1የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ኹለተኛ፡ወደ፡ዮናስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2ተነሥተኽ፡ወደዚያች፡ወደ፡ታላቂቱ፡ከተማ፡ወደ፡ነነዌ፡ኺድ፥የምነግርኽንም፡ስብከት፡ስበክላት፡አለው።
3ዮናስም፡ተነሥቶ፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ነነዌ፡ኼደ፤ነነዌም፡የሦስት፡ቀን፡መንገድ፡ያኽል፡ እጅግ፡ታላቅ፡ከተማ፡ነበረች።
4ዮናስም፡የአንድ፡ቀን፡መንገድ፡ያኽል፡ወደ፡ከተማዪቱ፡ውስጥ፡ሊገባ፡ዠመረ፤ጮኾም፦በሦስት፡ቀን፡ ውስጥ፡ነነዌ፡ትገለበጣለች፡አለ።
5የነነዌም፡ሰዎች፡እግዚአብሔርን፡አመኑ፤ለጾም፡ዐዋጅ፡ነገሩ፥ከታላቁም፡ዠምሮ፡እስከ፡ታናሹ፡ድረስ፡ ማቅ፡ለበሱ።
6ወሬውም፡ወደነነዌ፡ንጉሥ፡ደረሰ፤ርሱም፡ከዙፋኑ፡ተነሥቶ፡መጐናጸፊያውን፡አወለቀ፡ማቅም፡ ለበሰ፥በዐመድም፡ላይ፡ተቀመጠ።
7ዐዋጅም፡አስነገረ፥በነነዌም፡ውስጥ፡የንጉሡንና፡የመኳንንቱን፡ትእዛዝ፡አሳወጀ፥እንዲህም፡አለ፦ሰዎችና፡ እንስሳዎች፡ላሞችና፡በጎች፡አንዳችን፡አይቅመሱ፤አይሰማሩም፡ውሃንም፡አይጠጡ፤
8ሰዎችና፡እንስሳዎችም፡በማቅ፡ይከደኑ፥ወደ፡እግዚአብሔርም፡በብርቱ፡ይጩኹ፤ሰዎችም፡ዅሉ፡ከክፉ፡ መንገዳቸውና፡በእጃቸው፡ካለው፡ግፍ፡ይመለሱ።
9እኛ፡እንዳንጠፋ፡እግዚአብሔር፡ተመልሶ፡ይጸጸት፡እንደ፡ኾነ፥ከጽኑ፡ቍጣውም፡ይመለስ፡እንደ፡ኾነ፡ ማን፡ያውቃል፧ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
10እግዚአብሔርም፡ከክፉ፡መንገዳቸው፡እንደተመለሱ፡ሥራቸውን፡አየ፤እግዚአብሔርም፡ያደርግባቸው፡ ዘንድ፡በተናገረው፡ክፉ፡ነገር፡ተጸጽቶ፡አላደረገውም።