Skip to content
← Job

Chapter 37 · Amharic

Job

1ስለዚህም፡ልቤ፡ተንቀጠቀጠ፥ ከስፍራውም፡ተንቀሳቀሰ።

2የድምፁን፡መትመም፡ስሙ፥ ከአፉም፡የሚወጣውን፡ጕርምርምታ፡አድምጡ።

3ርሱን፡ወደ፡ሰማያት፡ዅሉ፡ታች፥ ብርሃኑንም፡ወደ፡ምድር፡ዳርቻ፡ይሰዳ፟ል።

4በስተዃላው፡ድምፅ፡ይጮኻል፤ በግርማውም፡ድምፅ፡ያንጐደጕዳል፤ ድምፁም፡በተሰማ፡ጊዜ፡ መብረቁን፡አይከለክልም።

5እግዚአብሔር፡በድምፁ፡ድንቅኛ፡ያንጐደጕዳል፤ እኛም፡የማናስተውለውን፡ታላቅ፡ነገር፡ያደርጋል።

6በረዶውንና፡ውሽንፍሩን፡ብርቱንም፡ዝናብ፦ በምድር፡ላይ፡ውደቁ፡ይላል።

7ሰው፡ዅሉ፡ሥራውን፡ያውቅ፡ዘንድ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የሰውን፡ዅሉ፡እጅ፡ያትማል።

8አውሬዎቹም፡ወደ፡ጫካው፡ይገባሉ፥ በዋሾቻቸውም፡ይቀመጣሉ።

9ከተሰወረ፡ማደሪያውም፡ዐውሎ፡ነፋስ፥ ከሰሜንም፡ብርድ፡ይወጣል።

10ከእግዚአብሔር፡እስትንፋስ፡ውርጭ፡ተሰጥቷል፤ የውሃዎችም፡ስፋት፡ይጠባ፟ል።

11የውሃውንም፡ሙላት፡በደመና፡ላይ፡ይጭናል፤ የብርሃኑንም፡ደመና፡ይበታትናል፤

13ለተግሣጽ፡ወይም፡ለምድሩ፡ወይም፡ለምሕረት፡ቢኾን፥ ሰው፡በሚኖርበት፡ዓለም፡ላይ፡ ያዘዘውን፡ዅሉ፡ያደርግ፡ዘንድ፡ ፈቃዱ፡ወደ፡መራችው፡ይዞራል።

14ኢዮብ፡ሆይ፥ይህን፡ስማ፤ ቁም፥የእግዚአብሔርንም፡ተኣምራት፡ዐስብ።

15በእውኑ፡እግዚአብሔር፡እንዴት፡እንደሚያዛ፟ቸው፥ የደመናውንም፡ብርሃን፡እንዴት፡እንደሚያበራ፡ዐውቀኻልን፧

16ወይስ፡የደመናውን፡ሚዛን፥ ወይስ፡በዕውቀት፡ፍጹም፡የኾነውን፡ተኣምራት፡ዐውቀኻልን፧

17በደቡብ፡ነፋስ፡ምድር፡ጸጥ፡ባለች፡ጊዜ፥ ልብስኽ፡የሞቀች፡አንተ፡ሆይ፥

18እንደ፡ቀለጠ፡መስተዋት፡ ብርቱ፡የኾኑትን፡ሰማያት፡ከርሱ፡ጋራ፡ልትዘረጋ፡ትችላለኽን፧

19እኛ፡ከጨለማ፡የተነሣ፡በሥርዐት፡መናገር፡አንችልምና፥ የምንለውን፡አስታውቀን።

20ማንም፡በርሱ፡ላይ፡ቢናገር፡ፈጽሞ፡ይዋጣልና፥ እኔ፡እናገር፡ዘንድ፡ብወድ፟፡ሰው፡ይነግረዋልን፧

21አኹንም፡ነፋስ፡ዐልፎ፡ካጠራ፟ቸው፡በዃላ፥ ሰው፡በሰማያት፡የሚበራውን፡ብርሃን፡ሊመለከት፡አይችልም።

22ከሰሜን፡ወርቅ፡የሚመስል፡ጌጠኛ፡ብርሃን፡ይወጣል፤ በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡የሚያስፈራ፡ግርማ፡አለ።

23ዅሉን፡የሚችል፡አምላክን፡እናገኝ፡ዘንድ፡አንችልም፤ በኀይል፡ታላቅ፡ነው፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org በፍርድና፡በጽድቅም፡አያስጨንቅም።

24ስለዚህ፥ሰዎች፡ይፈሩታል፤ በልባቸውም፡ጠቢባን፡የኾኑትን፡ዅሉ፡አይመለከትም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source