1ከዐይኔ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡ገባኹ፤ እንግዲህስ፡ቈንዦዪቱን፡እንዴት፡እመለከታለኹ፧
2የእግዚአብሔር፡ዕድል፡ፈንታ፡ከላይ፥ ዅሉንም፡የሚችል፡አምላክ፡ርስት፡ከአርያም፡ምንድር፡ነው፧
3መዓትስ፡ለኀጢአተኛ፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org መለየትስ፡ለሚበድሉ፡አይደለችምን፧
4መንገዴን፡አያይምን፧ ርምጃዬንስ፡ዅሉ፡አይቈጥርምን፧
6በእውነተኛ፡ሚዛን፡ልመዘን፥ እግዚአብሔርም፡ቅንነቴን፡ይወቅ። በሐሰት፡ኼጄ፡እንደ፡ኾነ፡ እግሬም፡ለሽንገላ፡ቸኵላ፡እንደ፡ኾነ፥
7ርምጃዬ፡ከመንገድ፡ፈቀቅ፡ብሎ፥ ልቤም፡ዐይኔን፡ተከትሎ፥ ነውርም፡ከእጄ፡ጋራ፡ተጣብቆ፡እንደ፡ኾነ፥
8እኔ፡ልዝራ፥ሌላ፡ሰውም፡ይብላው፤ የሚበቅለውም፡ዅሉ፡ይነቀል።
9ልቤ፡ወደ፡ሌላዪቱ፡ሴት፡ጐምዥቶ፡እንደ፡ኾነ፥ በባልንጀራዬም፡ደጅ፡አድብቼ፡እንደ፡ኾነ፥
10ሚስቴ፡ለሌላ፡ሰው፡ትፍጭ፥ ሌላዎችም፡በርሷ፡ላይ፡ይጐንበሱ።
11ይህ፡ክፉ፡አበሳ፥ ፈራጆችም፡የሚቀጡበት፡በደል፡ነውና፤
12ይህ፡እስከ፡ጥፋት፡ድረስ፡የሚበላ፡እሳት፥ ቡቃያዬንም፡ዅሉ፡የሚነቅል፡ነውና።
13ወንድ፡ባሪያዬ፡ወይም፡ሴት፡ባሪያዬ፡ከእኔ፡ጋራ፡በተሟገቱ፡ጊዜ፥ ሙግታቸውን፡ንቄ፡እንደ፡ኾነ፥
14እግዚአብሔር፡በተነሣ፡ጊዜ፡ምን፡አደርጋለኹ፧ በጐበኘኝ፡ጊዜ፡ምን፡እመልስለታለኹ፧
15እኔን፡በማሕፀን፡የፈጠረ፡ርሱንስ፡የፈጠረው፡አይደለምን፧ በማሕፀንስ፡ውስጥ፡የሠራን፡አንድ፡አይደለንምን፧
16ድኻውን፡ከልመናው፡ከልክዬ፥ የመበለቲቱን፡ዐይን፡አጨልሜ፡እንደ፡ኾነ፥
17እንጀራዬን፡ለብቻዬ፡በልቼ፡እንደ፡ኾነ፥ ድኻ፡አደጉም፡ደግሞ፡ከርሱ፡ሳይበላ፡ቀርቶ፡እንደ፡ኾነ፤
18ርሱን፡ግን፡ከታናሽነቴ፡ዠምሬ፡እንደ፡አባቱ፡ከእኔ፡ጋራ፡አሳድጌው፡ነበር፥ ርሷንም፡ከእናቴ፡ማሕፀን፡ዠምሬ፡መራዃት፤
19ዕራቍቱን፡የኾነው፡ሰው፡ሲጠፋ፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ወይም፡ድኻ፡ያለልብስ፡ሲኾን፡አይቼ፡እንደ፡ኾነ፥
20ጐንና፡ጐኑ፡ያልባረከችኝ፥ በበጎቼም፡ጠጕር፡ያልሞቀ፡እንደ፡ኾነ፤
21በበሩ፡ረዳት፡ስላየኹ፥ በድኻ፡አደጉ፡ላይ፡እጄን፡አንሥቼ፡እንደ፡ኾነ፥
22ትከሻዬ፡ከመሠረቷ፡ትውደቅ፥ ክንዴም፡ከመገናኛዋ፡ትሰበር።
23የእግዚአብሔር፡መዓት፡አስደንግጦኛልና፤ በክብሩም፡ፊት፡ምንም፡ለማድረግ፡አልቻልኹም።
24ወርቅን፡ተስፋ፡አድርጌ፥ ጥሩውንም፡ወርቅ፦ባንተ፡እታመናለኹ፡ብዬ፡እንደ፡ኾነ፤
25ሀብቴ፡ስለ፡በዛ፥ እጄም፡ብዙ፡ስላገኘች፡ደስ፡ብሎኝ፡እንደ፡ኾነ፤
26ፀሓይ፡ሲበራ፡ ጨረቃ፡በክብር፡ስትኼድ፡አይቼ፥
27ልቤ፡በስውር፡ተታሎ፟፥ አፌም፡እጄን፡ስሞ፡እንደ፡ኾነ፤
28ልዑል፡እግዚአብሔርን፡በካድኹ፡ነበርና፥ ይህ፡ደግሞ፡ፈራጆች፡የሚቀጡበት፡በደል፡በኾነ፡ነበር።
29በሚጠላኝ፡መጥፋት፡ደስ፡ብሎኝ፡ ክፉ፡ነገርም፡ባገኘው፡ጊዜ፡ሐሤት፡አድርጌ፡እንደ፡ኾነ፤
30ነገር፡ግን፥በመርገም፡ነፍሱን፡በመሻት፡ አንደበቴን፡ኀጢአት፡ይሠራ፡ዘንድ፡አልሰጠኹም፤
31በድንኳኔ፡የሚኖሩ፡ሰዎች፦ በከብቱ፡ሥጋ፡ያልጠገበ፡ማን፡ይገኛል፧ብለው፡እንደ፡ኾነ፤
32መጻተኛው፡ግን፡በሜዳ፡አያድርም፡ነበር፥ ደጄንም፡ለመንገደኛ፡እከፍት፡ነበር፤
33በደሌንም፡በብብቴ፡በመሸሸግ፡ ኀጢአቴን፡እንደ፡ሰው፡ሰውሬ፡እንደ፡ኾነ፤
34ከሕዝብ፡ብዛት፡ፈርቼ፥ የዘመዶቼም፡ንቀት፡አስደንግጦኝ፥ ዝም፡ብዬ፡ከደጅ፡ያልወጣኹ፡እንደ፡ኾነ፤
35የሚያዳምጠኝ፡ምነው፡በኖረልኝ! http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እንሆ፥የእጄ፡ምልክት፡ ዅሉን፡የሚችል፡አምላክ፡ይመልስልኝ፤ ከባላጋራዬ፡የተጻፈው፡የክስ፡ጽሑፍ፡ምነው፡በተገኘልኝ!
36በትከሻዬ፡ላይ፡እሸከመው፥ አክሊልም፡አድርጌ፡በራሴ፡አስረው፡ነበር፤
37የርምጃዬን፡ቍጥር፡አስታውቀው፥ እንደ፡አለቃም፡ኾኜ፡አቀርብለት፡ነበር።
38ዕርሻዬ፡በእኔ፡ላይ፡ጮኻ፡እንደ፡ኾነ፥ ትልሞቿም፡ባንድ፡ላይ፡አልቅሰው፡እንደ፡ኾነ፤
39ፍሬዋን፡ያለዋጋ፡በልቼ፥ የባለቤቶችንም፡ነፍስ፡አሳዝኜ፡እንደ፡ኾነ፥
40በስንዴ፡ፋንታ፡አሜከላ፥ በገብስም፡ፋንታ፡ኵርንችት፡ይውጣብኝ።የኢዮብ፡ቃል፡ተፈጸመ።