1እግዚአብሔርም፡በዐውሎ፡ነፋስ፡ውስጥ፡ኾኖ፡ለኢዮብ፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦
2ያለዕውቀት፡በሚነገር፡ቃል፡ ምክርን፡የሚያጨልም፡ይህ፡ማነው፧
3እንግዲህ፡እንደ፡ሰው፡ወገብኽን፡ታጠቅ፤ እጠይቅኻለኹ፥አንተም፡ተናገረኝ።
4ምድርን፡በመሠረትኹ፡ጊዜ፡አንተ፡ወዴት፡ነበርኽ፧ ታስተውል፡እንደ፡ኾንኽ፡ተናገር።
5ብታውቅስ፡መሠፈሪያዋን፡የወሰነ፥ በላይዋስ፡የመለኪያ፡ገመድ፡የዘረጋ፡ማን፡ነው፧
7አጥቢያ፡ኮከቦች፡በአንድነት፡ሲዘምሩ፥ የእግዚአብሔርም፡ልጆች፡ዅሉ፡እልል፡ሲሉ፥ መሠረቶቿ፡በምን፡ላይ፡ተተክለው፡ነበር፧ የማእዘኗንስ፡ድንጋይ፡ያቆመ፡ማን፡ነው፧
8ከማሕፀን፡እንደሚወጣ፡በወጣ፡ጊዜ፡ ባሕርን፡በመዝጊያዎች፡የዘጋ፡ማን፡ነው፧
9ደመናውን፡ለልብሱ፥ ጨለማንም፡ለመጠቅለያው፡አደረግኹ፤
10ድንበሩን፡በዙሪያው፡አድርጌ፥ መወርወሪያዎቹንና፡መዝጊያዎቹን፡አኑሬ።
11እስከዚህ፡ድረስ፡ድረሺ፥አትለፊ፤ በዚህም፡ለትዕቢተኛው፡ማዕበልሽ፡ገደብ፡ይኹን፡አልኹ።
13የምድርን፡ዳርቻ፡ይይዝ፡ዘንድ፥ ከርሷም፡በደለኛዎች፡ይናወጡ፡ዘንድ፥ በእውኑ፡ከተወለድኽ፡ዠምሮ፡ማለዳን፡አዘ፟ኻልን፧ ለወገግታም፡ስፍራውን፡አስታወቀኸዋልን፧
14ጭቃ፡ከማኅተም፡በታች፡እንደሚለወጥ፡እንዲሁ፡ርሷ፡ትለወጣለች፤ ነገርም፡ዅሉ፡እንደ፡ልብስ፡ተቀልሟል።
15ከበደለኛዎች፡ብርሃናቸው፡ተከልክሏል፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ከፍ፡ያለውም፡ክንድ፡ተሰብሯል።
16ወደባሕር፡ምንጭስ፡ውስጥ፡ገብተኻልን፧ በቀላዩስ፡መሠረት፡ውስጥ፡ተመላልሰኻልን፧
17የሞት፡በሮች፡ተገልጠውልኻልን፧ የሞትንስ፡ጥላ፡ደጆች፡አይተኻልን፧
18ምድርንስ፡በስፋቷ፡አስተውለኻታልን፧ ዅሉን፡ዐውቀኽ፡እንደ፡ኾነ፡ተናገር።
20ወደ፡ዳርቻው፡ትነዳው፡ዘንድ፥ ወደ፡ቤቱም፡የሚያደርሰውን፡ጐዳና፡ታውቅ፡ዘንድ፥ የብርሃን፡መኖሪያ፡መንገድ፡የት፡ነው፧ የጨለማውስ፡ቦታ፡ወዴት፡አለ፧
21በዚያን፡ጊዜ፡ተወልደኽ፡ነበርና፥ የዕድሜኽም፡ቍጥር፡ብዙ፡ነውና፤ በእውነት፡አንተ፡ሳታውቅ፡አትቀርም።
22በእውኑ፡ወደበረዶው፡ቤተ፡መዛግብት፡ገብተኻልን፧ የበረዶውንስ፡ቅንጣት፡ቤተ፡መዛግብት፡አይተኻልን፧
23ይኸውም፡ለመከራ፡ጊዜ፡ለሰልፍና፡ለጦርነት፡ቀን፡የጠበቅኹት፡ነው።
24ብርሃንስ፡በምን፡መንገድ፡ይከፈላል፧ የምሥራቅስ፡ነፋስ፡በምድር፡ላይ፡እንዴት፡ይበተናል፧
26ባድማውንና፡ውድማውን፡እንዲያጠግብ፥
27ሣሩንም፡እንዲያበቅል፥ ማንም፡በሌለባት፡ምድር፡ላይ፥ ሰውም፡በሌለባት፡ምድረ፡በዳ፡ላይ፡ዝናብን፡ያዘንብ፡ዘንድ፥ ለፈሳሹ፡ውሃ፡መንዶልዶያውን፥ ወይስ፡ለሚያንጐደጕድ፡መብረቅ፡መንገድን፡ያበጀ፡ማን፡ነው፧
28በእውኑ፡ለዝናብ፡አባት፡አለውን፧ ወይስ፡የጠልን፡ነጠብጣብ፡የወለደ፡ማን፡ነው፧
29በረዶስ፡ከማን፡ማሕፀን፡ወጣ፧ የሰማዩንስ፡ዐመዳይ፡ማን፡ወለደው፧
30ውሃዎች፡እንደ፡ድንጋይ፡ጠነከሩ፥ የቀላዩም፡ፊት፡ረግቷል።
31በእውኑ፡የሰባቱን፡ከዋክብት፡ዘለላ፡ታስር፡ዘንድ፥ ወይስ፡ኦሪዮን፡የሚባለውን፡ኮከብ፡ትፈታ፡ዘንድ፡ትችላለኽን፧ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
32ወይስ፡ማዛሮት፡የሚባሉትን፡ከዋክብት፡በጊዜያቸው፡ታወጣ፡ዘንድ፥ ወይስ፡ድብ፡የሚባለውን፡ኮከብ፡ከልጆቹ፡ጋራ፡ትመራ፡ዘንድ፡ትችላለኽን፧
33የሰማይን፡ሥርዐት፡ታውቃለኽን፧ በምድርስ፡ለይ፡እንዲሠለጥን፡ልታደርግ፡ትችላለኽን፧
34የውሃዎች፡ብዛት፡ይሸፍንኽ፡ዘንድ፡ ቃልኽን፡ወደ፡ደመናት፡ታነሣ፡ዘንድ፡ትችላለኽን፧
35መብረቆች፡ኼደው፦እንሆ፥እዚህ፡አለን፡ይሉኽ፡ዘንድ፡ ልትልካቸው፡ትችላለኽን፧
36በውስጡስ፡ጥበብን፡ያኖረ፥ ለሰውስ፡ልብ፡ማስተዋልን፡የሰጠ፡ማን፡ነው፧
38የሰማይን፡ደመና፡በጥበቡ፡ሊቈጥር፡የሚችል፡ማን፡ነው፧ ትቢያ፡በተበጠበጠ፡ጊዜ፥ ጓሎቹም፡በተጣበቁ፡ጊዜ፥ የሰማይን፡ረዋት፡ሊያዘነብል፡የሚችል፡ማን፡ነው፧
40በዋሾቻቸው፡ውስጥ፡ተጋድመው፥ በጫካም፡ውስጥ፡አድብተው፡ሳሉ፥ ለአንበሳዪቱ፡አደን፡ታድናለኽን፧ የልጆቿንስ፡ነፍስ፡ታጠግብ፡ዘንድ፡ትችላለኽን፧
41ልጆቹ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ሲጮኹ፥ የሚበሉትም፡ዐጥተው፡ሲቅበዘበዙ፥ ለቍራ፡መብልን፡የሚሰጠው፡ማን፡ነው፧