Skip to content
← Joel

Chapter 1 · Amharic

Joel

1ወደባቱኤል፡ልጅ፡ወደ፡ኢዮኤል፡የመጣው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ይህ፡ነው፦

2እናንተ፡ሽማግሌዎች፥ይህን፡ስሙ፤በምድርም፡የምትኖሩ፡ዅሉ፥አድምጡ።ይህ፡በዘመናችኹ፡ወይስ፡ በአባቶቻችኹ፡ዘመን፡ኾኖ፡ነበርን፧

3ይህን፡ለልጆቻችኹ፡ንገሩ፤ልጆቻችኹም፡ለልጆቻቸው፥ልጆቻቸውም፡ለዃለኛው፡ትውልድ፡ይንገሩ።

4ከተምች፡የቀረውን፡አንበጣ፡በላው፤ከአንበጣም፡የቀረውን፡ደጐብያ፡በላው፤ከደጐብያም፡የቀረውን፡ ኵብኵባ፡በላው።

5በተሓ፡ወይን፡ጠጃችኹ፡ከአፋችኹ፡ተወግዷልና፥እናንተ፡ሰካራሞች፥ነቅታችኹ፡አልቅሱ፤እናንተም፡ የወይን፡ጠጅ፡የምትጠጡ፡ዅሉ፥ዋይ፡በሉ።

6ቍጥርም፡የሌለው፡ብርቱ፡ሕዝብ፡በምድሬ፡ላይ፡ወጥቷልና፤ጥርሳቸው፡እንደ፡አንበሳ፡ ጥርስ፥መንጋጋቸውም፡እንደ፡እንስቲቱ፡አንበሳ፡መንጋጋ፡ነው።

7ወይኔን፡ባዶ፡ምድር፡አደረገው፥በለሴንም፡ሰበረው፤ባዶም፡አደረገው፥ጣለውም፤ቅርንጫፎቹም፡ነጡ።

8ለቍንዥናዋ፡ባል፡ማቅ፡ለብሳ፡እንደምታለቅስ፡ድንግል፡አልቅሺ።

9የእኽሉ፡ቍርባንና፡የመጠጡ፡ቍርባን፡ከእግዚአብሔር፡ቤት፡ተወግዷል፤የእግዚአብሔርም፡አገልጋዮች፡ ካህናቱ፡አለቀሱ።

10እኽሉ፡ጠፍቷልና፥ወይኑም፡ደርቋልና፥ዘይቱም፡ጐድሏልና፥ዕርሻው፡ምድረ፡በዳ፡ኾኗል፥ምድሪቱም፡ አልቅሳለች።

11መከሩ፡ከዕርሻቸው፡ጠፍቷልና፥ገበሬዎች፡ስለ፡ስንዴውና፡ስለ፡ገብሱ፡ዐፈሩ፤የወይን፡አትክልተኛዎችም፡ አለቀሱ።

12ወይኑ፡ደርቋል፥በለሱም፡ጠውልጓል፤ሮማኑና፡ተምሩ፡እንኰዩም፡የምድርም፡ዛፎች፡ዅሉ፡ ደርቀዋል፤ደስታም፡ከሰው፡ልጆች፡ዘንድ፡ርቋል።

13የእኽሉ፡ቍርባንና፡የመጠጡ፡ቍርባን፡ከአምላካችኹ፡ቤት፡ቀርቷልና፥እናንተ፡ካህናት፥ማቅ፡ ታጥቃችኹ፡አልቅሱ፤እናንተም፡የመሠዊያ፡አገልጋዮች፥ዋይ፡በሉ፤እናንተ፡የአምላኬ፡ አገልጋዮች፥ኑ፥ሌሊቱን፡ዅሉ፡በማቅ፡ላይ፡ተኙ።

14ጾምን፡ቀድሱ፥ጉባኤውንም፡ዐውጁ፤ሽማግሌዎችንና፡በምድር፡የሚኖሩትን፡ዅሉ፡ወደ፡አምላካችኹ፡ ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ሰብስቡ፥ወደ፡እግዚአብሔርም፡ጩኹ።

15የእግዚአብሔር፡ቀን፡ቀርቧልና፥ለቀኑ፡ወዮ! ርሱም፡ዅሉን፡ከሚችል፡ከአምላክ፡ዘንድ፡እንደ፡ጥፋት፡ ይመጣል።

16ከዐይናችን፡ፊት፡ምግብ፥ከአምላካችንም፡ቤት፡ደስታና፡እልልታ፡የጠፋ፡አይደለምን፧

17ዘሩ፡በምድር፡ውስጥ፡በሰበሰ፤እኽሉ፡ደርቋልና፥ጐተራዎቹ፡ባዶ፡ናቸው፥ጐታዎቹም፡ፈርሰዋል።

18እንስሳዎች፡እጅግ፡ጮኹ፤የላምም፡መንጋዎች፡ማሰማሪያ፡የላቸውምና፡ተጠራጠሩ፤የበግም፡መንጋዎች፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ጠፍተዋል።

19አቤቱ፥እሳት፡የምድረ፡በዳውን፡ማሰማሪያ፡በልቷልና፥ነበልባሉም፡የዱሩን፡ዛፍ፡ዅሉ፡ አቃጥሏልና፥ወዳንተ፡እጮኻለኹ።

20ፈሳሹ፡ውሃ፡ደርቋልና፥እሳቱም፡የምድረ፡በዳውን፡ማሰማሪያ፡በልቷልና፥የምድር፡አራዊት፡ወዳንተ፡ አለከለኩ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source