1እንሆ፥ተስፋው፡ከንቱ፡ነው፤ ያየው፡ዅሉ፡ስንኳ፡በፊቱ፡ይዋረዳል።
2ያንቀሳቅሰውም፡ዘንድ፡የሚደፍር፡የለም፤ እንግዲህ፡በፊቴ፡መቆም፡የሚችል፡ማን፡ነው፧
3እመልስለትስ፡ዘንድ፡መዠመሪያ፡የሰጠኝ፡ማን፡ነው፧ ከሰማይ፡ዅሉ፡በታች፡ያለው፡ገንዘቤ፡ነው።
4ስለ፡አካላቱና፡ስለ፡ብርቱ፡ኀይሉ፥ ስለ፡መልካም፡ሰውነቱ፡ዝም፡አልልም።
5የውጪ፡ልብሱን፡ማን፡ይገፋል፧ በጥንድ፡መንጋጋውስ፡ውስጥ፡ማን፡ይገባል፧
6የፊቱንስ፡ደጆች፡የሚከፍት፡ማን፡ነው፧ በጥርሶቹ፡ዙሪያ፡ግርማ፡አለ።
7ቅርፊቶቹ፡ጠንካራ፡ስለ፡ኾኑ፡ርሱ፡ትዕቢተኛ፡ነው፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org በጠባብ፡ማተሚያ፡እንደ፡ታተሙ፡ናቸው።
8ርስ፡በርሳቸው፡የተቀራረቡ፡ናቸውና፥ ነፋስ፡በመካከላቸው፡መግባት፡አይችልም።
9ርስ፡በርሳቸው፡የተገጣጠሙ፡ናቸው፤ እስከማይለያዩም፡ድረስ፡ተያይዘዋል።
10እንጥሽታው፡ብልጭታ፡ያወጣል፥ ዐይኖቹም፡እንደ፡ወገግታ፡ናቸው።
11ከአፉ፡ፋናዎች፡ይወጣሉ፥ የእሳትም፡ፍንጣሪ፡ይረጫል።
12እንደ፡ፈላ፡ድስትና፡እንደሚቃጠል፡ሸምበቆ፡ ከአንፍንጫው፡ጢስ፡ይወጣል።
13እስትንፋሱ፡ከሰልን፡ታቃጥላለች፥ ነበልባልም፡ከአፉ፡ይወጣል።
14በዐንገቱ፡ኀይል፡ታድራለች፤ ግርማ፡በፊቱ፡ይዘፍናል።
15የሥጋውም፡ቅርፊት፡የተጣበቀ፡ነው፤ እስከማይንቀሳቀሱም፡ድረስ፡በርሱ፡ላይ፡ጸንተዋል።
16ልቡ፡እንደ፡ድንጋይ፡የደነደነ፡ነው፤ እንደ፡ወፍጮ፡ድንጋይ፡የጸና፡ነው።
17በተነሣ፡ጊዜ፡ኀያላን፡ይፈራሉ፤ ከድንጋጤም፡የተነሣ፡ያብዳሉ።
18ሰይፍና፡ጦር፥ፍላጻና፡መውጊያም፡ቢያገኙት፡አያሸንፉትም።
19ብረትን፡እንደ፡ገለባ፥ ናስንም፡እንደ፡ነቀዘ፡ዕንጨት፡ይቈጥራቸዋል።
20ፍላጻ፡ሊያባርረው፡አይችልም፤ የወንጭፍም፡ድንጋዮች፡እንደ፡ገለባ፡ይኾኑለታል።
21በሎታውን፡እንደ፡ገለባ፡ይቈጥረዋል፤ ሠላጢኑም፡ሲሰበቅ፡ይሥቃል።
22ታቹ፡እንደ፡ስለታም፡ገል፡ነው፤ እንደ፡መዳመጫም፡በጭቃ፡ላይ፡ያልፋል።
23ቀላዩን፡እንደ፡ድስት፡ያፈላዋል፤ ባሕሩንም፡እንደ፡ሽቱ፡ምንቸት፡ያደርገዋል።
24በስተዃላው፡ብሩህ፡መንገድን፡ያበራል፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ቀላዩም፡ሽበት፡ይመስላል።
25ያለፍርሀት፡የተፈጠረ፥ እንደ፡ርሱ፡ያለ፡በምድር፡ላይ፡የለም።
26ከፍ፡ያለውን፡ዅሉ፡ይመለከታል፤ በትዕቢተኛዎችም፡ዅሉ፡ላይ፡ንጉሥ፡ነው።