1ኢዮብም፡ራሱን፡ጻድቅ፡አድርጎ፡ነበርና፥እነዚያ፡ሦስቱ፡ሰዎች፡መመለስን፡ተዉ።
2ከራም፡ወገን፡የኾነ፡የቡዛዊው፡የባርክኤል፡ልጅ፡የኤሊሁ፡ቍጣ፡ነደደ፤ከእግዚአብሔር፡ይልቅ፡ራሱን፡ ጻድቅ፡አድርጎ፡ነበርና፥ኢዮብን፡ተቈጣው።
3ደግሞም፡በኢዮብ፡ፈረዱበት፡እንጂ፡የሚገ፟ባ፟፡መልስ፡ስላላገኙ፥በሦስቱ፡ባልንጀራዎቹ፡ላይ፡ተቈጣ።
4ኤሊሁ፡ግን፡ከርሱ፡ይልቅ፡ሽማግሌዎች፡ነበሩና፥ከኢዮብ፡ጋራ፡መናገርን፡ጠብቆ፡ነበር።
5ኤሊሁም፡በነዚህ፡በሦስቱ፡ሰዎች፡አፍ፡መልስ፡እንደሌለ፡ባየ፡ጊዜ፡ቍጣው፡ነደደ።
6የቡዛዊውም፡የባርክኤል፡ልጅ፡ኤሊሁ፡ተናገረ፡እንዲህም፡አለ፦ እኔ፡በዕድሜ፡ታናሽ፡ነኝ፥እናንተ፡ግን፡ሽማግሌዎች፡ናችኹ፤ ስለዚህም፡ሠጋኹ፤ዕውቀቴን፡እገልጥላችኹ፡ዘንድ፡ፈራኹ።
7እንደዚህም፡አልኹ፦ዓመታት፡በተናገሩ፡ነበር፥ የዓመታትም፡ብዛት፡ጥበብን፡ባስተማረች፡ነበር።
8ነገር፡ግን፥በሰው፡ውስጥ፡መንፈስ፡አለ፥ ዅሉንም፡የሚችል፡የአምላክ፡እስትንፋስ፡ማስተዋልን፡ይሰጣል።
9በዕድሜ፡ያረጁ፡ጠቢባን፡አይደሉም፥ ሽማግሌዎችም፡ፍርድን፡አያስተውሉም።
10ስለዚህም፦ስሙኝ፤ እኔ፡ደግሞ፡ዕውቀቴን፡እገልጥላችዃለኹ፡አልኹ።
11እንሆ፥ቃላችኹን፡በትዕግሥት፡ጠበቅኹ፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የምትናገሩትን፡ነገር፡እስክትመረምሩ፡ድረስ፤ ብልኀታችኹን፡አዳመጥኹ።
12እንዲሁም፡ልብ፡አደረግኹ፤ እንሆም፥በእናንተ፡መካከል፡ኢዮብን፡ያስረዳ፥ ወይም፡ለቃሉ፡የመለሰ፡የለም።
13እናንተም፦ጥበብን፡አግኝተናል፤ እግዚአብሔር፡ነው፡እንጂ፡ሰው፡አያሸንፈውም፡እንዳትሉ፡ተጠንቀቁ።
14ርሱ፡ግን፡ቃሉን፡በእኔ፡ላይ፡አልተናገረም፤ እኔም፡በንግግራችኹ፡አልመልስለትም።
15እነርሱ፡ደነገጡ፥ዳግመኛም፡አልመለሱም፤ የሚናገሩትንም፡ዐጡ።
16እነርሱ፡አልተናገሩምና፥ ቆመው፡ዳግመኛ፡አልመለሱምና፡እኔ፡በትዕግሥት፡እጠብቃለኹን፧
17እኔ፡ደግሞ፡ፈንታዬን፡እመልሳለኹ፥ ዕውቀቴንም፡እገልጣለኹ፤
18እኔ፡ቃል፡ተሞልቻለኹና፥ በውስጤም፡ያለ፡መንፈስ፡አስገድዶኛልና።
19በተሓ፡ጠጅ፡እንደ፡ተሞላና፡ሊቀደድ፡እንደ፡ቀረበ፡አቍማዳ፥ ሊፈነዳ፡እንደማይችል፡እንደ፡ወይን፡ጠጅ፡ አቍማዳ፥እንሆ፥አንዠቴ፡ኾነ።
20ጥቂት፡እንድተነፍስ፡እናገራለኹ፤ ከንፈሬን፡ገልጬ፡እመልሳለኹ።
21ለሰው፡ፊት፡ግን፡አላደላም፤ ሰውንም፡አላቈላምጥም።
22በማቈላመጥ፡እናገር፡ዘንድ፡አላውቅምና፤ ያለዚያስ፡ፈጣሪዬ፡ፈጥኖ፡ከሕይወቴ፡ይለየኝ፡ነበር።