Skip to content
← Lamentations

Chapter 2 · Amharic

Lamentations

1አሌፍ።ጌታ፡በቍጣው፡የጽዮንን፡ሴት፡ልጅ፡እንደ፡ምን፡አደመናት! የእስራኤልን፡ውበት፡ከሰማይ፡ወደ፡ ምድር፡ጣለ፥በቍጣውም፡ቀን፡የእግሩን፡መረገጫ፡አላሰበም።

2ቤት።ጌታ፡የያዕቆብን፡ማደሪያዎች፡ዅሉ፡ዋጠ፥አልራራምም፤በመዓቱ፡የይሁዳን፡ሴት፡ልጅ፡ዐምባዎች፡ አፈረሰ፥ወደ፡ምድርም፡አወረዳቸው፤መንግሥቱንና፡አለቃዎቿን፡አረከሰ።

3ጋሜል።በጽኑ፡ቍጣው፡የእስራኤልን፡ቀንድ፡ዅሉ፡ቀጠቀጠ፤ቀኝ፡እጁን፡ከጠላት፡ፊት፡ወደ፡ዃላ፡ መለሰ፥በዙሪያውም፡እንደሚባላ፡እንደ፡እሳት፡ነበልባል፡ያዕቆብን፡አቃጠለ።

4ዳሌጥ።ቀስቱን፡እንደ፡ጠላት፡ገተረ፥እንደ፡አስጨናቂ፡ቀኝ፡እጁን፡አጸና፥ለዐይንም፡የሚያምረውን፡ ዅሉ፡ገደለ፤በጽዮን፡ሴት፡ልጅ፡ድንኳን፡መዓቱን፡እንደ፡እሳት፡አፈሰሰ።

5ሄ።ጌታ፡እንደ፡ጠላት፡ኾነ፥እስራኤልን፡ዋጠ፤አዳራሾቿን፡ዅሉ፡ዋጠ፥ዐምባዎቿን፡አጠፋ፤በይሁዳም፡ ሴት፡ልጅ፡ሐዘንና፡ልቅሶ፡አበዛ።

6ዋው።ማደሪያውን፡እንደ፡አትክልት፡ነቀለ፤የበዓሉን፡ስፍራ፡አጠፋ፤እግዚአብሔር፡በጽዮን፡ዓመት፡ በዓሉንና፡ሰንበቱን፡አስረሳ፥በቍጣውም፡መዓት፡ንጉሡንና፡ካህኑን፡አቃለለ።

7ዛይ።ጌታ፡መሠዊያውን፡ጣለ፥መቅደሱን፡ጠላ፥የአዳራሾቿንም፡ቅጥር፡በጠላት፡እጅ፡አሳልፎ፡ ሰጠ፤ድምፃቸውን፡እንደ፡ዓመት፡በዓል፡ቀን፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ከፍ፡ከፍ፡አደረጉ።

8ሔት።እግዚአብሔር፡የጽዮንን፡ሴት፡ልጅ፡ቅጥር፡ያፈርስ፡ዘንድ፡ዐሰበ፤የመለኪያውን፡ገመድ፡ ዘረጋ፥እጁን፡ከማጥፋት፡አልመለሰም፤ምሽጉና፡ቅጥሩ፡እንዲያለቅሱ፡አደረገ፤በአንድነት፡ደከሙ።

9ጤት።በሮቿ፡በመሬት፡ውስጥ፡ሰጠሙ፥መወርወሪያዎቿን፡አጠፋ፡ሰበረም፤ንጉሧና፡አለቃዎቿ፡ሕግ፡ በሌለባቸው፡በአሕዛብ፡መካከል፡አሉ፤ነቢያቷም፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ራእይ፡አላገኙም።

10ዮድ።የጽዮን፡ሴት፡ልጅ፡ሽማግሌዎች፡ዝም፡ብለው፡በመሬት፡ላይ፡ተቀምጠዋል፤ትቢያን፡በራሳቸው፡ ላይ፡ነሰነሱ፥ማቅም፡ታጠቁ፤የኢየሩሳሌም፡ደናግል፡ራሳቸውን፡ወደ፡ምድር፡አዘነበሉ።

11ካፍ።ሕፃኑና፡ጡት፡የሚጠባው፡በከተማዪቱ፡ጐዳና፡ላይ፡ሲዝሉ፥ዐይኔ፡በእንባ፡ደከመች፥አንዠቴም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ታወከ፤ስለወገኔ፡ሴት፡ልጅ፡ቅጥቃጤ፡ጕበቴ፡በምድር፡ላይ፡ተዘረገፈ።

12ላሜድ።በከተማ፡ጐዳና፡እንደ፡ተወጋ፡ሰው፡በዛሉ፡ጊዜ፥ነፍሳቸውም፡በእናቶቻቸው፡ብብት፡በወጣች፡ ጊዜ፥እናቶቻቸውን፦እኽልና፡የወይን፡ጠጅ፡ወዴት፡አለ፧ይሏቸዋል።

13ሜም።የኢየሩሳሌም፡ሴት፡ልጅ፡ሆይ፥ምን፡እመሰክርልሻለኹ፧በምንስ፡እመስልሻለኹ፧ድንግሊቱ፡ የጽዮን፡ልጅ፡ሆይ፥አጽናናሽ፡ዘንድ፡በምን፡አስተካክልሻለኹ፧ስብራትሽ፡እንደ፡ባሕር፡ታላቅ፡ ነውና፤የሚፈውስሽ፡ማን፡ነው፧

14ኖን።ነቢያትሽ፡ከንቱና፡ሐሰተኛ፡ራእይ፡አይተውልሻል፤ምርኮሽንም፡ይመልሱ፡ዘንድ፡በደልሽን፡ አልገለጡም፤ከንቱና፡የማይረባ፡ነገርንም፡አይተውልሻል።

15ሳምኬት።መንገድ፡ዐላፊዎች፡ዅሉ፡እጃቸውን፡ያጨበጭቡብሻልና፦በእውኑ፡የውበት፡ፍጻሜና፡የምድር፡ ዅሉ፡ደስታ፡የሚሏት፡ከተማ፡ይህች፡ናትን፧እያሉ፥በኢየሩሳሌም፡ሴት፡ልጅ፡ላይ፡ያፏጫሉ፥ራሳቸውንም፡ ያነቃንቃሉ።

16ዔ።ጠላቶችሽ፡ዅሉ፡አፋቸውን፡አላቀቁብሽ፤እያፏጩና፡ጥርሳቸውን፡እያፋ፟ጩ፦ውጠናታል፤ነገር፡ ግን፥ተስፋ፡ያደረግናት፡ቀን፡ይህች፡ናት፤አግኝተናታል፥አይተናትማል፡ይላሉ።

17ፌ።እግዚአብሔር፡ያሰበውን፡አደረገ፤በቀድሞ፡ዘመን፡ያዘዘውን፡ቃል፡ፈጸመ፤አፈረሰ፡ አልራራምም፤ጠላትንም፡ደስ፡አሠኘብሽ፥የሚያስጨንቁሽንም፡ቀንድ፡ከፍ፡ከፍ፡አደረገ።

18ጻዴ።ልባቸው፡ወደ፡ጌታ፡ጮኸ፦የጽዮን፡ሴት፡ልጅ፡ቅጥር፡ሆይ፥እንባሽን፡እንደ፡ፈሳሽ፡ቀንና፡ ሌሊት፡አፍሺ፟፤ለሰውነትሽ፡ዕረፍት፡አትስጪ፤የዐይንሽ፡ብሌን፡አታቋርጥ።

19ቆፍ።ተነሺ፥በሌሊት፡በመዠመሪያ፡ክፍል፡ጩኺ፥በጌታም፡ፊት፡ልብሽን፡እንደ፡ውሃ፡ አፍሺ፟፤በጐዳና፡ዅሉ፡ራስ፡ላይ፡በራብ፡ስለደከሙ፡ስለሕፃናትሽ፡ነፍስ፡እጆችሽን፡ወደ፡ርሱ፡አንሺ።

20ሬስ።አቤቱ፥እይ፤በማን፡ላይ፡እንደዚህ፡እንዳደረግኽ፡ተመልከት።በእውኑ፡ሴቶች፡ ፍሬያቸውን፥ያቀማጠሏቸውን፡ሕፃናት፥ይበላሉን፧በእውኑ፡ካህኑና፡ነቢዩ፡በጌታ፡መቅደስ፡ውስጥ፡ይገደላሉን፧

21ሳን።ብላቴናውና፡ሽማግሌው፡በመንገዶች፡ላይ፡ተጋደሙ፤ደናግሎቼና፡ጐበዛዝቴ፡በሰይፍ፡ ወድቀዋል፤በቍጣኽ፡ቀን፡ገደልኻቸው፤ሳትራራ፡ዐረድኻቸው።

22ታው።እንደ፡በዓል፡ቀን፡የሚያስፈሩኝን፡ከዙሪያዬ፡ጠራኽ፥በእግዚአብሔር፡ቍጣ፡ቀንም፡ያመለጠ፡ ወይም፡የቀረ፡አልተገኘም፤ያቀማጠልዃቸውንና፡ያሳደግዃቸውን፡ጠላቴ፡በላቸው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source