Skip to content
← Joel

Chapter 2 · Amharic

Joel

1የእግዚአብሔር፡ቀን፡መጥቷልና፥ርሱም፡ቀርቧልና፥በጽዮን፡መለከትን፡ንፉ፥በቅዱሱም፡ተራራዬ፡ላይ፡ እሪ፡በሉ፤በምድርም፡የሚኖሩ፡ዅሉ፡ይንቀጥቀጡ፤የእግዚአብሔር፡ቀን፡መጥቷልና፤

2የጨለማና፡የጭጋግ፡ቀን፥የደመናና፡የድቅድቅ፡ጨለማ፡ቀን፡ነው፤ታላቅና፡ብርቱ፡ሕዝብ፡በተራራዎች፡ ላይ፡እንደ፡ወገግታ፡ተዘርግቷል፤ከዘለዓለምም፡ዠምሮ፡እንደ፡እነርሱ፡ያለ፡አልነበረም፥ከነርሱም፡በዃላ፡ እስከ፡ብዙ፡ትውልድ፡ድረስ፡እንደ፡እነርሱ፡ያለ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አይኾንም።

3እሳት፡በፊታቸው፡ትባላለች፥በዃላቸውም፡ነበልባል፡ታቃጥላለች፤ምድሪቱ፡በፊታቸው፡እንደ፡ዔዴን፡ ገነት፥በዃላቸውም፡የምድረ፡በዳ፡በረሓ፡ናት፤ከነርሱም፡የሚያመልጥ፡የለም።

4መልካቸው፡እንደ፡ፈረስ፡መልክ፡ነው፥እንደ፡ፈረሶችም፡ይሮጣሉ።

5በተራራ፡ላይ፡እንዳሉ፡ሠረገላዎች፡ድምፅ፥ገለባውንም፡እንደሚበላ፡እንደ፡እሳት፡ነበልባል፡ ድምፅ፥ለሰልፍም፡እንደ፡ተዘጋጀ፡እንደ፡ብርቱ፡ሕዝብ፡ያኰበኵባሉ።

6ከፊታቸው፡አሕዛብ፡ይንቀጠቀጣሉ፤የሰውም፡ፊት፡ዅሉ፡ይጠቍራል።

7እንደ፡ኀያላን፡ይሮጣሉ፥እንደ፡ሰልፈኛዎችም፡በቅጥሩ፡ላይ፡ይወጣሉ፤እያንዳንዱም፡በመንገዱ፡ላይ፡ ይራመዳል፥ከርምጃቸውም፡አያፈገፍጉም።

8አንዱ፡ካንዱ፡ጋራ፡አይጋፉም፥እያንዳንዱም፡መንገዱን፡ይጠበጥባል፤በሰልፍ፡መካከል፡ ያልፋሉ፥እነርሱም፡አይቈስሉም።

9በከተማም፡ያኰበኵባሉ፥በቅጥሩም፡ላይ፡ይሮጣሉ፤ወደ፡ቤቶችም፡ይወጣሉ፥እንደ፡ሌባም፡በመስኮቶች፡ ይገባሉ።

10ምድሪቱም፡ከፊታቸው፡ትናወጣለች፥ሰማያትም፡ይንቀጠቀጣሉ፤ፀሓይና፡ጨረቃም፡ ይጨልማሉ፥ከዋክብትም፡ብርሃናቸውን፡ይሰውራሉ።

11እግዚአብሔርም፡በሰራዊቱ፡ፊት፡ድምፁን፡ይሰጣል፤ሰፈሩ፡እጅግ፡ብዙ፡ነውና፥ቃሉንም፡የሚያደርግ፡ ርሱ፡ኀያል፡ነውና፤የእግዚአብሔርም፡ቀን፡ታላቅና፡እጅግ፡የሚያስፈራ፡ነውና፥ማንስ፡ይችለዋል፧

12አኹንስ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥በፍጹም፡ልባችኹ፥በጾምም፥በልቅሶና፡በዋይታ፡ወደ፡እኔ፡ተመለሱ።

13ልባችኹን፡እንጂ፡ልብሳችኹን፡አትቅደዱ፤አምላካችኹም፡እግዚአብሔር፡ቸርና፡መሓሪ፥ቍጣው፡ የዘገየ፥ምሕረቱም፡የበዛ፥ለክፋትም፡የተጸጸተ፡ነውና፥ወደ፡ርሱ፡ተመለሱ።

14የሚመለስና፡የሚጸጸት፡እንደ፡ኾነ፥ለአምላካችኹም፡ለእግዚአብሔር፡የእኽልና፡የመጠጥ፡ቍርባን፡ የሚኾነውን፡በረከት፡የሚያተርፍ፡እንደ፡ኾነ፡ማን፡ያውቃል፧

15በጽዮን፡መለከትን፡ንፉ፥ጾምንም፡ቀድሱ፥ጉባኤውንም፡ዐውጁ፥

16ሕዝቡንም፡አከማቹ፥ማኅበሩንም፡ቀድሱ፥ሽማግሌዎቹንም፡ሰብስቡ፥ሕፃናቱንና፡ጡት፡የሚጠቡትን፡ አከማቹ፤ሙሽራው፡ከዕልፍኙ፥ሙሽራዪቱም፡ከጫጕላዋ፡ይውጡ።

17የእግዚአብሔርም፡አገልጋዮች፡ካህናት፡ከወለሉና፡ከመሠዊያው፡መካከል፡እያለቀሱ፦አቤቱ፥ለሕዝብኽ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ራራ፥አሕዛብም፡እንዳይነቅፏቸው፡ርስትኽን፡ለማላገጫ፡አሳልፈኽ፡አትስጥ፤ከአሕዛብ፡መካከል፦አምላካቸው፡ ወዴት፡ነው፧ስለ፡ምን፡ይላሉ፧ይበሉ።

18እግዚአብሔርም፡ስለ፡ምድሩ፡ቀና፥ለሕዝቡም፡ራራለት።

19እግዚአብሔርም፡መልሶ፡ሕዝቡን፦እንሆ፥እኽልንና፡ወይንን፡ዘይትንም፡እሰድ፟ላችዃለኹ፥እናንተም፡ በርሱ፡ትጠግባላችኹ፤ከእንግዲህም፡ወዲያ፡በአሕዛብ፡መካከል፡መሰደቢያ፡አላደርጋችኹም።

20የሰሜንንም፡ሰራዊት፡ከእናንተ፡ዘንድ፡አርቃለኹ፥ወደ፡በረሓና፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፥ፊቱን፡ወደምሥራቁ፡ ባሕር፡ዠርባውንም፡ወደምዕራቡ፡ባሕር፡አድርጌ፡አሳድደዋለኹ፤ርሱም፡ትዕቢትን፡አድርጓልና፥ግማቱ፡ ይወጣል፥ክርፋቱም፡ይነሣል፡አለ።

21ምድር፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ታላቅ፡ነገር፡አድርጓልና፥አትፍሪ፥ደስም፡ይበልሽ፥እልልም፡በዪ።

22እናንተ፡የምድር፡እንስሳዎች፡ሆይ፥የምድረ፡በዳው፡ማሰማሪያ፡ለምልሟልና፥ዛፉም፡ፍሬውን፡ አፍርቷልና፥በለሱና፡ወይኑም፡ኀይላቸውን፡ሰጥተዋልና፥አትፍሩ።

23እናንተ፡የጽዮን፡ልጆች፥አምላካችኹ፡እግዚአብሔር፡የፊተኛውን፡ዝናብ፡በጽድቅ፡ሰጥቷችዃልና፥እንደ፡ ቀድሞውም፡የፊተኛውንና፡የዃለኛውን፡ዝናብ፡አዝንቦላችዃልና፥በርሱ፡ደስ፡ይበላችኹ፥ለርሱም፡እልል፡በሉ።

24ዐውድማዎችም፡እኽልን፡ይሞላሉ፥መጥመቂያዎችም፡የወይን፡ጠጅንና፡ዘይትን፡አትረፍርፈው፡ያፈሳ፟ሉ።

25የሰደድኹባችኹ፡ታላቁ፡ሰራዊቴ፡አንበጣና፡ደጐብያ፡ኵብኵባና፡ተምች፡የበላቸውን፡ዓመታት፡ እመልስላችዃለኹ።

26ብዙ፡መብል፡ትበላላችኹ፥ትጠግቡማላችኹ፤ከእናንተም፡ጋራ፡ተኣምራትን፡የሠራውን፡የአምላካችኹን፡ የእግዚአብሔርን፡ስም፡ታመሰግናላችኹ፤ሕዝቤም፡ለዘለዓለም፡አያፍርም።

27እኔም፡በእስራኤል፡መካከል፡እንዳለኹ፥እኔም፡አምላካችኹ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፥ከእኔም፡በቀር፡ ሌላ፡አምላክ፡እንደሌለ፡ታውቃላችኹ፤ሕዝቤም፡ለዘለዓለም፡አያፍርም።

28ከዚህም፡በዃላ፡እንዲህ፡ይኾናል፤መንፈሴን፡በሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡ላይ፡አፈሳ፟ለኹ፤ወንዶችና፡ሴቶች፡ ልጆቻችኹም፡ትንቢት፡ይናገራሉ፥ሽማግሌዎቻችኹም፡ሕልምን፡ያልማሉ፥ጐበዞቻችኹም፡ራእይ፡ያያሉ፤

29ደግሞም፡በዚያ፡ወራት፡በወንዶችና፡በሴቶች፡ባሪያዎች፡ላይ፡መንፈሴን፡አፈሳ፟ለኹ፤

30በላይ፡በሰማይ፡ድንቆችን፡አሳያለኹ፥በታች፡በምድርም፡ደምና፣እሳት፣የጢስም፡ጭጋግ።

31ታላቁና፡የሚያስፈራው፡የእግዚአብሔር፡ቀን፡ሳይመጣ፡ፀሓይ፡ወደ፡ጨለማ፥ጨረቃም፡ወደ፡ደም፡ ይለወጣል።

32እንዲህም፡ይኾናል፤የእግዚአብሔር፡ስም፡የሚጠራ፡ዅሉ፡ይድናል፤እግዚአብሔርም፡እንደ፡ ተናገረ፥በጽዮን፡ተራራና፡በኢየሩሳሌም፡መድኀኒት፡ይገኛል።ደግሞም፡እግዚአብሔር፡የጠራቸው፥የምሥራች፡ የሚሰበከላቸው፡ይገኛሉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source