1አኹን፡ግን፡በዕድሜ፡ከእኔ፡የሚያንሱ፥ አባቶቻቸውን፡ከመንጋዬ፡ውሻዎች፡ጋራ፡ለማኖር፡የናቅዃቸው፥ በእኔ፡ላይ፡ተሣለቁብኝ።
2ሙሉ፡ሰው፡መኾናቸው፡ጠፍቶባቸው፡ነበርና፥ የእጃቸው፡ብርታት፡ለእኔ፡ምን፡ይጠቅማል፧
3በራብና፡በቀጠና፡የመነመኑ፡ናቸው፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የመፍረስና፡የመፈታት፡ጨለማ፡ወዳለበት፡ ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ይሸሻሉ።
4በቍጥቋጦ፡አጠገብ፡ያለውን፡ ጨው፡ጨው፡የሚለውን፡አትክልት፡ይለቅማሉ፤ የክትክታ፡ሥር፡ደግሞ፡መብላቸው፡ነው።
5ከሰዎች፡ተለይተው፡ተሰደዱ፤ በሌባ፡ላይ፡እንደሚጮኽ፡ይጮኹባቸዋል።
6በሸለቆ፡ፈረፈርና፡በምድር፡ጕድጓድ፡ በድንጋይም፡ዋሻ፡ውስጥ፡ይኖራሉ።
7በቍጥቋጦ፡መካከል፡ይጮኻሉ፤ ከሳማ፡በታች፡ተሰብስበዋል።
8የሰነፎችና፡የነውረኛዎች፡ልጆች፡ናቸው፤ ከምድርም፡በግርፋት፡የተባረሩ፡ናቸው።
9አኹንም፡እኔ፡መዝፈኛና፡መተረቻ፡ኾንዃቸው።
10ተጸየፉኝ፥ከእኔም፡ራቁ፤ አክታቸውንም፡በፊቴ፡መትፋትን፡አልተዉም።
11የቀስቴን፡አውታር፡አላልቶብኛል፥አዋርዶኝማል፤ እነርሱም፡በፊቴ፡ልጓማቸውን፡ፈተ፟ዋል።
12በቀኜ፡በኩል፡ዱርዬዎች፡ተነሥተዋል፥ እግሬንም፡ይገለብጣሉ፤ የጥፋታቸውን፡መንገድ፡በእኔ፡ላይ፡ይጐድባሉ።
13ጐዳናዬን፡ያበላሻሉ፤ ረዳት፡የሌላቸው፡ሰዎች፡መከራዬን፡ያበዛሉ።
14በሰፊ፡ፍራሽ፡እንደሚመጡ፡ይመጡብኛል፤ በባድማ፡ውስጥ፡ይንከባለሉብኛል።
15ድንጋጤ፡በላዬ፡ተመለሰችብኝ፥ ክብሬንም፡እንደ፡ነፋስ፡ያሳድዷታል፤ ደኅንነቴም፡እንደ፡ደመና፡ዐልፋለች።
16አኹንም፡ነፍሴ፡በውስጤ፡ፈሰሰች፤ የመከራም፡ዘመን፡ያዘችኝ።
17በሌሊት፡ዐጥንቴ፡በደዌ፡ተነደለች፥ ዥማቶቼም፡አያርፉም።
18ከታላቁ፡ደዌ፡ኀይል፡የተነሣ፡ልብሴ፡ተበላሸች፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እንደ፡ቀሚስ፡ክሳድ፡ዐነቀችኝ።
19ርሱ፡በጭቃ፡ውስጥ፡ጣለኝ፥ ዐፈርና፡ዐመድም፡መሰልኹ።
20ወዳንተ፡ጮኽኹ፥አልመለስኽልኝም፤ ተነሣኹ፥አልተመለከትኸኝም።
21ተመልሰኽ፡ጨካኝ፡ኾንኽብኝ፤ በእጅኽም፡ብረታት፡አስጨነቅኸኝ።
22በነፋስ፡አነሣኸኝ፥በላዩም፡አስቀመጥኸኝ፤ በዐውሎ፡ነፋስ፡አቀለጥኸኝ።
23ለሞት፡ሕያዋንም፡ዅሉ፡ለሚሰበሰቡበት፡ቤት፡አሳልፈኽ፡እንደምትሰጠኝ፡ዐውቄያለኹና።
24ነገር፡ግን፥ሰው፡በወደቀ፡ጊዜ፡እጁን፡አይዘረጋምን፧ በጥፋቱስ፡ጊዜ፡አይጮኽምን፧
25ጭንቅ፡ቀን፡ላገኘው፡ሰው፡አላለቀስኹምን፧ ለችግረኛስ፡ነፍሴ፡አላዘነችምን፧
26ነገር፡ግን፥በጎነትን፡በተጠባበቅኹ፡ጊዜ፡ክፉ፡ነገር፡መጣችብኝ፤ ብርሃንን፡በትዕግሥት፡ጠበቅኹ፥ጨለማም፡መጣ።
27አንዠቴ፡ፈላች፥አላረፈችም፤ የመከራም፡ዘመን፡መጣችብኝ።
28ያለፀሓይ፡በትካዜ፡ኼድኹ፤ በጉባኤም፡መካከል፡ቆሜ፡ጮኽኹ።
29ለቀበሮ፡ወንድም፥ ለሰጐንም፡ባልንጀራ፡ኾንኹ።
30ቍርበቴ፡ጠቈረ፥ከእኔም፡ተለይቶ፡ርግፍግፍ፡አለ፤ ዐጥንቴም፡ከትኵሳት፡የተነሣ፡ተቃጠለች።
31ስለዚህ፥መሰንቆዬ፡ለሐዘን፥ እንቢልታዬም፡ለሚያለቅሱ፡ቃል፡ኾነ።