Skip to content
← Job

Chapter 28 · Amharic

Job

1በእውነት፡ብር፡የሚወጣበት፥ ወርቅም፡የሚነጠርበት፡ስፍራ፡አለ።

2ብረት፡ከመሬት፡ውስጥ፡ይወሰዳል፤ መዳብም፡ከድንጋይ፡ይቀለጣል።

3ሰው፡ለጨለማ፡ፍጻሜን፡ያደርጋል፤ የጨለማውንና፡የሞት፡ጥላን፡ድንጋይ፡እስከ፡ወሰኑ፡ድረስ፡ይፈላልጋል።

4ሰው፡ከሚኖርበት፡ርቀው፡መውረጃ፡ይቈፍራሉ፤ ከሰውም፡እግር፡ተረሱ፥ ከሰዎችም፡ርቀው፡እየተንጠለጠሉ፡ይወዛወዛሉ።

5እንጀራ፡ከምድር፡ውስጥ፡ይወጣል፤ በእሳትም፡እንደሚኾን፡ታችኛው፡ይገለበጣል።

6ድንጋይዋ፡የሰንፔር፡ስፍራ፡ነው፥ የወርቅም፡ድቃቂ፡አለው።

7መንገዷን፡ጭልፊት፡አያውቀውም፥ የአሞራም፡ዐይን፡አላየውም።

8የትዕቢት፡ልጆች፡አልረገጧትም፥ ደቦል፡አንበሳ፡አላለፈባትም።

9ሰው፡ወደ፡ቡላድ፡ድንጋይ፡እጁን፡ይዘረጋል፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ተራራውንም፡ከመሠረቱ፡ይገለብጣል።

10ከድንጋይ፡ውስጥ፡መንዶልዶያ፡ይወቅራል፤ ዐይኑም፡ዕንቍን፡ዅሉ፡ታያለች።

11ፈሳሹም፡እንዳይንጠባጠብ፡ይገድባል፤ የተሰወረውንም፡ነገር፡ወደ፡ብርሃን፡ያወጣል።

12ነገር፡ግን፥ጥበብ፡የምትገኘው፡ወዴት፡ነው፧ የማስተዋልስ፡ስፍራ፡ወዴት፡ነው፧

13ሰው፡መንገዷን፡አያውቅም፤ በሕያዋን፡ምድር፡አትገኝም።

14ቀላይ፦በእኔ፡ውስጥ፡የለችም፡ይላል፤ ባሕርም፦በእኔ፡ዘንድ፡የለችም፡ይላል።

15በምዝምዝ፡ወርቅ፡አትገኝም፥ ብርም፡ስለ፡ዋጋዋ፡አይመዘንም።

16በኦፊር፡ወርቅ፥ በከበረም፡መረግድና፡በሰንፔር፡አትገመትም።

17ወርቅና፡ብርጭቆ፡አይወዳደሯትም፥ በጥሩ፡ወርቅም፡ዕቃ፡አትለወጥም።

18ስለ፡ዛጐልና፡ስለ፡አልማዝ፡አይነገርም። የጥበብ፡ዋጋ፡ከቀይ፡ዕንቍ፡ይልቅ፡ይበልጣል።

19የኢትዮጵያ፡ቶጳዝዮን፡አይተካከላትም፥ በጥሩም፡ወርቅ፡አትገመትም።

20እንግዲያሳ፡ጥበብ፡ከወዴት፡ትመጣለች፧ የማስተዋልስ፡ስፍራ፡ወዴት፡ነው፧

21ከሕያዋን፡ዅሉ፡ዐይን፡ተሰውራለች፥ ከሰማይ፡ወፎች፡ተሸሽጋለች።

22ጥፋትና፡ሞት፦ወሬዋን፡በዦሮዎቻችን፡ሰማን፡ብለዋል።

23እግዚአብሔር፡መንገዷን፡ያስተውላል፥ ርሱም፡ስፍራዋን፡ያውቃል።

24ርሱም፡የምድርን፡ዳርቻ፡ይመለከታል፥ ከሰማይም፡በታች፡ያለውን፡ዅሉ፡ያያል።

25ለነፋስ፡ሚዛንን፡ባደረገለት፡ጊዜ፥ ውሃዎችንም፡በስፍር፡በሰፈረ፡ጊዜ፥

26ለዝናብም፡ሥርዐትን፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ለነጐድጓድ፡መብረቅም፡መንገድን፡ባደረገ፡ጊዜ፥

27በዚያን፡ጊዜ፡አያት፥ገለጣትም፤ አዘጋጃትም፥ደግሞም፡መረመራት።

28ሰውንም፦እንሆ፥እግዚአብሔርን፡መፍራት፡ጥበብ፡ነው፤ ከኀጢአትም፡መራቅ፡ማስተዋል፡ነው፡አለው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source