1ኢዮብም፡ምሳሌውን፡ይመስል፡ዘንድ፡ደገመ፥እንዲህም፡አለ፦
2ፍርዴን፡ያስወገደ፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! ነፍሴንም፡መራራ፡ያደረገ፡ዅሉን፡የሚችል፡ሕያው፡አምላክን!
3እስትንፋሴ፡በእኔ፡ውስጥ፥ የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡ባፍንጫዬ፡ውስጥ፡ገና፡ሳለ፥
4ከንፈሬ፡ኀጢአትን፡አትናገርም፥ አንደበቴም፡ሽንገላን፡አያወጣም።
5እናንተን፡ማጽደቅ፡ከእኔ፡ዘንድ፡ይራቅ፤ እስክሞት፡ድረስ፡ፍጹምነቴን፡ከእኔ፡አላርቅም።
6ጽድቄን፡እይዛለኹ፡ርሱንም፡አልተውም፤ ከቀኖቼም፡ዅሉ፡ስለ፡አንዱ፡ልቤ፡አይዘልፈኝም።
7ጠላቴ፡እንደ፡በደለኛ፥ በእኔ፡ላይም፡የሚነሣ፡እንደ፡ኀጢአተኛ፡ይኹን።
8እግዚአብሔር፡ባጠፋውና፡ነፍሱን፡በለየ፡ጊዜ፥ የዝንጉ፡ሰው፡ተስፋው፡ምንድር፡ነው፧
9በእውኑ፡መከራ፡በመጣበት፡ጊዜ፥ እግዚአብሔር፡ጩኸቱን፡ይሰማልን፧
10ዅሉንስ፡በሚችል፡አምላክ፡ደስ፡ይለዋልን፧ እግዚአብሔርንስ፡ዅልጊዜ፡ይጠራልን፧
11እኔ፡ስለእግዚአብሔር፡እጅ፡አስተምራችዃለኹ፤ ዅሉን፡በሚችል፡አምላክ፡ዘንድ፡ያለውን፡አልሸሽግም።
12እንሆ፥ዅላችኹ፡አይታችዃል፤ ስለ፡ምን፡ከንቱ፡ኾናችኹ፧
13ይህች፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡የበደለኛ፡ዕድል፡ፈንታ፥ ግፈኛም፡ዅሉን፡ከሚችል፡አምላክ፡ዘንድ፡የሚቀበላት፡ርስት፡ናት፤
14ልጆቹ፡ቢበዙ፡ለሰይፍ፡ይኾናሉ፤ ዘሩም፡እንጀራን፡አይጠግብም።
15ለርሱም፡የቀሩት፡በቸነፈር፡ይቀበራሉ፤ መበለቶቻቸውም፡አያለቅሱም።
16ርሱ፡ብርን፡እንደ፡ዐፈር፡ቢከምር፥ ልብስንም፡እንደ፡ጭቃ፡ቢያዘጋጅ፥
17ርሱ፡ያዘጋጀው፡ይኾናል፥ነገር፡ግን፥ጻድቅ፡ይለብሰዋል፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ብሩንም፡ንጹሓን፡ይከፋፈሉታል።
18የሚሠራው፡ቤት፡እንደ፡ሸረሪት፡ድር፡ይሠራል፥ ጠባቂም፡እንደሚሠራው፡ጐዦ፡ነው።
19ባለጠጋ፡ኾኖ፡ይተኛል፥ዳግመኛም፡አይተኛም፤ ዐይኑን፡ይከፍታል፥ርሱም፡የለም።
20ድንጋጤ፡እንደ፡ጐርፍ፡ታገኘዋለች፤ በሌሊትም፡ዐውሎ፡ነፋስ፡ትነጥቀዋለች።
21የምሥራቅ፡ነፋስ፡ያነሣዋል፥ርሱም፡ይኼዳል፤ ከቦታውም፡ይጠርገዋል።
22ርሱ፡ይጥልበታል፥አይራራለትም፤ ከእጁ፡ፈጥኖ፡መሸሽ፡ይወዳ፟ል።
23ሰው፡በእጁ፡ያጨበጭብበታል፤ ከስፍራውም፡በፉጨት፡ያስወጡታል።