Skip to content
← Job

Chapter 35 · Amharic

Job

1ኤሊሁም፡ደግሞ፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦

2ይህ፡ጽድቅ፡እንደ፡ኾነ፡ታስባለኽን፧ ወይስ፦በእግዚአብሔር፡ፊት፡እኔ፡ጻድቅ፡ነኝ፡ትላለኽን፧

3አንተ፦ምን፡ጥቅም፡አለኽ፧ ኀጢአት፡ሠርቼ፡ከማገኘው፡ይልቅ፡ኀጢአት፡ባልሠራ፡ኖሮ፡ምን፡እጠቀማለኹ፧ብለኽ፡ጠይቀኻልና።

4እኔ፡ለአንተና፡ከአንተ፡ጋራ፡ላሉ፡ለባልንጀራዎችኽ፡እመልሳለኹ።

5ዐይኖችኽን፡ወደ፡ሰማይ፡አቅንተኽ፡እይ፤ ከአንተም፡ከፍ፡ከፍ፡ያሉትን፡ደመናት፡ተመልከት።

6ኀጢአት፡ብትሠራ፡ምን፡ትጐዳዋለኽ፧ መተላለፍኽስ፡ቢበዛ፡ምን፡ታደርገዋለኽ፧

7ጻድቅስ፡ብትኾን፡ምን፡ትሰጠዋለኽ፧ ወይስ፡ከእጅኽ፡ምንን፡ይቀበላል፧

8እንደ፡አንተ፡ያለውን፡ሰው፡ክፋትኽ፡ይጐዳዋል፤ ለሰውም፡ልጅ፡ጽድቅኽ፡ይጠቅመዋል።

9ከግፍ፡ብዛት፡የተነሣ፡ሰዎች፡ይጮኻሉ፤ ከኀያላንም፡ክንድ፡የተነሣ፡ለርዳታ፡ይጠራሉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

11ነገር፡ግን፦በሌሊት፡መዝሙርን፡የሚሰጥ፥ ከምድርም፡እንስሳዎች፡ይልቅ፡የሚያስተምረን፡ ከሰማይም፡ወፎች፡ይልቅ፡ጥበበኛዎች፡የሚያደርገን፤ ፈጣሪዬ፡እግዚአብሔር፡ወዴት፡ነው፧የሚል፡የለም።

12በዚያ፡ስለ፡ክፉ፡ሰዎች፡ትዕቢት፡ይጮኻሉ፥ ርሱ፡ግን፡አይመልስላቸውም።

13በእውነት፡እግዚአብሔር፡ከንቱ፡ነገርን፡አይሰማም፥ ዅሉን፡የሚችል፡አምላክም፡አይመለከተውም፤

14ይልቁንም፦አላየውም፤ ነገሩ፡በርሱ፡ፊት፡ነው፥እኔም፡አጠብቀዋለኹ፡ስትል።

15አኹን፡ግን፡በቍጣው፡አልጐበኘምና። በኀጢአት፡እጅግ፡አያስብም፡ትላለኽ።

16ስለዚህ፥ኢዮብ፡አፉን፡በከንቱ፡ይከፍታል፥ ያለዕውቀትም፡ቃሉን፡ያበዛል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source