1የበረሓ፡ፍየል፡የምትወልድበትን፡ጊዜ፡ታውቃለኽን፧ ዋላዪቱስ፡የምታምጥበትን፡ጊዜ፡ትመለከታለኽን፧
2ርሷ፡የምትፈጽመውንስ፡ወራት፡ትቈጥራለኽን፧ የምትወልድበትንስ፡ጊዜ፡ታውቃለኽን፧
3ይንበረከካሉ፥ልጆቻቸውንም፡ይወልዳሉ፥ ከምጣቸውም፡ያርፋሉ።
4ልጆቻቸው፡ይጠነክራሉ፥ በሜዳም፡ያድጋሉ፤ ይወጣሉ፥ወደ፡እነርሱም፡አይመለሱም።
5የሜዳውስ፡አህያ፡ሐራነት፡ማን፡አወጣው፧ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የበረሓውንስ፡አህያ፡ከእስራቱ፡ማን፡ፈታው፧
6በረሓውን፡ለርሱ፡ቤት፡አድርጌ፡ሰጠኹት፤ መኖሪያውም፡በጨው፡ምድር፡ነው።
7በከተማ፡ውካታ፡ይዘብታል፤ የነጂውን፡ጩኸት፡አይሰማም።
8ተራራውን፡እንደ፡መሰምሪያው፡ይመለከተዋል፥ ለምለሙንም፡ዅሉ፡ይፈልጋል።
9ጐሽ፡ያገለግልኽ፡ዘንድ፡ይታዘዛልን፧ ወይስ፡በግርግምኽ፡አጠገብ፡ያድራልን፧
10ጐሽ፡ይተልምልኽ፡ዘንድ፡ትጠምደዋለኽን፧ ወይስ፡ከአንተ፡በዃላ፡በዕርሻ፡ላይ፡ይጐለጕላልን፧
11ጕልበቱስ፡ብርቱ፡ስለ፡ኾነ፡ትታመነዋለኽን፧ ተግባርኽንስ፡ለርሱ፡ትተዋለኽን፧
12ዘርኽንስ፡ይመልስልኽ፡ዘንድ፥ በዐውድማኽስ፡ያከማችልኽ፡ዘንድ፡ትታመነዋለኽን፧
13የሰጐን፡ክንፍ፡በደስታ፡ይንቀሳቀሳል፤ ነገር፡ግን፡ክንፉና፡ላባው፡ጭምተኛ፡ነውን፧
14ዕንቍላሏን፡በመሬት፡ላይ፡ትተዋለች፥ በዐፈርም፡ውስጥ፡ታሞቀዋለች፤
15እግር፡ይሰብረው፡ዘንድ፥ የምድረ፡በዳም፡አውሬ፡ይረግጠው፡ዘንድ፡ትረሳለች።
16የርሷ፡እንዳልኾኑ፡በልጆቿ፡ትጨክናለች። በከንቱም፡ብትሠራ፡አትፈራም፤
17እግዚአብሔር፡ጥበብን፡ከርሷ፡ከልክሏልና፥ ማስተዋልንም፡አልሰጣትምና።
18ወደ፡ላይ፡ከፍ፡ከፍ፡ስትል፡ በፈረስና፡በፈረሰኛው፡ትሳለቃለች።
19ለፈረስ፡ጕልበቱን፡ሰጥተኸዋልን፧ ዐንገቱንስ፡ጋማ፡አልብሰኸዋልን፧
20እንደ፡አንበጣስ፡አፈናጠርኸውን፧ የማንኰራፋቱ፡ክብር፡የሚያስፈራ፡ነው።
21በኰቴው፡በሸለቆው፡ውስጥ፡ይጐደፍራል፥ በጕልበቱም፡ደስ፡ይለዋል፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ሰይፍም፡የታጠቁትን፡ለመገናኘት፡ይወጣል።
22በፍርሀት፡ላይ፡ይሥቃል፥ ርሱም፡አይደነግጥም፤ ከሰይፍም፡ፊት፡አይመለስም።
23በርሱ፡ላይ፡የፍላጻ፡ኰረጆና፡ብልጭልጭ፡የሚል፡ጦር፡ ሠላጢንም፡ያንኳኳሉ።
24በጭካኔና፡በቍጣ፡መሬትን፡ይውጣል፤ የመለከትም፡ድምፅ፡ቢሰማ፡አይቆምም።
25የመለከትም፡ድምፅ፡ሲሰማ፦ዕሠይ! ይላል፤ ከሩቅ፡ኾኖ፡ሰልፍንና፡የአለቃዎቹን፡ጩኸት፥ የሰራዊቱንም፡ውካታ፡ያሸታል።
26በእውኑ፡ከጥበብኽ፡የተነሣ፡ጭልፊት፡ያንዣብባልን፧ ወይስ፡ክንፎቹን፡ወደ፡ደቡብ፡ይዘረጋልን፧
27በአፍኽ፡ትእዛዝ፡ንስር፡ከፍ፡ከፍ፡ይላልን፧ ቤቱንስ፡በአርያም፡ላይ፡ያደርጋልን፧
28በገደል፡ላይ፡ይኖራል፤ በገደሉ፡ገመገምና፡በጥጉ፡ያድራል።
29በዚያም፡ኾኖ፡የሚነጥቀውን፡ይጐበኛል፤ ዐይኑም፡በሩቅ፡ትመለከታለች።
30ጫጩቶቹም፡ደም፡ይጠጣሉ፤ በድን፡ባለባትም፡ስፍራ፡ርሱ፡በዚያ፡አለ።