1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደዐማቴ፡ልጅ፡ወደ፡ዮናስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2ተነሥተኽ፡ወደዚያች፡ወደ፡ታላቂቱ፡ከተማ፡ወደ፡ነነዌ፡ኺድ፥ክፋታቸውም፡ወደ፡ፊቴ፡ ወጥቷልና፥በርሷ፡ላይ፡ስበክ።
3ዮናስ፡ግን፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፡ወደ፡ተርሴስ፡ይኰበልል፡ዘንድ፡ተነሣ፤ወደ፡ኢዮጴም፡ወረደ፥ወደ፡ ተርሴስም፡የምታልፍ፡መርከብ፡አገኘ፤ከእግዚአብሔርም፡ፊት፡ኰብሎ፟፡ከነርሱ፡ጋራ፡ወደ፡ተርሴስ፡ይኼድ፡ ዘንድ፡ዋጋ፡ሰጥቶ፡ወደ፡ርሷ፡ገባ።
4እግዚአብሔርም፡በባሕሩ፡ላይ፡ታላቅ፡ነፋስን፡አመጣ፥በባሕርም፡ላይ፡ታላቅ፡ማዕበል፡ኾነ፥መርከቢቱም፡ ልትሰበር፡ቀረበች።
5መርከበኛዎቹም፡ፈሩ፥እያንዳንዱም፡ወደ፡አምላኩ፡ጮኸ፤መርከቢቱም፡እንድትቀል፟ላቸው፡በውስጧ፡ የነበረውን፡ዕቃ፡ወደ፡ባሕር፡ጣሉት፤ዮናስ፡ግን፡ወደ፡መርከቡ፡ውስጠኛው፡ክፍል፡ወርዶ፡ነበር፥በከባድ፡ እንቅልፍም፡ተኝቶ፡ነበር።
6የመርከቡም፡አለቃ፡ወደ፡ርሱ፡ቀርቦ፦ምነው፡ተኝተኻል፧እንዳንጠፋ፡እግዚአብሔር፡ያስበን፡እንደ፡ኾነ፡ ተነሥተኽ፡አምላክኽን፡ጥራ፡አለው።
7ርስ፡በርሳቸውም፦ይህ፡ክፉ፡ነገር፡በማን፡ምክንያት፡እንዳገኘን፡እናውቅ፡ዘንድ፡ኑ፥ዕጣ፡እንጣጣል፡ ተባባሉ።ዕጣም፡ተጣጣሉ፥ዕጣውም፡በዮናስ፡ላይ፡ወደቀ።
8የዚያን፡ጊዜም፦ይህ፡ክፉ፡ነገር፡በማን፡ምክንያት፡እንዳገኘን፡እባክኽ፡ንገረን፤ሥራኽ፡ምንድር፡ ነው፧ከወዴትስ፡መጣኽ፧አገርኽስ፡ወዴት፡ነው፧ወይስ፡ከማን፡ወገን፡ነኽ፧አሉት።
9ርሱም፦እኔ፡ዕብራዊ፡ነኝ፤ባሕሩንና፡የብሱን፡የፈጠረውን፡የሰማይን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ አመልካለኹ፡አላቸው።
10እነዚያም፡ሰዎች፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፡እንደ፡ኰበለለ፡ርሱ፡ስለ፡ነገራቸው፡ዐውቀዋልና፥እጅግ፡ ፈርተው፦ይህ፡ያደረግኸው፡ምንድር፡ነው፧አሉት።
11ባሕሩንም፡ሞገዱ፡አጥብቆ፡ያናውጠው፡ነበርና፦ባሕሩ፡ከእኛ፡ዘንድ፡ጸጥ፡እንዲል፡ምን፡ እናድርግብኽ፧አሉት።
12ርሱም፦ይህ፡ታላቅ፡ማዕበል፡በእኔ፡ምክንያት፡እንዳገኛችኹ፡ዐውቃለኹና፡አንሥታችኹ፡ወደ፡ባሕር፡ ጣሉኝ፥ባሕሩም፡ጸጥ፡ይልላችዃል፡አላቸው።
13ሰዎቹ፡ግን፡ወደ፡ምድሩ፡ሊመለሱ፡አጥብቀው፡ቀዘፉ፤ዳሩ፡ግን፡ባሕሩ፡እጅግ፡አብዝቶ፡ይናወጥባቸው፡ ነበርና፥አልቻሉም።
14ስለዚህ፥ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኸው፦አቤቱ፥እንደ፡ወደድኽ፡ አድርገኻልና፥እንለምንኻለን፤አቤቱ፥ስለዚህ፡ሰው፡ነፍስ፡እንዳንጠፋ፡ንጹሕም፡ደም፡በእኛ፡ላይ፡ እንዳታደርግ፡እንለምንኻለን፡አሉ።
15ዮናስንም፡ወስደው፡ወደ፡ባሕሩ፡ጣሉት፤ባሕሩም፡ከመናወጡ፡ጸጥ፡አለ።
16ሰዎችም፡እግዚአብሔርን፡እጅግ፡ፈሩ፥ለእግዚአብሔርም፡መሥዋዕትን፡አቀረቡ፥ስእለትንም፡ተሳሉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org