Skip to content
← Job

Chapter 42 · Amharic

Job

1ኢዮብም፡መለሰ፡እግዚአብሔርንም፡እንዲህ፡አለው፦

2ዅሉን፡ታደርግ፡ዘንድ፡ቻይ፡እንደ፡ኾንኽ፥ ዐሳብኽም፡ይከለከል፡ዘንድ፡ከቶ፡እንደማይቻል፡ዐወቅኹ።

3ያለዕውቀት፡ምክርን፡የሚሰውር፡ማን፡ነው፧ ስለዚህ፡እኔ፡የማላስተውለውን፥ የማላውቀውንም፡ድንቅ፡ነገር፡ተናግሬያለኹ።

4እባክኽ፥ስማኝ፡እኔም፡ልናገር፤ እጠይቅኽማለኹ፥አንተም፡ተናገረኝ።

5መስማትንስ፡በዦሮ፡በመስማት፡ሰምቼ፡ነበር፤ አኹን፡ግን፡ዐይኔ፡አየችኽ፤

6ስለዚህ፥ራሴን፡እንቃለኹ፤ በዐፈርና፡በዐመድ፡ላይ፡ተቀምጬ፡እጸጸታለኹ።

7እግዚአብሔርም፡ይህን፡ቃል፡ለኢዮብ፡ከተናገረ፡በዃላ፡እግዚአብሔር፡ቴማናዊውን፡ኤልፋዝን፦እንደ፡ ባሪያዬ፡እንደ፡ኢዮብ፡ቅንን፡ነገር፡ስለ፡እኔ፡አልተናገራችኹምና፡ቍጣዬ፡በአንተና፡በኹለቱ፡ባልንጀራዎችኽ፡ ላይ፡ነዷ፟ል።

8አኹን፡እንግዲህ፡ሰባት፡ወይፈኖችና፡ሰባት፡አውራ፡በጎች፡ይዛችኹ፡ወደ፡ባሪያዬ፡ወደ፡ኢዮብ፡ዘንድ፡ ኺዱ፥የሚቃጠልንም፡መሥዋዕት፡ስለ፡ራሳችኹ፡አሳርጉ፤ባሪያዬም፡ኢዮብ፡ስለ፡እናንተ፡ይጸልያል፥እኔም፡ እንደ፡ስንፍናችኹ፡እንዳላደርግባችኹ፡ፊቱን፡እቀበላለኹ፤እንደ፡ባሪያዬ፡እንደ፡ኢዮብ፡ቅን፡ነገር፡ስለ፡እኔ፡ አልተናገራችኹምና።

9ቴማናዊውም፡ኤልፋዝ፡ሹሐዊውም፡በልዳዶስ፡ናዕማታዊውም፡ሶፋር፡ኼደው፡እግዚአብሔር፡እንዳዘዛቸው፡ አደረጉ፡እግዚአብሔርም፡የኢዮብን፡ፊት፡ተቀበለ።

10ኢዮብም፡ስለ፡ወዳጆቹ፡በጸለየ፡ጊዜ፡እግዚአብሔርም፡ምርኮውን፡መለሰለት፤እግዚአብሔርም፡ቀድሞ፡ በነበረው፡ፋንታ፡ኹለት፡ዕጥፍ፡አድርጎ፡ለኢዮብ፡ሰጠው።

11ወንድሞቹና፡እኅቶቹ፡ቀድሞም፡ያውቁት፡የነበሩት፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡መጡ፥በቤቱም፡ከርሱ፡ጋራ፡ እንጀራ፡በሉ፤ስለ፡ርሱም፡ዐዘኑለት፥እግዚአብሔርም፡ካመጣበት፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡ አጽናኑት፤እያንዳንዳቸውም፡ብርና፡የወርቅ፡ቀለበት፡ሰጡት።

12እግዚአብሔርም፡ከፊተኛው፡ይልቅ፡የዃለኛውን፡ለኢዮብ፡ባረከ፤ዐሥራ፡አራት፡ሺሕም፡በጎች፥ስድስት፡ ሺሕም፡ግመሎች፥አንድ፡ሺሕም፡ጥማድ፡በሬዎች፥አንድ፡ሺሕም፡እንስት፡አህያዎች፡ነበሩት።

13ደግሞም፡ሰባት፡ወንዶችና፡ሦስት፡ሴቶች፡ልጆች፡ኾኑለት። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

14የመዠመሪያዪቱንም፡ስም፡ይሚማ፥የኹለተኛዪቱንም፡ስም፡ቃስያ፥የሦስተኛዪቱንም፡ስም፡አማልቶያስ፡ ቂራስ፡ብሎ፡ሰየማቸው።

15እንደ፡ኢዮብ፡ሴቶች፡ልጆችም፡ያሉ፡የተዋቡ፡ሴቶች፡በአገሩ፡ዅሉ፡አልተገኙም፤አባታቸውም፡ ከወንድሞቻቸው፡ጋራ፡ርስት፡ሰጣቸው።

16ከዚህም፡በዃላ፡ኢዮብ፡መቶ፡አርባ፡ዓመት፡ኖረ፥ልጆቹንና፡የልጅ፡ልጆቹንም፡እስከ፡አራት፡ትውልድ፡ ድረስ፡አየ።

17ኢዮብም፡ሸምግሎ፥ዕድሜም፡ጠግቦ፡ሞተ፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source