Skip to content
← Job

Chapter 26 · Amharic

Job

1ኢዮብም፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦

2ኀይል፡የሌለውን፡ምንኛ፡ረዳኸው! ብርታት፡የሌለውን፡ክንድ፡ምንኛ፡አዳንኸው!

3ጥበብስ፡የሌለውን፡ምንኛ፡መከርኸው! ብዙ፡ዕውቀትንስ፡ምንኛ፡ገለጥኽለት!

4ይህንስ፡ቃል፡በማን፡ርዳታ፡ተናገርኽ፧ የማንስ፡መንፈስ፡ከአንተ፡ዘንድ፡ወጣ፧

5ሙታን፡ሰዎች፡ከውሃዎች፡በታች፥ በውሃዎችም፡ውስጥ፡ከሚኖሩ፡በታች፡ይንቀጠቀጣሉ።

6ሲኦል፡በፊቱ፡ዕራቍቷን፡ናት፥ ለጥፋትም፡መጋረጃ፡የለውም።

7ሰሜንን፡በባዶ፡ስፍራ፡ላይ፡ይዘረጋል፥ ምድሪቱንም፡በታቿ፡አንዳች፡አልባ፡ያንጠለጥላል።

8ውሃዎችን፡በደመናዎቹ፡ውስጥ፡ያስራል፥ ደመናዪቱም፡ከታች፡አልተቀደደችም።

9የዙፋኑን፡ፊት፡ይከድናል፥ ደመናውንም፡ይዘረጋበታል።

10ብርሃንና፡ጨለማ፡እስከሚለያዩበት፡ዳርቻ፡ድረስ፥ በውሃዎች፡ፊት፡ላይ፡ድንበርን፡አደረገ።

11የሰማይ፡አዕማድ፡ይንቀጠቀጣሉ፥ ከተግሣጹም፡የተነሣ፡ይደነግጣሉ።

12በኀይሉ፡ባሕርን፡ጸጥ፡ያደርጋል፥ በማስተዋሉም፡ረዓብን፡ይመታል።

13በመንፈሱ፡ሰማያት፡ውበትን፡አገኙ፥ እጁም፡በራሪዪቱን፡እባብ፡ወጋች።

14እንሆ፥ይህ፡የመንገዱ፡ዳርቻ፡ብቻ፡ነው፤ ይህም፡የሰማነው፡ነገር፡ምንኛ፡ጥቂት፡ነው! የኀይሉንስ፡ነጐድጓድ፡ያስተውል፡ዘንድ፡ማን፡ይችላል፧ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source