1ኤሊሁም፡ደግሞ፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦
2ገና፡ስለ፡እግዚአብሔር፡የሚነገር፡አለኝና፡ ጥቂት፡ቈየኝ፥እኔም፡አስታውቅኻለኹ።
3ዕውቀቴን፡ከሩቅ፡አመጣለኹ፥ ፈጣሪዬንም፦ጻድቅ፡ነው፡እላለኹ።
4ቃሌ፡በእውነት፡ያለሐሰት፡ነው፤ በዕውቀትም፡ፍጹም፡የኾነ፡ከአንተ፡ጋራ፡አለ።
5እንሆ፥እግዚአብሔር፡ኀያል፡ነው፥ማንንም፡አይንቅም፤ ርሱም፡በማስተዋል፡ብርታት፡ኀያል፡ነው።
6ርሱ፡የበደለኛዎችን፡ሕይወት፡አያድንም፤ ለችግረኛዎች፡ግን፡ፍርዱን፡ይሰጣል።
7ዐይኑን፡ከጻድቃን፡ላይ፡አያርቅም፤ ለዘለዓለምም፡ከነገሥታት፡ጋራ፡በዙፋን፡ላይ፡ያስቀምጣቸዋል፥ እነርሱም፡ከፍ፡ከፍ፡ይላሉ።
8በሰንሰለት፡ቢታሰሩ፥ ወይም፡በችግር፡ገመድ፡ቢጠመዱ፥
9ሥራቸውንና፡መተላለፋቸውን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org በትዕቢትም፡እንዳደረጉ፡ይናገራቸዋል።
10ዦሯቸውን፡ለተግሣጽ፡ይከፍተዋል፥ ከኀጢአትም፡ይመለሱ፡ዘንድ፡ያዛ፟ቸዋል።
11ቢሰሙ፡ቢያገለግሉትም፥ ዕድሜያቸውን፡በልማት፥ ዘመናቸውንም፡በተድላ፡ይፈጽማሉ።
12ባይሰሙ፡ግን፡በሰይፍ፡ይጠፋሉ፥ ያለዕውቀትም፡ይሞታሉ።
13ዝንጉዎች፡ግን፡ቍጣን፡ያዘጋጃሉ፤ ርሱም፡ባሰራቸው፡ጊዜ፡አይጮኹም።
14በሕፃንነታቸው፡ሳሉ፡ይሞታሉ፥ ሕይወታቸውም፡በሰዶማውያን፡መካከል፡ይጠፋል።
15የተቸገረውን፡በችግሩ፡ያድነዋል፤ በመከራም፡ዦሯቸውን፡ይገልጣል።
16እንዲሁም፡አንተን፡ከመከራ፡ ችግር፡ወደሌለበት፡ወደ፡ሰፊ፡ስፍራ፡በወሰደኽ፡ነበር፥ በማእድኽ፡ላይ፡የተዘጋጀውም፡ስብ፡በሞላበት፡ነበር።
17አንተ፡ግን፡በበደለኛዎች፡ፍርድ፡የተሞላኽ፡ነኽ፤ ስለዚህ፡ፍርድና፡ብይን፡ይይዝኻል።
18ቍጣ፡ለስድብ፡አያታል፟ኽ፤ የማማለጃም፡ብዛት፡ፈቀቅ፡አያድርግኽ።
19ባለጠግነትኽ፡የኀይልኽም፡ብርታት፡ዅሉ፡ ያለችግር፡እንድትኾን፡ሊረዳኽ፡ይችላልን፧
20ወገኖች፡ከስፍራቸው፡የሚወጡበትን፡ሌሊት፡አትመኝ።
21ከመከራ፡ይልቅ፡ይህን፡መርጠኻልና፥ ኀጢአትን፡እንዳትመለከት፡ተጠንቀቅ።
22እንሆ፥እግዚአብሔር፡በኀይሉ፡ከፍ፡ያለውን፡ነገር፡ያደርጋል፤ እንደ፡ርሱስ፡ያለ፡አስተማሪ፡ማን፡ነው፧
23መንገዱን፡ማን፡አዘዘለት፧ ወይስ፦ኀጢአትን፡ሠርተኻል፡የሚለው፡ማን፡ነው፧
24ሰዎች፡የዘመሩትን፡ሥራውን፡ታከብር፡ዘንድ፡ዐስብ።
25ሰዎች፡ዅሉ፡ተመልክተውታል፤ ሰውም፡ከሩቅ፡ያየዋል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
26እንሆ፥እግዚአብሔር፡ታላቅ፡ነው፥እኛም፡አናውቀውም። የዘመኑም፡ቍጥር፡አይመረመርም።
27የውሃውን፡ነጠብጣብ፡ወደ፡ላይ፡ይስባል፥ ዝናብም፡ከጉም፡ይንጠባጠባል፤
28ደመናት፡ያዘንባሉ፥ በሰዎችም፡ላይ፡በብዙ፡ያንጠባጥባሉ።
29የደመናውንም፡መዘርጋት፥ የማደሪያውንም፡ነጐድጓድ፡የሚያስተውል፡ማን፡ነው፧
30እንሆ፥በዙሪያው፡ብርሃኑን፡ይዘረጋል፤ የባሕሩንም፡ጥልቀት፡ይከድናል።
31በእነዚህ፡በአሕዛብ፡ላይ፡ይፈርዳል፤ ብዙም፡ምግብ፡ይሰጣል።
32እጆቹን፡በብርሃን፡ይሰውራል፥ በጠላቱም፡ላይ፡ይወጣ፡ዘንድ፡ያዘ፟ዋል፤
33የነጐድጓድ፡ድምፅ፡ስለ፡ርሱ፡ይናገራል፤ እንስሳዎችም፡ደግሞ፡ስለሚመጣው፡ውሽንፍር፡ይጮኻሉ።