1አሌፍ።ሕዝብ፡ሞልቶባት፡የነበረች፡ከተማ፡ብቻዋን፡እንዴት፡ተቀመጠች! በአሕዛብ፡መካከል፡ታላቅ፡ የነበረች፡እንደ፡መበለት፡ኾናለች፤በአውራጃዎች፡መካከል፡ልዕልት፡የነበረች፡ተገዢ፡ኾናለች።
2ቤት።በሌሊት፡እጅግ፡ታላቅሳለች፥እንባዋም፡በጕንጯ፡ላይ፡አለ፤ከውሽማዎቿ፡ዅሉ፡የሚያጽናናት፡ የለም፤ወዳጆቿ፡ዅሉ፡ወነጀሏት፡ጠላቶችም፡ኾኗት።
3ጋሜል።ይሁዳ፡ስለመጨነቅና፡ስለባርነት፡ብዛት፡ተማረከች፤በአሕዛብ፡መካከል፡ተቀመጠች፡ዕረፍትም፡ አላገኘችም፤የሚያስጨንቋት፡ዅሉ፡ተጨንቃ፡አገኟት።
4ዳሌጥ።ወደ፡ዓመት፡በዓልም፡የሚመጣ፡የለምና፡የጽዮን፡መንገዶች፡አለቀሱ፤በሮቿ፡ዅሉ፡ፈርሰዋል፡ ካህናቷም፡እየጮኹ፡ያለቅሳሉ፤ደናግሎቿም፡ተጨነቁ፡ርሷም፡በምሬት፡አለች።
5ሄ።ስለኀጢአቷ፡ብዛት፡እግዚአብሔር፡አስጨንቋታልና፥አስጨናቂዎቿ፡ራስ፡ኾኑ፥ጠላቶቿም፡ ተከናወነላቸው፤ሕፃናቷ፡ባስጨናቂዎች፡ፊት፡ተማርከዋል።
6ዋው።ከጽዮን፡ሴት፡ልጅ፡ውበቷ፡ዅሉ፡ወጥቷል፤አለቃዎቿ፡ማሰማሪያ፡እንደማያገኙ፡ዋላዎች፡ ኾኑ፤ከሚያባርሯቸው፡ፊት፡ተዳክመው፡ኼዱ።
7ዛይ።ኢየሩሳሌም፡በጭንቀቷና፡በመከራዋ፡ወራት፡ከጥንት፡ዠምሮ፡የነበረላትን፡የከበረን፡ነገር፡ዅሉ፡ ዐሰበች፤ሕዝቧ፡በአስጨናቂዎች፡እጅ፡በወደቀ፡ጊዜ፡የሚረዳትም፡በሌላት፡ጊዜ፥አስጨናቂዎች፡አይዋት፡ በመፍረሷም፡ሣቁ።
8ሔት።ኢየሩሳሌም፡እጅግ፡ኀጢአት፡ሠርታለች፤ስለዚህ፥ረክሳለች፤ያከብሯት፡የነበሩ፡ዅሉ፡ኀፍረተ፡ ሥጋዋን፡አይተዋታልና፥አቃለሏት፤ርሷም፡እየጮኸች፡ታለቅሳለች፥ወደ፡ዃላም፡ዘወር፡አለች።
9ጤት።አደፏ፡በልብሷ፡ዘርፍ፡ነበረ፤ፍጻሜዋን፡አላሰበችም፤ስለዚህ፥በድንቅ፡ተዋርዳለች፥የሚያጽናናትም፡ የለም፤አቤቱ፥ጠላት፡ከፍ፡ከፍ፡ብሏልና፥መከራዬን፡ተመልከት።
10ዮድ።አስጨናቂው፡በከበረ፡ነገሯ፡ዅሉ፡ላይ፡እጁን፡ዘረጋ፤ወደ፡ጉባኤኽ፡እንዳይገቡ፡ያዘዝኻቸው፡ አሕዛብ፡ወደ፡መቅደሷ፡ሲገቡ፡አይታለችና።
11ካፍ።ሕዝቧ፡ዅሉ፡እየጮኹ፡ያለቅሳሉ፡እንጀራም፡ይፈልጋሉ፤ሰውነታቸውን፡ለማበርታት፡የከበረ፡ ሀብታቸውን፡ስለ፡መብል፡ሰጥተዋል፤አቤቱ፥ተጐሳቍያለኹና፡እይ፥ተመልከትም።
12ላሜድ።እናንተ፡መንገድ፡ዐላፊዎች፡ዅሉ፥በእናንተ፡ዘንድ፡ምንም፡የለምን፧እግዚአብሔር፡በጽኑ፡ ቍጣው፡ቀን፡እኔን፡እንዳስጨነቀበት፡በእኔ፡ላይ፡እንደተደረገው፡እንደእኔ፡መከራ፡የሚመስል፡መከራ፡ እንዳለ፡ተመልከቱ፥እዩ።
13ሜም።ከላይ፡እሳትን፡ወደ፡ዐጥንቴ፡ሰደደ፡በረታችበትም፤ለእግሬ፡ወጥመድ፡ዘረጋ፡ወደ፡ዃላም፡ መለሰኝ፥አጠፋኝም፡ቀኑንም፡ዅሉ፡አደከመኝ።
14ኖን።የኀጢአቶቼ፡ቀንበር፡በእጁ፡ተይዛለች፤ታስረው፡በዐንገቴ፡ላይ፡ወጥተዋል፤ጕልበቴን፡ አደከመ።ጌታ፡በፊታቸው፡እቆም፡ዘንድ፡በማልችላቸው፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጠኝ።
15ሳምኬት።ጌታ፡ኀያላኔን፡ዅሉ፡ከውስጤ፡አስወገዳቸው፤ጕልማሳዎቼን፡ያደቅ፟፡ዘንድ፡ጉባኤን፡ ጠራብኝ፤ጌታ፡ድንግሊቱን፡የይሁዳን፡ልጅ፡በመጥመቂያ፡እንደሚረገጥ፡አድርጎ፡ረገጣት። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
16ዔ።የሚያጽናናኝ፡ነፍሴንም፡የሚያበረታት፡ከእኔ፡ርቋልና፥ስለዚህ፡አለቅሳለኹ፤ዐይኔ፥ዐይኔ፡ውሃ፡ ያፈሳ፟ል።ጠላት፡በርትቷልና፥ልጆቼ፡ጠፍተዋል።
17ፌ።ጽዮን፡እጇን፡ዘረጋች፤የሚያጽናናት፡የለም፤እግዚአብሔር፡በያዕቆብ፡ዙሪያ፡ያሉትን፡ እንዲያስጨንቁት፡አዘዘ፤ኢየሩሳሌም፡በመካከላቸው፡እንደ፡ርኩስ፡ነገር፡ኾናለች።
18ጻዴ።በአፉ፡ነገር፡ላይ፡ዐመፅ፡አድርጌያለኹና፥እግዚአብሔር፡ጻድቅ፡ነው።እናንተ፡አሕዛብ፡ ዅሉ፥እባካችኹ፡ስሙ፥መከራዬንም፡ተመልከቱ፤ደናግሎቼና፡ጐበዛዝቴ፡ተማርከው፡ኼዱ።
19ቆፍ።ውሽማዎቼን፡ጠራኹ፥እነርሱም፡አታለሉኝ፤ካህናቴና፡ሽማግሌዎቼ፡ሰውነታቸውን፡ያበረቱ፡ዘንድ፡ መብል፡ሲፈልጉ፡በከተማ፡ውስጥ፡ሞቱ።
20ሬስ።አቤቱ፥ተጨንቄያለኹና፥አንዠቴም፡ታውኮብኛልና፥ተመልከት፤ዐመፃን፡ፈጽሞ፡አድርጌያለኹና፡ ልቤ፡በውስጤ፡ተገላበጠብኝ፤በሜዳ፡ሰይፍ፡ልጆቼን፡አጠፋ፡በቤትም፡ሞት፡አለ።
21ሳን።እኔ፡እየጮኽኹ፡እንደማለቅስ፡ሰምተዋል፤የሚያጽናናኝ፡የለም፤ጠላቶቼ፡ዅሉ፡ስለ፡መከራዬ፡ ሰምተዋል፤አንተ፡አድርገኸዋልና፥ደስ፡አላቸው፤ስለ፡ርሱ፡የተናገርኸውን፡ቀን፡ታመጣለኽ፡እነርሱም፡እንደ፡ እኔ፡ይኾናሉ።
22ታው።ልቅሶዬ፡እጅግ፡ነውና፥ልቤም፡ደክሟልና፥ክፋታቸው፡ዅሉ፡ወደ፡ፊትኽ፡ይድረስ፥ስለ፡ ኀጢአቴ፡ዅሉ፡እንዳደረግኽብኝ፡አድርግባቸው።