Skip to content
← Jonah

Chapter 2 · Amharic

Jonah

1እግዚአብሔርም፡ዮናስን፡የሚውጥ፡ታላቅ፡ዓሣ፡አሰናዳ፤ዮናስም፡ሦስት፡ቀንና፡ሦስት፡ሌሊት፡በዓሣው፡ ሆድ፡ውስጥ፡ነበረ።

2ዮናስም፡በዓሣው፡ሆድ፡ውስጥ፡ኾኖ፡ወደ፡አምላኩ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸለየ፥እንዲህም፡አለ፦

3በመከራዬ፡ሳለኹ፡ወደ፡አምላኬ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኽኹ፥ርሱም፡ሰማኝ፤በሲኦልም፡ሆድ፡ውስጥ፡ ኾኜ፡ጮኽኹ፥ቃሌንም፡አዳመጥኽ።

4ወደ፡ጥልቁ፡ወደ፡ባሕሩ፡ውስጥ፡ጣልኸኝ፥ፈሳሾችም፡በዙሪያዬ፡ነበሩ፤ማዕበልኽና፡ሞገድኽ፡ዅሉ፡ በላዬ፡ዐለፉ።

5እኔም፦ከዐይንኽ፡ፊት፡ተጣልኹ፤ነገር፡ግን፥ወደ፡ቅዱስ፡መቅደስኽ፡ደግሞ፡እመለከታለኹ፡አልኹ።

6ውሃዎችም፡እስከ፡ነፍሴ፡ድረስ፡ከበቡኝ፤ጥልቁ፡ባሕር፡በዙሪያዬ፡ነበረ፤የባሕሩ፡ሣር፡በራሴ፡ተጠምጥሞ፡ ነበር።

7ወደተራራዎች፡መሠረት፡ወረድኹ፤በምድርና፡በመወርወሪያዎቿ፡ለዘለዓለም፡ተዘጋኹ፤አንተ፡ግን፥አቤቱ፡ አምላኬ፥ሕይወቴን፡ከጕድጓዱ፡አወጣኽ።

8ነፍሴ፡በዛለችብኝ፡ጊዜ፡እግዚአብሔርን፡ዐሰብኹት፤ጸሎቴም፡ወዳንተ፡ወደ፡ቅዱስ፡መቅደስኽ፡ገባች።

9ከንቱነትንና፡ሐሰትን፡የሚጠብቁ፡ምሕረታቸውን፡ትተዋል።

10እኔ፡ግን፡በምስጋና፡ቃል፡እሠዋልኻለኹ፤የተሳልኹትንም፡እከፍላለኹ።ደኅንነት፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ ነው።

11እግዚአብሔርም፡ዓሣውን፡አዘዘው፥ርሱም፡ዮናስን፡በየብስ፡ላይ፡ተፋው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source