1እግዚአብሔርም፡መለሰ፡ኢዮብንም፡እንዲህ፡አለው፦
2በእውኑ፡የሚከራከር፡ሰው፡ዅሉን፡ከሚችል፡አምላክ፡ጋራ፡ይከራከራልን፧ ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡የሚዋቀስ፡ርሱ፡ይመልስለት።
3ኢዮብም፡መለሰ፡እግዚአብሔርንም፡እንዲህ፡አለው፦
4እንሆ፥እኔ፡ወራዳ፡ሰው፡ነኝ፤የምመልስልኽ፡ምንድር፡ነው፧ እጄን፡በአፌ፡ላይ፡እጭናለኹ።
5አንድ፡ጊዜ፡ተናገርኹ፥አልመልስምም፤ ኹለተኛ፡ጊዜም፥ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አልናገርም።
6እግዚአብሔርም፡በዐውሎ፡ነፋስ፡ውስጥ፡ኾኖ፡ለኢዮብ፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦
7እንግዲህ፡እንደ፡ወንድ፡ወገብኽን፡ታጠቅ፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እጠይቅኻለኹ፥አንተም፡ተናገረኝ።
8በእውኑ፡ፍርዴን፡ታፈርሳለኽን፧ አንተስ፡ጻድቅ፡ትኾን፡ዘንድ፡በእኔ፡ትፈርዳለኽን፧
9እንደእግዚአብሔር፡ክንድ፡ያለ፡ክንድ፡አለኽን፧ ወይስ፡እንደ፡ርሱ፡ባለ፡ድምፅ፡ታንጐደጕዳለኽን፧
10በታላቅነትና፡በልዕልና፡ተላበስ፤ በክብርና፡በግርማም፡ተጐናጸፍ።
11የቍጣኽን፡ፈሳሽ፡አፍስ፟፤ ትዕቢተኛውንም፡ዅሉ፡ተመልክተኽ፡አዋርደው።
12ትዕቢተኛውንም፡ዅሉ፡ተመልከት፥ዝቅ፡ዝቅም፡አድርገው፤ በደለኛዎችንም፡ወዲያውኑ፡ርገጣቸው።
13በዐፈር፡ውስጥ፡በአንድነት፡ሰውራቸው፤ በተሸሸገም፡ስፍራ፡ፊታቸውን፡ሸፍን።
14በዚያን፡ጊዜም፡ቀኝ፡እጅኽ፡ታድንኽ፡ዘንድ፡እንድትችል፡ እኔ፡ደግሞ፡እመሰክርልኻለኹ።
15ከአንተ፡ጋራ፡የሠራኹትን፡ጕማሬ፥እስኪ፥ተመልከት፤ እንደ፡በሬ፡ሣር፡ይበላል።
16እንሆ፥ብርታቱ፡በወገቡ፡ውስጥ፡ነው፤ ኀይሉም፡በሆዱ፡ዥማት፡ውስጥ፡ነው።
17ዥራቱን፡እንደ፡ጥድ፡ዛፍ፡ያወዛውዛል፤ የወርቹ፡ዥማት፡የተጐነጐነ፡ነው።
18ዐጥንቱ፡እንደ፡ናስ፡አገዳ፡ነው፤ አካላቱ፡እንደ፡ብረት፡ዘንጎች፡ናቸው።
19ርሱ፡የእግዚአብሔር፡ፍጥረት፡አውራ፡ነው፤ ሠሪውም፡ሰይፉን፡ሰጠው።
20የሜዳ፡እንስሳዎች፡ዅሉ፡የሚጫወቱበት፡ተራራ፡ ምግብን፡ያበቅልለታል።
21ጥላ፡ካለው፡ዛፍ፡በታች፥ በደንገልና፡በረግረግ፡ውስጥ፡ይተኛል።
22ጥላ፡ያለው፡ዛፍ፡በጥላው፡ይሰውረዋል፤ የወንዝ፡አሓያ፡ዛፎች፡ይከቡ፟ታል።
23እንሆ፥ወንዙ፡ቢጐርፍ፡አይደነግጥም፤ ዮርዳኖስም፡እስከ፡አፉ፡ድረስ፡ቢፈስ፟፡ርሱ፡ይተማመናል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
24ዐይኖቹ፡እያዩ፡ይያዛልን፧ አፍንጫውስ፡በወጥመድ፡ይበሳልን፧
25በእውኑ፡አዞውን፡በመቃጥን፡ታወጣለኽን፧ ምላሱንስ፡በገመድ፡ታስረዋለኽን፧
26ወይስ፡ስናጋ፡በአፍንጫው፡ታደርጋለኽን፧ ወይስ፡በችንካር፡ጕንጩን፡ትበሳለኽን፧
27በእውኑ፡ወዳንተ፡እጅግ፡ይለምናልን፧ በጣፈጠስ፡ቃል፡ይናገርኻልን፧
28በእውኑ፡ከአንተ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡ይገባልን፧ ወይስ፡ለዘለዓለም፡ባሪያ፡ታደርገዋለኽን፧
29ከወፍ፡ጋራ፡እንደምትጫወት፡ከርሱ፡ጋራ፡ትጫወታለኽን፧ ወይስ፡ለሴት፡ባሪያዎችኽ፡ታስረዋለኽን፧
30አጥማጆች፡በርሱ፡ይከራከራሉን፧ ወይስ፡ነጋዴዎች፡ያካፍሉታልን፧
31በእውኑ፡ቍርበቱን፡በጭሬ፥ ራሱንስ፡በዓሣ፡ጦር፡ትሞላዋለኽን፧
32እጅኽን፡በላዩ፡ጫን፤ ሰልፉን፡ዐስብ፥እንግዲህም፡አትድገም።