1ሹሐዊውም፡በልዳዶስ፡መለሰ፡እንዲህም፡አለ፦
2ገዢነትና፡መፈራት፡በርሱ፡ዘንድ፡ናቸው፤ በከፍታውም፡ሰላም፡አድራጊ፡ነው።
3በእውኑ፡ለሰራዊቶቹ፡ቍጥር፡አላቸውን፧ ብርሃኑስ፡የማይወጣው፡በማን፡ላይ፡ነው፧
4ሰውስ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ጻድቅ፡ይኾን፡ዘንድ፥ ከሴትስ፡የተወለደ፡ንጹሕ፡ይኾን፡ዘንድ፡እንዴት፡ይችላል፧
5እንሆ፥ጨረቃ፡እንኳ፡ብሩህ፡አይደለም፥ ከዋክብትም፡በፊቱ፡ንጹሓን፡አይደሉም። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
6ይልቁንስ፡ብስብስ፡የኾነ፡ሰው፥ ትልም፡የኾነ፡የሰው፡ልጅ፡ምንኛ፡ያንስ!