1እንሆም፥በዚያ፡ወራትና፡በዚያ፡ዘመን፥የይሁዳንና፡የኢየሩሳሌምን፡ምርኮ፡በምመልስበት፡ጊዜ፥
2አሕዛብን፡ዅሉ፡ሰብስቤ፡ወደኢዮሳፍጥ፡ሸለቆ፡አወርዳቸዋለኹ፤በዚያም፡ስለ፡ሕዝቤና፡ስለ፡ርስቴ፡ስለ፡ እስራኤል፡በአሕዛብ፡መካከል፡የበተኗቸውን፡ምድሬንም፡የተካፈሏትን፡እፋረድባቸዋለኹ።
3በሕዝቤም፡ላይ፡ዕጣ፡ተጣጣሉ፤ወንድ፡ልጅን፡ለጋለሞታ፡ዋጋ፡ሰጡ፥ሴት፡ልጅን፡ለወይን፡ጠጅ፡ ሸጡ፥ጠጡም።
4ጢሮስና፡ሲዶና፡የፍልስጥኤምም፡ግዛት፡ዅሉ፡ሆይ፥ከእናንተ፡ጋራ፡ለእኔ፡ምን፡አለኝ፧በእውኑ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ብድራትን፡ትመልሱልኛላችኹን፧ብድራትን፡ብትመልሱልኝ፡ፈጥኜ፡በችኰላ፡ብድራታችኹን፡በራሳችኹ፡ላይ፡ እመልሳለኹ።
5ብሬንና፡ወርቄን፡ወስዳችዃልና፥የተወደደውንም፡መልካሙን፡ዕቃዬን፡ወደ፡መቅደሳችኹ፡ አግብታችዃልና፥
6ከዳርቻቸውም፡ታርቋቸው፡ዘንድ፡የይሁዳንና፡የኢየሩሳሌምን፡ልጆች፡ለግሪክ፡ሰዎች፡ሸጣችዃልና፥
7እንሆ፥እነርሱን፡ከሸጣችኹበት፡ስፍራ፡አስነሣቸዋለኹ፥ብድራታችኹንም፡በራሳችኹ፡ላይ፡እመልሳለኹ።
8እግዚአብሔር፡ተናግሯልና፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻችኹን፡በይሁዳ፡ልጆች፡እጅ፡እሸጣለኹ፥እነርሱም፡ ለሩቆቹ፡ሕዝብ፡ለሳባ፡ሰዎች፡ይሸጧችዃል።
9ይህን፡በአሕዛብ፡መካከል፡ዐውጁ፡ለሰልፍ፡ተዘጋጁ፡ኀያላንን፡አስነሡ፡ሰልፈኛዎች፡ዅሉ፡ይቅረቡ፡ ይውጡም።
10ማረሻችኹን፡ሰይፍ፥ማጭዳችኹንም፡ጦር፡ለማድረግ፡ቀጥቅጡ፤ደካማውም፦እኔ፡ብርቱ፡ነኛ፡ይበል።
11እናንተ፡በዙሪያ፡ያላችኹ፡አሕዛብ፡ዅሉ፥ቸኵላችኹ፡ኑ፥ተሰብሰቡ፤አቤቱ፥ኀያላንኽን፡ወደዚያ፡ አውርድ።
12አሕዛብ፡ይነሡ፥ወደኢዮሳፍጥ፡ሸለቆም፡ይውጡ፤በዙሪያ፡ባሉ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ላይ፡እፈርድ፡ዘንድ፡ በዚያ፡እቀመጣለኹና።
13መከሩ፡ደርሷልና፥ማጭድ፡ስደዱ፤መጥመቂያውም፡ሞልቷልና፥ኑ፡ርገጡ፤ክፋታቸውም፡ በዝቷልና፥መጥመቂያ፡ዅሉ፡ፈርሷል።
14የእግዚአብሔር፡ቀን፡በፍርድ፡ሸለቆ፡ቀርቧልና፥የብዙ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ውካታ፡በፍርድ፡ሸለቆ፡አለ።
15ፀሓይና፡ጨረቃ፡ጨልመዋል፥ከዋክብትም፡ብርሃናቸውን፡ሰውረዋል።
16እግዚአብሔርም፡በጽዮን፡ኾኖ፡ድምፁን፡ከፍ፡አድርጎ፡ይጮኻል፥በኢየሩሳሌምም፡ኾኖ፡ቃሉን፡ ይሰጣል፤ሰማይና፡ምድርም፡ይናወጣሉ፤እግዚአብሔር፡ግን፡ለሕዝቡ፡መሸሸጊያ፥ለእስራኤልም፡ልጆች፡ መጠጊያ፡ይኾናል።
17እኔም፡በተቀደሰው፡ተራራዬ፡በጽዮን፡የምቀመጥ፡አምላካችኹ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኹ፡ ታውቃላችኹ፤የዚያን፡ጊዜም፡ኢየሩሳሌም፡የተቀደሰች፡ትኾናለች፥እንግዳዎችም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ አያልፉባትም።
18በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤ተራራዎች፡በተሓ፡ጠጅ፡ያንጠባጥባሉ፥ኰረብታዎችም፡ወተትን፡ ያፈሳ፟ሉ፥በይሁዳም፡ያሉት፡ፈፋዎች፡ዅሉ፡ውሃን፡ያጐርፋሉ፡ከእግዚአብሔርም፡ቤት፡ምንጭ፡ ትፈልቃለች፥የሰጢምንም፡ሸለቆ፡ታጠጣለች።
19በአገራቸው፡ንጹሑን፡ደም፡አፍሰ፟ዋልና፥በይሁዳ፡ልጆች፡ላይ፡ስላደረጉት፡ግፍ፡ግብጽ፡ምድረ፡ በዳ፥ኤዶምያስም፡በረሓ፡ይኾናል።
20ነገር፡ግን፥ይሁዳ፡ለዘለዓለም፥ኢየሩሳሌምም፡ለልጅ፡ልጅ፡መኖሪያ፡ይኾናል።
21እኔም፡ንጹሕ፡ያላደረግኹትን፡ደማቸውን፡ንጹሕ፡አደርገዋለኹ፥እግዚአብሔርም፡በጽዮን፡ያድራል፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org