1ነገር፡ግን፥ኢዮብ፡ሆይ፥ንግግሬን፡እንድትሰማ፥ ቃሌንም፡ዅሉ፡እንድታደምጥ፡እለምንኻለኹ።
2እንሆ፥አፌን፡ከፍቻለኹ፥ አንደበቴም፡በትናጋዬ፡ተናግሯል።
3ቃሌ፡የልቤን፡ቅንነት፡ያወጣል፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ከንፈሮቼም፡የሚያውቁትን፡በቅንነት፡ይናገራሉ።
4የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡ፈጠረኝ፥ ዅሉንም፡የሚችል፡የአምላክ፡እስትንፋስ፡ሕይወት፡ሰጠኝ።
5ይቻልኽ፡እንደ፡ኾነ፡መልስልኝ፤ ቃልኽንም፡አዘጋጅተኽ፡በፊቴ፡ቁም።
6እንሆ፥በእግዚአብሔር፡ፊት፡እኔ፡እንደ፡አንተ፡ነኝ፤ እኔ፡ደግሞ፡ከጭቃ፡የተፈጠርኹ፡ነኝ።
7እንሆ፥ግርማዬ፡አታስፈራኽም፡ እጄም፡አትከብድብኽም።
8በዦሮዬ፡ተናግረኻል፥ የቃልኽንም፡ድምፅ፡ሰምቻለኹ፥እንዲህም፡ብለኻል።
9እኔ፡ያለመተላለፍ፡ንጹሕ፡ነኝ፤ ያለነውር፡ነኝ፥ኀጢአትም፡የለብኝም፤
10እንሆ፥ምክንያት፡አግኝቶብኛል፥ እንደ፡ጠላቱም፡ቈጥሮኛል፤
11እግሬን፡በግንድ፡አጣበቀ፥ መንገዴንም፡ዅሉ፡ተመለከተ።
12እንሆ፥አንተ፡በዚህ፡ጻድቅ፡አይደለኽም፤ እግዚአብሔር፡ከሰው፡ይበልጣል፡ብዬ፡እመልስልኻለኹ።
13አንተ፦ለቃሌ፡ዅሉ፡አይመልስልኝም፡ብለኽ፥ ስለ፡ምን፡ከርሱ፡ጋራ፡ትከራከራለኽ፧
14እግዚአብሔር፡ባንድ፡መንገድ፡በሌላም፡ይናገራል፤ ሰው፡ግን፡አያስተውለውም።
15በሕልም፥በሌሊት፡ራእይ፥ ዐፍላ፡እንቅልፍ፡በሰዎች፡ላይ፡ሲወድቅ፥ በዐልጋ፡ላይ፡ተኝተው፡ሳሉ፥
16በዚያን፡ጊዜ፡የሰዎችን፡ዦሮ፡ይከፍታል፥ በተግሣጹም፡ያስደነግጣቸዋል፥
17ሰውን፡ከክፉ፡ሥራው፡ይመልሰው፡ዘንድ፡ ከሰውም፡ትዕቢትን፡ይሰውር፡ዘንድ፤
18ነፍሱን፡ከጕድጓድ፥ በሰይፍም፡እንዳይጠፋ፡ሕይወቱን፡ይጠብቃል።
19ደግሞ፡በዐልጋ፡ላይ፡በደዌ፡ይገሥጸዋል፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ዐጥንቱንም፡ዅሉ፡ያደነዝዛል።
20ሕይወቱም፡እንጀራን፥ ነፍሱም፡ጣፋጭ፡መብልን፡ትጠላለች።
21ሥጋው፡እስከማይታይ፡ድረስ፡ይሰለስላል፤ ተሸፍኖ፡የነበረውም፡ዐጥንት፡ይገለጣል።
22ነፍሱ፡ወደ፡ጕድጓዱ፥ ሕይወቱም፡ወደሚገድሏት፡ቀርባለች።
23የቀናውን፡መንገድ፡ለሰው፡ያስታውቀው፡ዘንድ፥ ከሺሕ፡አንድ፡ኾኖ፡የሚተረጕም፡መልአክ፡ቢገኝለት፥
24እየራራለት። ቤዛ፡አግኝቻለኹና፡ ወደ፡ጕድጓድ፡እንዳይወርድ፡አድነው፡ቢለው፥
25ሥጋው፡እንደ፡ሕፃን፡ሥጋ፡ይለመልማል፤ ወደጕብዝናውም፡ዘመን፡ይመለሳል።
26ወደ፡እግዚአብሔር፡ይጸልያል፥ ርሱም፡ሞገስን፡ይሰጠዋል፡ ፊቱንም፡በደስታ፡ያሳየዋል፤ ለሰውም፡ጽድቁን፡ይመልስለታል።
27ርሱም፡በሰው፡ፊት፡እየዘመረ፦ እኔ፡በድያለኹ፥ቅኑንም፡አጣምሜያለኹ፤ የሚገ፟ባ፟ኝንም፡ብድራት፡አልተቀበልኹም፤
28ነፍሴ፡ወደ፡ጕድጓድ፡እንዳትወርድ፡አድኗታል፥ ሕይወቴም፡ብርሃንን፡ታያለች፡ይላል።
29እግዚአብሔር፡ይህን፡ዅሉ፡ ኹለት፡ጊዜና፡ሦስት፡ጊዜ፡ከሰው፡ጋራ፡ያደርጋል፤
30ይህም፡ነፍሱን፡ከጕድጓድ፡ይመልስ፡ዘንድ፥ በሕያዋንም፡ብርሃን፡ያበራ፡ዘንድ፡ነው።
31ኢዮብ፡ሆይ፥አድምጥ፥እኔንም፡ስማ፤ ዝም፡በል፥እኔም፡እናገራለኹ።
32ነገር፡ቢኖርኽ፡መልስልኝ፤ ትጸድቅ፡ዘንድ፡እወዳ፟ለኹና፡ተናገር።
33ያለዚያም፡እኔን፡ስማ፤ ዝም፡በል፥እኔም፡ጥበብን፡አስተምርኻለኹ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org