፡ይመጣሉ፥እያለቀሱም፡መንገዳቸውን፡ይኼዳሉ፥አምላካቸውንም፡እግዚአብሔርን፡ይፈልጋሉ።

5ፊታቸውንም፡ወደዚያ፡አቅንተው፦ኑ፥ከቶ፡በማይረሳ፡በዘለዓለም፡ቃል፡ኪዳን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ ተጠጉ፡ብለው፡ስለ፡ጽዮን፡መንገድ፡ይጠይቃሉ።

6ሕዝቤ፡የጠፉ፡በጎች፡ኾነዋል፤እረኛዎቻቸው፡አሳቷቸው፥በተራራዎችም፡ላይ፡የተቅበዘበዙ፡ አደረጓቸው፤ከተራራ፡ወደ፡ኰረብታ፡ዐለፉ፥በረታቸውንም፡ረሱ።

7ያገኟቸው፡ዅሉ፡በሏቸው፥ጠላቶቻቸውም፦በጽድቅ፡ማደሪያ፡በእግዚአብሔር፡ላይ፥በአባቶቻቸው፡ተስፋ፡ በእግዚአብሔር፡ላይ፡ኀጢአት፡ስለ፡ሠሩ፡እኛ፡አልበደልንም፡አሉ።

8ከባቢሎን፡መካከል፡ሽሹ፥ከከለዳውያንም፡ድር፡ውጡ፥በመንጋዎችም፡ፊት፡እንደ፡አውራ፡ፍየሎች፡ ኹኑ።

9እንሆ፥ከሰሜን፡ምድር፡የታላላቅ፡አሕዛብን፡ጉባኤ፡አስነሣለኹ፡በባቢሎንም፡ላይ፡ አመጣቸዋለኹ፤በርሷም፡ላይ፡ይሰለፋሉ፥ከዚያም፡ትወሰዳለች፤ፍላጻዎቻቸውም፡ባዶውን፡እንደማይመለስ፡ እንደ፡ብልኅ፡ዠግና፡ፍላጻ፡ናቸው።

10የከላውዴዎንም፡ምድር፡ትበዘበዛለች፥የሚበዘብዟትም፡ዅሉ፡ይጠግባሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

11ርስቴን፡የምትበዘብዙ፡እናንተ፡ሆይ፥ደስ፡ብሏችዃልና፥ሐሤትንም፡አድርጋችዃልና፥በመስክ፡ላይም፡ እንዳለች፡ጊደር፡ኾናችኹ፡ተቀናጥታችዃልና፥እንደ፡ብርቱዎችም፡ፈረሶች፡አሽካክታችዃልና፥

12እናታችኹ፡እጅግ፡ታፍራለች፥የወለደቻችኹም፡ትጐሰቍላለች፤እንሆ፥በአሕዛብ፡መካከል፡ዃለኛዪቱ፡ ትኾናለች፤ምድረ፡በዳና፡ደረቅ፡ምድር፡በረሓም፡ትኾናለች።

13ከእግዚአብሔር፡ቍጣ፡የተነሣ፡ባድማ፡ትኾናለች፡እንጂ፡ሰው፡አይቀመጥባትም፤በባቢሎንም፡በኩል፡ የሚያልፍ፡ዅሉ፡ይደነቃል፡በመጣባትም፡መቅሠፍት፡ዅሉ፡ያፏጫል።

14እናንተ፡ቀስትን፡የምትገትሩ፡ሰዎች፡ዅሉ፥በባቢሎን፡ላይ፡በዙሪያዋ፡ተሰለፉ፤በእግዚአብሔር፡ላይ፡ ኀጢአት፡ሠርታለችና፡ወርውሩባት፡ፍላጻዎችንም፡አትንፈጉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

15የእግዚአብሔር፡በቀል፡ነውና፥በዙሪያዋ፡ጩኹባት፤እጇን፡ሰጠች፤ግንቦቿ፡ወደቁ፡ቅጥሮቿም፡ ፈረሱ፤ርሷን፡ተበቀሉ፡እንደ፡ሠራችውም፡ሥሩባት።

16ዘሪውንና፡በመከር፡ጊዜ፡ማጭድ፡የሚይዘውን፡ከባቢሎን፡አጥፉ፤ከሚያስጨንቅ፡ሰይፍ፡ፊት፡እያንዳንዱ፡ ወደ፡ወገኑ፡ይመለሳል፡እያንዳንዱም፡ወደ፡አገሩ፡ይሸሻል።

17እስራኤል፡የባዘነ፡በግ፡ነው፤አንበሳዎች፡አሳደዱት፤መዠመሪያ፡የአሶር፡ንጉሥ፡በላው፥በመጨረሻም፡ የባቢሎን፡ንጉሥ፡ናቡከደነጾር፡ዐጥንቱን፡ቈረጠመው።

18ስለዚህ፥የእስራኤል፡አምላክ፣የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የአሶርን፡ንጉሥ፡እንደ፡ ቀጣኹ፡እንዲሁ፥እንሆ፥የባቢሎንን፡ንጉሥና፡ምድሩን፡እቀጣለኹ።

19እስራኤልንም፡ወደ፡ማሰማሪያው፡እመልሳለኹ፥በቀርሜሎስና፡በባሳንም፡ላይ፡ይሰማራል፥ሰውነቱም፡ በኤፍሬም፡ተራራና፡በገለዓድ፡ላይ፡ትጠግባለች።

20እነዚህን፡ያስቀረዃቸውን፡ይቅር፡እላቸዋለኹና፡በዚያን፡ወራት፡በዚያም፡ዘመን፥ይላል፡ እግዚአብሔር፥የእስራኤል፡በደል፡የይሁዳም፡ኀጢአት፡ይፈለጋል፡ምንም፡አይገኝም።

21በምራታይም፡ምድር፡ላይ፡በፋቁድም፡በሚኖሩት፡ላይ፡ውጣ፤ግደላቸው፡ፈጽመኽም፡አጥፋቸው፥ይላል፡ እግዚአብሔር፥እንዳዘዝኹኽም፡ዅሉ፡አድርግ።

22የሰልፍና፡የታላቅ፡ጥፋት፡ውካታ፡በምድር፡ላይ፡አለ።

23የምድር፡ዅሉ፡መዶሻ፡እንዴት፡ደቀቀ፥እንዴትስ፡ተሰበረ! ባቢሎንስ፡በአሕዛብ፡መካከል፡እንዴት፡ ባድማ፡ኾነች!

24ባቢሎን፡ሆይ፥አጥምጄብሻለኹ፥አንቺም፡ሳታውቂ፡ተይዘሻል፤ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡ስለ፡ተዋጋሽ፡ ተገኝተሻል፥ተይዘሽማል።

25የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡በከለዳውያን፡ምድር፡ይሠራ፡ዘንድ፡ሥራ፡አለውና፥እግዚአብሔር፡ዕቃ፡ ቤቱን፡ከፍቶ፡የቍጣውን፡ዕቃ፡ጦር፡አውጥቷል።

26ከየበኩሉ፡በርሷ፡ላይ፡ውጡ፥ጐተራዎቿንም፡ክፈቱ፤እንደ፡ክምርም፡አድርጓት፥ፈጽማችኹም፡ አጥፏት፥አንዳችም፡አታስቀሩላት።

27ወይፈኖቿን፡ዅሉ፡ዕረዱ፥ወደ፡መታረድም፡ይውረዱ፤ቀናቸው፣የመጐብኘታቸው፡ጊዜ፡ ደርሷልና፥ወዮላቸው!

28የአምላካችንን፡የእግዚአብሔርን፡በቀል፡የመቅደሱንም፡በቀል፡በጽዮን፡ይነግሩ፡ዘንድ፥ሸሽተው፡ ከባቢሎን፡አገር፡ያመለጡት፡ሰዎች፡ድምፅ፡ተሰምቷል።

29ቀስትን፡የሚገትሩትን፡ቀስተኛዎችን፡ዅሉ፡በባቢሎን፡ላይ፡ጥሯቸው፤በዙሪያዋ፡ስፈሩባት፡አንድም፡ አያምልጥ፤በእስራኤል፡ቅዱስ፡ላይ፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ኰርታለችና፥እንደ፡ሥራዋ፡መጠን፡ መልሱላት፥እንዳደረገችም፡ዅሉ፡አድርጉባት።

30ስለዚህ፥ጐበዛዝቷ፡በአደባባይዋ፡ላይ፡ይወድቃሉ፥በዚያም፡ቀን፡ሰልፈኛዎቿ፡ዅሉ፡ይጠፋሉ፥ይላል፡ እግዚአብሔር።

31ትዕቢተኛው፡ሆይ፥የመጐብኘትኽ፡ጊዜ፥ቀንኽ፡ደርሷልና፥እንሆ፥ባንተ፡ላይ፡ነኝ፥ይላል፡የሰራዊት፡ ጌታ፡እግዚአብሔር።

32ትዕቢተኛው፡ተሰናክሎ፡ይወድቃል፡የሚያነሣውም፡የለም፤በከተማዎቹም፡ውስጥ፡እሳት፡ አነዳ፟ለኹ፥በዙሪያውም፡ያለውን፡ዅሉ፡ትበላለች።

33የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የእስራኤል፡ልጆችና፡የይሁዳ፡ልጆች፡በአንድነት፡ ተገፍተዋል፥የማረኳቸውም፡ዅሉ፡በኀይል፡ይይዟቸዋል፥ይለቋ፟ቸውም፡ዘንድ፡እንቢ፡ብለዋል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

34ተቤዢያቸው፡ብርቱ፡ነው፥ስሙም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ነው፤ምድርንም፡ያሳርፍ፡ ዘንድ፥በባቢሎንም፡የሚኖሩትን፡ያውክ፡ዘንድ፥ሙግታቸውን፡ፈጽሞ፡ይሟገታል።

35ሰይፍ፡በከለዳውያንና፡በባቢሎን፡በሚኖሩ፡ላይ፥በአለቃዎቿና፡በጥበበኛዎቿ፡ላይ፡አለ፥ይላል፡ እግዚአብሔር።

36ሰይፍ፡በሚጓደዱት፡ላይ፡አለ፡ሰነፎችም፡ይኾናሉ፥ሰይፍም፡በኀያላኗ፡ላይ፡አለ፡እነርሱም፡ይደነግጣሉ።

37ሰይፍ፡በፈረሶቻቸውና፡በሠረገላዎቻቸው፡ላይ፡በመካከሏም፡ባሉት፡በልዩ፡በልዩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ላይ፡ አለ፥እነርሱም፡እንደ፡ሴቶች፡ይኾናሉ፤ሰይፍም፡በመዝገቧ፡ላይ፡አለ፡ለብዝበዛም፡ይኾናል።

38ርሷ፡የተቀረጹ፡ምስሎች፡ምድር፡ናት፥እነርሱም፡በጣዖታት፡ይመካሉና፥ድርቅ፡በውሃዎቿ፡ላይ፡ ይኾናል፥እነርሱም፡ይደርቃሉ።

39ስለዚህ፥የምድረ፡በዳ፡አራዊት፡ከተኵላዎች፡ጋራ፡ይቀመጡባታል፥ሰጐኖችም፡ይቀመጡባታል፤ሰውም፡ ከዚያ፡ወዲያ፡ለዘለዓለም፡አይቀመጥባትም፥እስከልጅ፡ልጅም፡ድረስ፡የሚኖርባት፡የለም።

40ሰዶምንና፡ገሞራን፡በአጠገባቸውም፡የነበሩትን፡ከከተማዎች፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ገለበጣቸው፥ይላል፡ እግዚአብሔር፥እንዲሁ፡ሰው፡በዚያ፡አይቀመጥም፡የሰውም፡ልጅ፡አይኖርባትም።

41እንሆ፥ሕዝብ፡ከሰሜን፡ይመጣል፤ታላቅ፡ሕዝብና፡ብዙ፡ነገሥታትም፡ከምድር፡ዳርቻ፡ይነሣሉ።

42ቀስትንና፡ጦርን፡ይይዛሉ፤ጨካኞች፡ናቸው፥ምሕረትም፡አያደርጉም፤ድምፃቸው፡እንደ፡ባሕር፡ ይተማ፟ል፥በፈረሶችም፡ላይ፡ይቀመጣሉ።የባቢሎን፡ሴት፡ልጅ፡ሆይ፥ለሰልፍ፡እንደ፡ተዘጋጀ፡ሰው፡ እያንዳንዳቸው፡ባንቺ፡ላይ፡ተሰለፉ።

43የባቢሎን፡ንጉሥ፡ወሬያቸውን፡ሰምቷል፥እጁም፡ደክማለች፥ጭንቀትም፡ይዞታል፥ምጥ፡ወላድ፡ሴትን፡ እንደሚይዛት፡ጭንቀት፡ይዞታል።

44እንሆ፥ከርሷ፡ዘንድ፡በቶሎ፡አባርራቸዋለኹና፥በጠነከረው፡ዐምባ፡ላይ፡ከዮርዳኖስ፡ትዕቢት፡ውስጥ፡ እንደ፡አንበሳ፡ይወጣል፤የተመረጠውንም፡በርሷ፡ላይ፡እሾመዋለኹ፤እንደ፡እኔ፡ያለ፡ማን፡ነው፧ወይስ፡ ለእኔ፡ጊዜ፡የሚወስን፡ማን፡ነው፧ወይስ፡ፊቴን፡የሚቃወም፡እረኛ፡ማን፡ነው፧

45ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡በባቢሎን፡ላይ፡የመከረባትን፡ምክር፥በከለዳውያንም፡ምድር፡ላይ፡ያሰባትን፡ ዐሳብ፡ስሙ፤በእውነት፡የመንጋ፡ትናንሾች፡ይጐተታሉ፤በእውነት፡ማደሪያቸውን፡ባድማ፡ያደርግባቸዋል።

46ከባቢሎን፡መያዝ፡ድምፅ፡የተነሣ፡ምድር፡ተናወጠች፥ጩኸትም፡በአሕዛብ፡መካከል፡ዘንድ፡ተሰማ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source