Skip to content
← Job

Chapter 29 · Amharic

Job

1ኢዮብም፡ምሳሌውን፡ይመስል፡ዘንድ፡ደገመ፥እንዲህም፡አለ፦

2እግዚአብሔር፡ይጠብቀኝ፡እንደ፡ነበረው፡ጊዜ፥ እንደ፡ፊተኛው፡ወራት፡ምነው፡በኾንኹ!

3በራሴ፡ላይ፡መብራቱ፡በበራ፡ጊዜ፥ እኔም፡ጨለማውን፡ዐልፌ፡በብርሃኑ፡በኼድኹ፡ጊዜ፥

4በሙሉ፡ሰውነቴ፡እንደ፡ነበርኹ፡ጊዜ፥ እግዚአብሔር፡ድንኳኔን፡በጋረደ፡ጊዜ፥

5ዅሉን፡የሚችል፡አምላክ፡ከእኔ፡ጋራ፡ገና፡ሳለ፥ ልጆቼም፡በዙሪያዬ፡ሳሉ፥

6መንገዴ፡በቅቤ፡ይታጠብ፡በነበረ፡ጊዜ፥ ድንጋዩ፡የዘይት፡ፈሳሽ፡ያፈስ፟ልኝ፡በነበረ፡ጊዜ።

7ወደከተማዪቱ፡በር፡በወጣኹ፡ጊዜ፥ በአደባባዩም፡ወንበሬን፡ባኖርኹ፡ጊዜ፥

8ጐበዛዝት፡እኔን፡አይተው፡ተሸሸጉ፥ ሽማግሌዎችም፡ተነሥተው፡ቆሙ።

9አለቃዎቹ፡ከመናገር፡ዝም፡አሉ፥ እጃቸውንም፡በአፋቸው፡ላይ፡ጫኑ።

10የታላላቆቹም፡ድምፅ፡አረመመ፤ ምላሳቸውም፡በትናጋቸው፡ተጣጋ።

11የሰማችኝ፡ዦሮ፡አሞገሰችኝ፥ ያየችኝም፡ዐይን፡መሰከረችልኝ፤

12የሚጮኸውን፡ችግረኛ፥ ድኻ፡አደጉንና፡ረጂ፡የሌለውን፡አድኜ፡ነበርና።

13ለጥፋት፡የቀረበው፡በረከት፡በላዬ፡መጣ፤ የባልቴቲቱንም፡ልብ፡እልል፡አሠኘኹ።

14ጽድቅን፡ለበስኹ፡ርሷም፡ለበሰችኝ፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ፍርዴም፡እንደ፡መጐናጸፊያና፡እንደ፡ኵፋር፡ነበረ።

15ለዕውር፡ዐይን፥ ለዐንካሳ፡እግር፡ነበርኹ።

16ለድኻው፡አባት፡ነበርኹ፤ የማላውቀውንም፡ሰው፡ሙግት፡መረመርኹ።

17የኀጢአተኛውን፡መንጋጋ፡ሰበርኹ፥ የነጠቀውንም፡ከጥርሱ፡ውስጥ፡አስጣልኹ።

18እኔም፡አልኹ፦በልጆቼ፡መካከል፡እሞታለኹ፥ ዕድሜዬንም፡እንደ፡አሸዋ፡አበዛለኹ፤

19ሥሬ፡በውሃ፡ላይ፡ተዘርግቷል፥ ጠልም፡በቅርንጫፌ፡ላይ፡ያድራል፤

20ክብሬ፡በእኔ፡ዘንድ፡ታድሷል፥ ቀስቴም፡በእጄ፡ውስጥ፡ለምልሟል።

21ሰዎች፡እኔን፡ሰምተው፡በትዕግሥት፡ተጠባበቁ፥ ምክሬንም፡ለማዳመጥ፡ዝም፡አሉ።

22ከቃሌ፡በዃላ፡አንዳች፡አልመለሱም፤ ንግግሬም፡በርሱ፡ላይ፡ተንጠባጠበ።

23ዝናብን፡እንደሚጠብቁ፡በትዕግሥት፡ጠበቁኝ፤ የጥቢን፡ዝናብ፡እንደሚሹ፡አፋቸውን፡ከፈቱ።

24እነርሱ፡ባልታመኑ፡ጊዜ፡ሣቅኹላቸው፤ የፊቴንም፡ብርሃን፡አላወረዱም።

25መንገዳቸውን፡መረጥኹ፤ እንደ፡አለቃ፡ኾኜ፡ተቀመጥኹ፤ ንጉሥ፡በሰራዊቱ፡መካከል፡እንደሚኖር፥ ሐዘነተኛዎችን፡እንደሚያጽናና፡ኖርኹ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source