Skip to content
← Job

Chapter 34 · Amharic

Job

1ኤሊሁም፡ደግሞ፡መለሰ፥እንዲህም፡አለ፦

2እናንተ፡ጥበበኛዎች፥ቃሌን፡ስሙ፤ እናንተም፡ዐዋቂዎች፥ወደ፡እኔ፡አድምጡ።

3ትናጋ፡መብልን፡እንደሚቀምስ፥ ዦሮ፡ቃልን፡ትለያለችና።

4ቅን፡የኾነውን፡ነገር፡እንምረጥ፤ መልካሙንም፡ነገር፡በመካከላችን፡እንወቅ።

5ኢዮብ፦እኔ፡ጻድቅ፡ነኝ፥ እግዚአብሔር፡ግን፡ፍርዴን፡አስወገደ፤

6ምንም፡እውነተኛ፡ብኾን፡እንደ፡ውሸተኛ፡ተቈጠርኹ፤ ምንም፡ባልበድል፡ቍስሌ፡የማይፈወስ፡ነው፡ብሏል።

9ኢዮብም፦በእግዚአብሔር፡መደሰት፡ ለሰው፡ምንም፡አይጠቅምም፡ብሏልና፥ ከበደለኛዎች፡ጋራ፡የሚተባበር፥ ክፉ፡ከሚያደርጉስ፡ጋራ፡የሚኼድ፥ መሳለቅን፡እንደ፡ውሃ፡የሚጠጣት፡ እንደ፡ኢዮብ፡ያለ፡ሰው፡ማን፡ነው፧

10ስለዚህ፥እናንተ፡አእምሮ፡ያላችኹ፡ሰዎች፥ስሙኝ፤ ክፋትን፡ያደርግ፡ዘንድ፡ከእግዚአብሔር፥ በደልንም፡ይሠራ፡ዘንድ፡ዅሉን፡ከሚችል፡አምላክ፡ይራቅ።

11ለሰው፡ሥራውን፡ይመልስለታል፥ ሰውም፡እንደ፡መንገዱ፡ያገኝ፡ዘንድ፡ያደርጋል።

12በእውነት፡እግዚአብሔር፡ክፉ፡አይሠራም፥ ዅሉንም፡የሚችል፡አምላክ፡ፍርድን፡ጠማማ፡አያደርግም።

13ምድርን፡ዐደራ፡የሰጠው፡ማን፡ነው፧ ዓለምንስ፡ዅሉ፡በርሱ፡ላይ፡ያኖረ፡ማን፡ነው፧

14ርሱ፡ልቡን፡ወደ፡ራሱ፡ቢመልስ፥ መንፈሱንና፡እስትንፋሱን፡ወደ፡ራሱ፡ቢሰበስብ፥

15ሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡በአንድነት፡ይጠፋል፥ ሰውም፡ወደ፡ዐፈር፡ይመለሳል።

16አስተዋይ፡ብትኾን፡ይህን፡ስማ፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የንግግሬንም፡ቃል፡አድምጥ።

17በእውኑ፡ጽድቅን፡የሚጠላ፡ይሠለጥናልን፧ ጻድቅና፡ኀያል፡የኾነውስ፡በደለኛ፡ታደርገዋለኽን፧

18ማንም፡ሰው፡ንጉሡን፦በደለኛ፡ነኽ፥ መኳንንቱንም፦ክፉዎች፡ናችኹ፡ይላልን፧

19እነርሱ፡ዅሉ፡የእጁ፡ሥራ፡ናቸውና፥ በአለቃዎች፡ፊት፡አያደላም፥ ባለጠጋውንም፡ሰው፡ከድኻው፡ይበልጥ፡አይመለከትም።

20እነርሱ፡በመንፈቀ፡ሌሊት፡በድንገት፡ይሞታሉ፤ ሕዝቡ፡ተንቀጥቅጦ፡ያልፋል፥ ኀያላንም፡ያለእጅ፡ይነጠቃሉ።

21ዐይኖቹ፡በሰው፡መንገድ፡ላይ፡ናቸው፥ ርምጃውንም፡ዅሉ፡ያያል።

22ኀጢአትን፡የሚሠሩ፡ይሰወሩበት፡ዘንድ፡ ጨለማ፡ወይም፡የሞት፡ጥላ፡የለም።

23ሰው፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለመፈራረድ፡እንዲመጣ፡ ጊዜ፡አይወሰንለትም።

24ታላላቆችን፡ያለምርመራ፡ይሰባብራል፥ በእነርሱም፡ፋንታ፡ሌላዎችን፡ያቆማል።

25ሥራቸውን፡ያውቃል፤ እንዲደቁ፟ም፡በሌሊት፡ይገለባብጣቸዋል።

26ሰዎች፡እያዩ፡እንደ፡ክፉዎች፡ይመታቸዋል፤

28የድኻውን፡ልቅሶ፡ወደ፡ርሱ፡ያደርሱ፡ዘንድ፥ ርሱም፡የችግረኛውን፡ድምፅ፡ይሰማ፡ዘንድ፥ ርሱን፡ከመከተል፡ፈቀቅ፡ብለዋልና፥ ከመንገዱም፡ዅሉ፡አንዱን፡አልተመለከቱምና።

29በሕዝብ፡ወይም፡በሰው፡ዘንድ፡ቢኾን፥ ርሱ፡ቢያሳርፍ፡የሚፈርድ፡ማን፡ነው፧ ፊቱንስ፡ቢሰውር፡የሚያየው፡ማን፡ነው፧

30ይህም፡ዝንጉ፡ሰው፡እንዳይነግሥ፥ ሕዝቡም፡የሚያጠምድ፡እንዳይኖር፡ነው።

31እግዚአብሔርን፦እኔ፡ሳልበድል፡ቅጣት፡ተቀበልኹ፤

32የማላየውን፡ነገር፡አንተ፡አስተምረኝ፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ኀጢአትንም፡ሠርቼ፡እንደ፡ኾነ፥ ደግሜ፡አልሠራም፡የሚለው፡ማን፡ነው፧

33በእውኑ፡አንተ፡ጥለኸዋልና፥ ፍዳው፡አንተ፡እንደምትወደ፟ው፡ይኾናልን፧ አንተ፡ትመርጣለኽ፡እንጂ፡እኔ፡አይደለኹም፤ ስለዚህ፡የምታውቀውን፡ተናገር።

34የሚሰሙኝ፡ጥበበኛዎች፡ዅሉ፥ አስተዋዮችም፡እንዲህ፡ይሉኛል።

35ኢዮብ፡ያለዕውቀት፡ተናግሯል፥ ቃሉም፡በአእምሮ፡አይደለችም።

36ኢዮብ፡እስከ፡ፍጻሜ፡ድረስ፡ምነው፡በተፈተነ፡ኖሮ! ርሱ፡እንደ፡ክፉዎች፡መልሷልና፤

37በኀጢአቱም፡ላይ፡ዐመፅን፡ጨምሯልና፥ በእኛም፡መካከል፡በእጁ፡ያጨበጭባልና፥ ቃልንም፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ያበዛልና።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source