1ይህም፡ዮናስን፡ከቶ፡ደስ፡አላሠኘውም፥ርሱም፡ተቈጣ።
2ወደ፡እግዚአብሔርም፡ጸለየና፦አቤቱ፥እለምንኻለኹ፤በአገሬ፡ሳለኹ፡የተናገርኹት፡ይህ፡ አልነበረምን፧አንተ፡ቸርና፡ይቅር፡ባይ፥ታጋሽም፥ምሕረትኽም፡የበዛ፥ከክፉው፡ነገርም፡የተነሣ፡የምትጸጸት፡ አምላክ፡እንደ፡ኾንኽ፡ዐውቄ፡ነበርና፥ስለዚህ፡ወደ፡ተርሴስ፡ለመኰብለል፡ፈጥኜ፡ነበር።
3አኹንም፥አቤቱ፥ከሕይወት፡ሞት፡ይሻለኛልና፥እባክኽ፥ነፍሴን፡ከእኔ፡ውሰድ፡አለው።
4እግዚአብሔርም፦በእውኑ፡ትቈጣ፡ዘንድ፡ይገ፟ባኻ ፟ ልን፧አለ።
5ዮናስም፡ከከተማዪቱ፡ወጣ፥ከከተማዪቱም፡በስተምሥራቅ፡በኩል፡ተቀመጠ፤ከተማዪቱንም፡የሚያገኛትን፡ እስኪያይ፡ድረስ፡በዚያ፡ለራሱ፡ዳስ፡ሠርቶ፡ከጥላው፡በታች፡ተቀመጠ።
6እግዚአብሔር፡አምላክም፡ቅል፡አዘጋጀ፥ከጭንቀቱም፡ታድነው፡ዘንድ፡በራሱ፡ላይ፡ጥላ፡እንድትኾን፡ በዮናስ፡ላይ፡ከፍ፡ከፍ፡አደረጋት፤ዮናስም፡ስለ፡ቅሊቱ፡እጅግ፡ደስ፡አለው።
7በነጋው፡ግን፡ወገግ፡ባለ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ትልን፡አዘጋጀ፥ርሷም፡ቅሊቱን፡እስክትደርቅ፡ድረስ፡ መታቻት።
8ፀሓይም፡በወጣች፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ትኵስ፡የምሥራቅ፡ነፋስ፡አዘጋጀ፡ዮናስ፡እስኪዝል፡ድረስም፡ፀሓይ፡ ራሱን፡መታው፤ለራሱም፡ሞትን፡ፈለገና፦ከሕይወት፡ሞት፡ይሻለኛል፡አለ።
9እግዚአብሔርም፡ዮናስን፦በእውኑ፡ስለዚች፡ቅል፡ትቈጣ፡ዘንድ፡ይገ፟ባኻ ፟ ልን፧አለው።ርሱም፦እስከ፡ ሞት፡ድረስ፡እቈጣ፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟ኛል፡አለ።
10እግዚአብሔርም፦አንተ፡ትበቅል፡ዘንድ፡ላልደከምኽባት፡ላላሳደግኻትም፥ባንድ፡ሌሊት፡ለበቀለች፥ባንድ፡ ሌሊትም፡ለደረቀችው፡ቅል፡አዝነኻል።
11እኔስ፡ቀኛቸውንና፡ግራቸውን፡የማይለዩ፡ከመቶ፡ኻያ፡ሺሕ፡የሚበልጡ፡ሰዎችና፡ብዙ፡እንስሳዎች፡ ላሉባት፡ለታላቂቱ፡ከተማ፡ለነነዌ፡አላዝንምን፧አለው፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org